ትንቢተ ሕዝቅኤል 32
32
ሙሾ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርኦን
1እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል። 3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በመረቤም አወጣሃለሁ። 4በሰፊ ምድረ በዳም እጥልሃለሁ፤ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፤ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። 5ሥጋህን በተራሮች ላይ አደርጋለሁ፤ በደምህም አረካቸዋለሁ።#ዕብ. “ሸለቆቹንም በሬሳህ ክምር እሞላለሁ” ይላል። 6የምቷኝባትንም#“የምቷኝባትንም” የሚለው በዕብ. ብቻ። ምድር እስከ ተረራሮች ድረስ በደምህ አጠጣለሁ፤ መስኖዎችም ከአንተ ይሞላሉ። 7በጠፋህም ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብትንም አጨልማለሁ፤ ፀሐዩንም በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም። 8የሰማይን ብርሃኖች ሁሉ በላይህ አጨልማለሁ፤ በምድርህም ላይ ጨለማን አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 9በማታውቃቸውም ሀገሮች በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ድል መሆንህን በአሰማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ። 10ብዙ አሕዛብን አስደንቅብሃለሁ፤ ሰይፌም በፊታቸው በተወረወረች ጊዜ ንጉሦቻቸው እጅግ አድርገው ይፈራሉ፤ በወደቅህባትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ይንቀጠቀጣል።”
11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል። 12በኀያላን ሰይፍ ኀይልህን እጥላለሁ፤ ሁሉ የአሕዛብ ጨካኞች ናቸው፤ የግብፅንም ትዕቢት ያጠፋሉ፤ ኀይልዋም ሁሉ ይደመሰሳል። 13በብዙም ውኃ አጠገብ ያሉትን እንስሶች ሁሉ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የሰው እግር አያደፈርሳትም፤ የእንስሳም ኮቴ አይረግጣትም። 14በዚያን ጊዜ ውኆቻቸውን አጠራለሁ፤ ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት ይፈስሳሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 15የግብፅንም ምድር ባድማና ውድማ በአደረግሁ ጊዜ፥ ምድርም በመላዋ በጠፋች ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 16ይኸውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞሹለታል፤ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች ያሞሹለታል፤ ስለ ግብፅና ስለ ኀይልዋ ሁሉ ያሞሹለታል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሙሾ ስለ ግብፅ
17እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 18“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እርስዋንና የብርቱዎቹን አሕዛብ ሴቶች ልጆች#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞቱት ሴቶች ልጆች” ይላል። ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው። 19በውበት የምትበልጪው ማን ነው? ውረጂ ካልተገረዙትም ጋር ተኚ። 20በሰይፍ በተገደሉት መካከል ከእርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ኀይሉም ሁሉ ይጠፋል፤#ዕብ. “ለሰይፍ ተሰጥታለች” ይላል። እርስዋንና ብዛቷን ሁሉ ጐትቱ። 21የኀያላን አለቆች በሲኦል ውስጥ ሆነው ከረዳቶቹ ጋር ይናገሩታል፤ በሰይፍም የተገደሉት ያልተገረዙ ወርደው ተኝተዋል።
22“አሦርና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ተገደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘቅትም ጣሉአቸው#“ሁሉም ድል ተነሡ ወደ ጥልቅ ዐዘቅትም ጣሉአቸው” የሚለው በዕብ. እና በግሪኩ የለም። ሠራዊቱም በመቃብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀው ተገደሉ። 23መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል ነው፤ ጉባኤዋም በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል።
24“ኤላምም በዚያ አለች፤ ኀይልዋም ሁሉ በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል፤ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር ቅጣታቸውን አግኝተዋል። 25በተገደሉት መካከል ከብዛቷ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው፤ ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ በሕያዋንም ምድር ያስፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፤ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል።
26“ሞሳሕና ቶቤል፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና። 27በሕያዋንም ምድር ኀያላኑን ያስፈሩ ነበርና፤ መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ከአደረጉ፥ ኀጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወደቁ ካልተገረዙ ኀያላን ጋር ይተኛሉ። 28አንተም ደግሞ ባልተገረዙት መካከል ትሰበራለህ፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትተኛለህ።
29“ኤዶምያስና ነገሥታቷ፥ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር 30ከአልተገረዙና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል፤ የሰሜን አለቆች ሁሉ፥ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኀይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሀት አፍረዋል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ያልተገረዙት ተኝተዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ቅጣታቸውን ተሸክመዋል።
31“በሰይፍ የተገደሉ#“በሰይፍ የተገደሉ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ፈርዖንና ሠራዊቱ#“ሰራዊቱ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁሉ ያዩአቸዋል፤ ፈርዖንም ስለ ኀይላቸው ሁሉ ይጽናናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 32መፈራቴን በሕያዋን ምድር አድርጌአለሁ፤ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ በተገደሉት፥ ባልተገረዙት መካከል ይተኛሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 32: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ