የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 24

24
የዛ​ገች ድስት ምሳሌ
1በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! የዚ​ህን ቀን፥ የዛ​ሬን ቀን ስም ጻፍ፤ በዚህ ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመ​ጣ​ልና። 3ለዐ​መ​ፀ​ኛ​ውም ቤት ምሳ​ሌን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስ​ቲ​ቱን ጣድ፥ ውኃም ጨም​ር​ባት። 4ቍራ​ጭ​ዋ​ንም፥ መል​ካ​ሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑ​ንና ወር​ቹን በእ​ር​ስዋ ውስጥ ጨምር፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም አጥ​ን​ቶች ሙላ​ባት። 5ከመ​ን​ጋው የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ውሰድ፤ አጥ​ን​ቶ​ቹም እን​ዲ​በ​ስሉ በበ​ታ​ችዋ እሳት አን​ድድ፤ አፍ​ላው፤ በእ​ጅጉ ይፍላ፤ አጥ​ን​ቶ​ቹም በው​ስ​ጥዋ ይቀ​ቀሉ።
6“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዝገቷ ላለ​ባት፥ ዝገ​ቷም ከእ​ር​ስዋ ላል​ወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! ቍራጭ ቍራ​ጩን አውጣ፤ ዕጣ አል​ወ​ደ​ቀ​ባ​ትም። 7ደም​ዋም በመ​ካ​ከ​ልዋ አለ። በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ገ​ችው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔ በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አኖ​ር​ሁት እንጂ በአ​ፈር ይከ​ደን ዘንድ በመ​ሬት ላይ አላ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ትም” ይላል። እንጂ በአ​ፈር ይከ​ደን ዘንድ በመ​ሬት ላይ አላ​ፈ​ሰ​ሰ​ች​ውም። 8መዓ​ቴን አወጣ ዘንድ፥ በቀ​ሌ​ንም እበ​ቀል ዘንድ፥ ደምዋ እን​ዳ​ይ​ከ​ደን በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ግሁ። 9ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! እኔ ደግሞ ማገ​ዶ​ዋን ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። 10ደሟ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ ሥጋዋ ያርር ዘንድ፥ አጥ​ን​ቶ​ች​ዋም ይቀ​ጠ​ቀጡ ዘንድ፤ እን​ጨ​ቱን አበ​ዛ​ለሁ፤ እሳ​ቱ​ንም አነ​ድ​ዳ​ለሁ፥#ዕብ. “ሥጋ​ውን ቀቅል ፤ መረ​ቁ​ንም አጣ​ፍ​ጠው ፤ አጥ​ን​ቶቹ ይቃ​ጠሉ” ይላል። 11ድስ​ቷም እስ​ክ​ት​ፈ​ላና እስ​ክ​ት​ሰ​በር ድረስ በፍሙ ላይ አኖ​ራ​ታ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ዋም በመ​ካ​ከሏ እንደ ሰም ይቀ​ል​ጣል፤ ዝገ​ት​ዋም ይጠ​ፋል፤#ዕብ. “ትሞ​ቅም ዘንድ፥ ናስ​ዋም ትግል ዘንድ፥ ርኩ​ሰ​ቷም በው​ስ​ጥዋ ይቀ​ልጥ ዘንድ፥ ዝገ​ቷም ይጠፋ ዘንድ ባዶ​ዋን በፍም ላይ አድ​ር​ጋት” ይላል። 12በከ​ንቱ ደከ​መች፤ ሆኖም#“በከ​ንቱ ደከ​መች ሆኖም ...” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ብዙ ዝገቷ ከእ​ር​ስዋ#ዕብ. “በእ​ሳት እንኳ” ይላል። አል​ለ​ቀ​ቀም። 13በር​ኵ​ሰ​ትሽ ሴሰ​ኝ​ነት አለ፤ አነ​ጻ​ሁሽ፤ አል​ነ​ጻ​ሽ​ምና መዓ​ቴን በላ​ይሽ እስ​ክ​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ ከር​ኵ​ሰ​ትሽ አት​ነ​ጺም። 14እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እመ​ጣ​ለሁ፤ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ውም፤ አል​ራ​ራም፤ አል​ጸ​ጸ​ትም፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽና እንደ ሥራ​ሽም እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ የሰ​ውን ደም እንደ አፈ​ሰ​ስሽ እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ት​ሽም ተበ​ቅዬ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ስም​ሽም ጐሰ​ቈለ፥ ብዙ ኀዘ​ን​ንም ታዝ​ኛ​ለሽ።”
የነ​ቢዩ ሚስት መሞት
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 16“የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐ​ይ​ን​ህን አም​ሮት በመ​ቅ​ሠ​ፍት እወ​ስ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ዋይ አት​በል፤ አታ​ል​ቅ​ስም፤ እን​ባ​ህ​ንም አታ​ፍ​ስስ። 17በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”
18እኔም በማ​ለዳ ለሕ​ዝቡ ተና​ገ​ርሁ፤ ወደ ማታም ሚስቴ ሞተች፤ በነ​ጋ​ውም እንደ ታዘ​ዝሁ አደ​ረ​ግሁ። 19ሕዝ​ቡም፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ለእኛ ምን እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን?” አሉኝ። 20እኔም እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 21ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የኀ​ይ​ላ​ች​ሁን ትም​ክ​ሕት፥ የዐ​ይ​ና​ች​ሁን አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ች​ሁ​ንም ምኞት፥ መቅ​ደ​ሴን አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ። 22እኔም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸው አት​ጽ​ና​ኑም፤#ዕብ. “ከን​ፈ​ራ​ች​ሁ​ንም አት​ሸ​ፍ​ኑም ...” ይላል። የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​በ​ሉም። 23መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ች​ሁም በራ​ሳ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ዋይ አት​ሉም፤ አታ​ለ​ቅ​ሱ​ምም፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁም ትሰ​ለ​ስ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ጓደ​ኞ​ቻ​ች​ሁን ታጽ​ና​ና​ላ​ችሁ። 24ሕዝ​ቅ​ኤ​ልም ምል​ክት ይሆ​ና​ች​ኋል፤ እርሱ እንደ አደ​ረገ ሁሉ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።
25“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይ​ላ​ቸ​ውን፥ የተ​መ​ኩ​በ​ት​ንም ደስታ፥ የዐ​ይ​ና​ቸ​ው​ንም አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ምኞት፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ሰ​ድ​ሁ​ባ​ቸው ቀን፥ 26በዚያ ቀን ያመ​ለ​ጠው ይህን ነገር በጆ​ሮህ ያሰማ ዘንድ ወደ አንተ ይመ​ጣል። 27በዚያ ቀን አፍህ ላመ​ለ​ጠው ይከ​ፈ​ታል፤ አን​ተም ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ዲዳ አት​ሆ​ንም፤ ምል​ክ​ትም ትሆ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ