የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 33

33
ሕዝ​ቅ​ኤል የእ​ስ​ራ​ኤል ጕበኛ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ለሕ​ዝ​ብህ ልጆች ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጦርን በም​ድር ላይ በአ​መ​ጣሁ ጊዜ፥ የም​ድር ሕዝብ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አንድ ሰውን ወስ​ደው ለራ​ሳ​ቸው ጕበኛ ቢያ​ደ​ርጉ፥ 3እር​ሱም በም​ድር ላይ የመ​ጣ​ውን ጦር በአየ ጊዜ መለ​ከ​ትን ቢነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ቢያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፤ 4የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ የሚ​ሰማ ሰው ባይ​ጠ​ነ​ቀቅ፥ ጦር መጥቶ ቢወ​ስ​ደው፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል። 5የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ሰምቶ ስላ​ል​ተ​ጠ​ነ​ቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ ቢጠ​ነ​ቀ​ቅስ ኖሮ ነፍ​ሱን በአ​ዳነ ነበር። 6ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።
7“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።#“ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 8ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ ኀጢ​አ​ተኛ ሆይ! በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ከክፉ መን​ገዱ ታስ​ጠ​ነ​ቅቅ ዘንድ ባት​ና​ገር፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ። 9ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።
10“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት፦ እና​ንተ፦ በደ​ላ​ች​ንና ኀጢ​አ​ታ​ችን በላ​ያ​ችን አሉ፤ እኛም ሰል​ስ​ለ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ዴ​ትስ በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን? ብላ​ችሁ ተና​ግ​ራ​ች​ኋል በላ​ቸው። 11እኔ ሕያው ነኝና ኀጢ​አ​ተ​ኛው ከመ​ን​ገዱ ተመ​ልሶ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢ​አ​ተ​ኛው ይሞት ዘንድ አል​ፈ​ቅ​ድም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ተመ​ለሱ፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ? በላ​ቸው። 12አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብ​ህን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በበ​ደ​ለ​በት ቀን የጻ​ድቅ ጽድቁ አያ​ድ​ነ​ውም፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛም ከኀ​ጢ​አቱ በተ​መ​ለ​ሰ​በት ቀን በኀ​ጢ​አቱ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ ጻድ​ቁም ኀጢ​አት በሠ​ራ​በት ቀን በጽ​ድቁ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም። 13እኔ ጻድ​ቁን፦ በር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽ​ድቁ ታምኖ ኀጢ​አት ቢሠራ በሠ​ራው ኀጢ​አት ይሞ​ታል እንጂ ጽድቁ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም። 14እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤ 15ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም መያ​ዣን ቢመ​ልስ፥ የነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ቢከ​ፍል፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ትእ​ዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢ​አ​ትም ባይ​ሠራ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም። 16የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​በ​ትም፤ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን አድ​ር​ጎ​አ​ልና፤ በእ​ር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።
17“የሕ​ዝ​ብህ ልጆች፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ይላሉ፤ ነገር ግን የእ​ነ​ርሱ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም። 18ጻድቅ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ ይሞ​ት​በ​ታል። 19ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ቢያ​ደ​ርግ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ር​በ​ታል። 20እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ትላ​ላ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ላይ እንደ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ደቅ
21እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በተ​ማ​ረ​ክን በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪ​ክና የግ​እዝ ንባብ በ12ኛው ዓመት በ12ኛው ወር” ይላል። ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተ​ማ​ዪቱ ተያ​ዘች አለኝ። 22ያመ​ለ​ጠ​ውም ሳይ​መጣ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ በነ​ጋ​ውም ወደ እኔ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከ​ፈ​ተች፤ ከዚ​ያም በኋላ እኔ ዲዳ አል​ሆ​ን​ሁም።
23የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፥ 24“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ 25ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?#ምዕ. 33 ቍ. 25 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 26ሰይ​ፋ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ ቆማ​ች​ኋል፤ ርኩስ ነገ​ርን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሚስ​ቶች ታስ​ነ​ው​ራ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?#ምዕ. 33 ቍ. 26 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ስለ​ዚ​ህም እን​ዲህ በላ​ቸው፦ 27ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች ያሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በም​ድረ በዳ ያለ​ውን ለአ​ራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ችና በዋ​ሻ​ዎች ያሉ በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታሉ። 28ምድ​ሪ​ቱ​ንም ባድ​ማና ውድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ስድብ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትዕ​ቢት” ይላል። ይቀ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ማንም አያ​ል​ፍ​ባ​ቸ​ውም። 29ስላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ርኵ​ሰት ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ባድ​ማና ውድማ ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።
30“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብህ ልጆች በቅ​ጥር አጠ​ገ​ብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይና​ገ​ራሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አንዱ ከአ​ንዱ ጋር፦ እን​ሂ​ድና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ቃል እን​ስማ ይላሉ። 31ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥#ዕብ. “ብዙ ፍቅር ይገ​ል​ጣሉ” ይላል። ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።#ዕብ. “ልባ​ቸው ግን ስስ​ታ​ቸ​ውን ትከ​ተ​ላ​ለች” ይላል። 32እነሆ አንተ መል​ካም ድምፅ እን​ዳ​ለው እን​ደ​ሚ​ወ​ደድ መዝ​ሙር ማለ​ፊ​ያም አድ​ርጎ በገና እን​ደ​ሚ​ጫ​ወት ሰው #“ማለ​ፊ​ያም አድ​ርጎ እን​ደ​ሚ​ጫ​ወት ሰው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁነ​ህ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም። 33እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ይላሉ፦ እነሆ ይህ ይመ​ጣል፤ በመ​ጣም ጊዜ እነ​ርሱ ነቢይ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ነበረ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ