የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 26

26
በጢ​ሮስ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ከወሩ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰ​በ​ረች፥ ጠፋ​ችም፥ ሕዝ​ቧም ወደ እር​ስዋ ተመ​ለሱ፤ ሞልታ የነ​በ​ረች አለ​ቀች ብላ​ለ​ችና፤ 3ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕ​ርም ሞገ​ድ​ዋን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ እን​ዲሁ ብዙ አሕ​ዛ​ብን አወ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ። 4የጢ​ሮ​ስ​ንም ቅጥ​ሮች ያፈ​ር​ሳሉ፤ ግን​ቦ​ች​ዋ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ ትቢ​ያ​ዋ​ንም ከእ​ር​ስዋ እፍ​ቃ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋ​ይም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። 5በባ​ሕር ውስጥ የመ​ረብ ማስጫ ትሆ​ና​ለች፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብዝ​በዛ ትሆ​ና​ለች። 6በሜዳ ያሉ​ትም ሴቶች ልጆ​ችዋ በሰ​ይፍ ይገ​ደ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።
7“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰ​ሜን የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከሰ​ረ​ገ​ሎች፥ ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችም፥ ከጉ​ባ​ኤና ከብዙ ሕዝ​ብም ጋር በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ። 8እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤ 9ግን​ቦ​ች​ሽ​ንና ቅጥ​ር​ሽን በም​ሳር ያፈ​ር​ሳል። 10ከፈ​ረ​ሶ​ቹም ብዛት የተ​ነሣ በት​ቢያ ይሸ​ፍ​ን​ሻል፤ ከሠ​ረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵ​ርና ከፈ​ረ​ሶቹ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ቅጥ​ሮ​ች​ሽን ያፈ​ር​ሳል፤ ወን​በዴ መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እን​ዲ​ገባ በሮ​ች​ሽን ይገ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል። 11ፈረ​ሶቹ አደ​ባ​ባ​ይ​ሽን ይረ​ግ​ጣሉ፤ ሠራ​ዊ​ቶ​ች​ሽ​ንም በሾ​ተል ይገ​ድ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የጸና አር​በ​ኛ​ሽ​ንም በም​ድር ላይ ይጥ​ለ​ዋል። 12ገን​ዘ​ብ​ሽን ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ መን​ጋ​ሽ​ንም ይዘ​ር​ፋሉ፤ አም​ባ​ሽ​ንም ይን​ዳሉ፤ የተ​ወ​ደዱ ቤቶ​ች​ሽ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ እን​ጨ​ቶ​ች​ሽ​ንና ድን​ጋ​ይ​ሽን፥ መሬ​ት​ሽ​ንም በባ​ሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥ​ሉ​ታል። 13የዘ​ፋ​ኞ​ች​ሽ​ንም ብዛት ዝም አሰ​ኛ​ለሁ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ሽም ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይ​ሰ​ማም። 14እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋይ አደ​ር​ግ​ሻ​ለሁ፤ የመ​ረ​ብም ማስጫ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ሠ​ሪም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
15“ስለ ጢሮስ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሾተ​ላ​ቸ​ውን በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ዘዙ ጊዜ ከው​ድ​ቀ​ትሽ፥ ከቈ​ሰ​ሉ​ትም ጩኸት የተ​ነሣ፤ ደሴ​ቶች የሚ​ነ​ዋ​ወጡ አይ​ደ​ለ​ምን? 16የባ​ሕ​ርም አለ​ቆች ሁሉ ከዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ ዘው​ዳ​ቸ​ውን ከራ​ሳ​ቸው ያወ​ር​ዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያወ​ል​ቃሉ፤ በመ​ሬ​ትም ላይ ተቀ​ም​ጠው ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ራሉ፤ ስለ አን​ቺም ያለ​ቅ​ሳሉ። 17በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ! 18አሁን በው​ድ​ቅ​ትሽ ቀን ደሴ​ቶች ይፈ​ራሉ፥#“በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያሉ ደሴ​ቶች ከመ​ው​ጣ​ትሽ የተ​ነሣ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያሉ ደሴ​ቶች ከመ​ው​ጣ​ትሽ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።
19“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰው እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ባድማ ከተማ ባደ​ረ​ግ​ሁሽ ጊዜ፥ ቀላ​ዩ​ንም ባወ​ጣ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆ​ችም በከ​ደ​ኑሽ ጊዜ፥ 20ወደ ጥልቁ ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ወደ ቀደ​ሙት ሕዝብ አወ​ር​ድ​ሻ​ለሁ። በም​ድ​ርም ላይ በሕ​ይ​ወ​ትሽ ጸን​ተሽ እን​ዳ​ት​ኖ​ሪም ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈ​ረ​ሰው ቤት ከም​ድር በታች አኖ​ር​ሻ​ለሁ። 21ለሞት እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሪም፤ ይፈ​ል​ጉ​ሻል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አያ​ገ​ኙ​ሽም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ