የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 32

32
ሙሾ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ኦን
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ዖን ሙሾ አሙሽ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ የአ​ሕ​ዛ​ብን አን​በሳ መስ​ለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነ​ሃል፤ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም ወግ​ተ​ሃል፤ ውኃ​ው​ንም በእ​ግ​ርህ አደ​ፍ​ር​ሰ​ሃል፥ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም በተ​ረ​ከ​ዝህ ረግ​ጠ​ሃል። 3ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በብዙ አሕ​ዛብ ጉባኤ መረ​ቤን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ረ​ቤም አወ​ጣ​ሃ​ለሁ። 4በሰፊ ምድረ በዳም እጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ሁሉ ከአ​ንተ አጠ​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። 5ሥጋ​ህን በተ​ራ​ሮች ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በደ​ም​ህም አረ​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።#ዕብ. “ሸለ​ቆ​ቹ​ንም በሬ​ሳህ ክምር እሞ​ላ​ለሁ” ይላል። 6የም​ቷ​ኝ​ባ​ት​ንም#“የም​ቷ​ኝ​ባ​ት​ንም” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ምድር እስከ ተረ​ራ​ሮች ድረስ በደ​ምህ አጠ​ጣ​ለሁ፤ መስ​ኖ​ዎ​ችም ከአ​ንተ ይሞ​ላሉ። 7በጠ​ፋ​ህም ጊዜ ሰማ​ዮ​ችን እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ ፀሐ​ዩ​ንም በደ​መና እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ጨረ​ቃም ብር​ሃ​ኑን አይ​ሰ​ጥም። 8የሰ​ማ​ይን ብር​ሃ​ኖች ሁሉ በላ​ይህ አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ በም​ድ​ር​ህም ላይ ጨለ​ማን አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9በማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ድል መሆ​ን​ህን በአ​ሰ​ማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝ​ብን ልብ አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ። 10ብዙ አሕ​ዛ​ብን አስ​ደ​ን​ቅ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፌም በፊ​ታ​ቸው በተ​ወ​ረ​ወ​ረች ጊዜ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸው እጅግ አድ​ር​ገው ይፈ​ራሉ፤ በወ​ደ​ቅ​ህ​ባ​ትም ቀን እያ​ን​ዳ​ንዱ ስለ ነፍሱ በየ​ጊ​ዜው ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል።”
11ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመ​ጣ​ብ​ሃል። 12በኀ​ያ​ላን ሰይፍ ኀይ​ል​ህን እጥ​ላ​ለሁ፤ ሁሉ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች ናቸው፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ትዕ​ቢት ያጠ​ፋሉ፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ ይደ​መ​ሰ​ሳል። 13በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ ያሉ​ትን እን​ስ​ሶች ሁሉ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ የሰው እግር አያ​ደ​ፈ​ር​ሳ​ትም፤ የእ​ን​ስ​ሳም ኮቴ አይ​ረ​ግ​ጣ​ትም። 14በዚ​ያን ጊዜ ውኆ​ቻ​ቸ​ውን አጠ​ራ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ዘይት ይፈ​ስ​ሳሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 15የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ባድ​ማና ውድማ በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ ምድ​ርም በመ​ላዋ በጠ​ፋች ጊዜ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ሠ​ፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 16ይኸ​ውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ የአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ ስለ ግብ​ፅና ስለ ኀይ​ልዋ ሁሉ ያሞ​ሹ​ለ​ታል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ሙሾ ስለ ግብፅ
17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 18“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞ​ቱት ሴቶች ልጆች” ይላል። ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው። 19በው​በት የም​ት​በ​ል​ጪው ማን ነው? ውረጂ ካል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም ጋር ተኚ። 20በሰ​ይፍ በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከእ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ሉም ሁሉ ይጠ​ፋል፤#ዕብ. “ለሰ​ይፍ ተሰ​ጥ​ታ​ለች” ይላል። እር​ስ​ዋ​ንና ብዛ​ቷን ሁሉ ጐትቱ። 21የኀ​ያ​ላን አለ​ቆች በሲ​ኦል ውስጥ ሆነው ከረ​ዳ​ቶቹ ጋር ይና​ገ​ሩ​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም የተ​ገ​ደ​ሉት ያል​ተ​ገ​ረዙ ወር​ደው ተኝ​ተ​ዋል።
22“አሦ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በዚያ ተገ​ደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘ​ቅ​ትም ጣሉ​አ​ቸው#“ሁሉም ድል ተነሡ ወደ ጥልቅ ዐዘ​ቅ​ትም ጣሉ​አ​ቸው” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪኩ የለም። ሠራ​ዊ​ቱም በመ​ቃ​ብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ደሉ። 23መቃ​ብ​ራ​ቸው በጕ​ድ​ጓዱ በው​ስ​ጠ​ኛው ክፍል ነው፤ ጉባ​ኤ​ዋም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል።
24“ኤላ​ምም በዚያ አለች፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ ሳይ​ገ​ረ​ዙም ወደ ታች​ኛው ምድር ወር​ደ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ተ​ዋል። 25በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከብ​ዛቷ ሁሉ ጋር መኝ​ታን አድ​ር​ገ​ው​ላ​ታል፤ መቃ​ብ​ርዋ በዙ​ሪ​ያዋ ነው፤ ሁሉም ያል​ተ​ገ​ረ​ዙና በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ ናቸው፤ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ያስ​ፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ገ​ደ​ሉ​ትም መካ​ከል ተሰ​ጥ​ተ​ዋል።
26“ሞሳ​ሕና ቶቤል፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ነው፤ ሁሉም ሳይ​ገ​ረዙ በሰ​ይፍ ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ነበ​ርና። 27በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ኀያ​ላ​ኑን ያስ​ፈሩ ነበ​ርና፤ መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወ​ረዱ፥ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ከራ​ሳ​ቸው በታች ከአ​ደ​ረጉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ጥ​ን​ታ​ቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወ​ደቁ ካል​ተ​ገ​ረዙ ኀያ​ላን ጋር ይተ​ኛሉ። 28አን​ተም ደግሞ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትሰ​በ​ራ​ለህ፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ትተ​ኛ​ለህ።
29“ኤዶ​ም​ያ​ስና ነገ​ሥ​ታቷ፥ አለ​ቆ​ች​ዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር 30ከአ​ል​ተ​ገ​ረ​ዙና ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተኝ​ተ​ዋል፤ የሰ​ሜን አለ​ቆች ሁሉ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ወር​ደው በዚያ አሉ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸ​ውም ያስ​ፈሩ በነ​በ​ረው ፍር​ሀት አፍ​ረ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ተኝ​ተ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል።
31“በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ#“በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ፈር​ዖ​ንና ሠራ​ዊቱ#“ሰራ​ዊቱ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁሉ ያዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ፈር​ዖ​ንም ስለ ኀይ​ላ​ቸው ሁሉ ይጽ​ና​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 32መፈ​ራ​ቴን በሕ​ያ​ዋን ምድር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ፈር​ዖ​ንና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በሰ​ይፍ በተ​ገ​ደ​ሉት፥ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ይተ​ኛሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ