ትንቢተ ሕዝቅኤል 31
31
ግብፅ በዝግባ ዛፍ እንደምትመሰል
1እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ አንደኛው ዓመት በሦስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንንና ሕዝቡን እንዲህ በላቸው፦ በታላቅነትህ ማንን ትመስላለህ? 3እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመናዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ። 4ውኃም አበቀለው፥ ቀላይም አሳደገው፥ ወንዞችም በተተከለበት ዙሪያ ይጎርፉ ነበር፤ ፈሳሾቹንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ላከ። 5ስለዚህ ቁመቱ ከምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አለ፤ ቅርንጫፎቹም በዙ፤ ጫፎቹም ከብዙ ውኆች የተነሣ ረዘሙ። 6የሰማይም ወፎች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ተዋለዱ፤#ዕብ. “ጎጆቻቸውን ሠሩ” ይላል። የምድርም አራዊት ሁሉ ከጫፎቹ በታች ተዋለዱ፤ ከጥላውም በታች ታላላቆች አሕዛብ ሁሉ ይቀመጡ ነበር። 7ሥሩም በብዙ ውኃ አጠገብ ነበረና በታላቅነቱና በጫፎቹ ርዝመት የተዋበ ነበረ። 8በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አይተካከሉትም፥#ዕብ. “አላጨለሙትም” ይላል። ጥዶችም ቅርንጫፎቹን፥ አስታ የሚባለውም ዛፍ ጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ገነት ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር። 9በጫፎቹ ብዛት ውብ አደረግሁት፤ በእግዚአብሔርም ገነት በዔድን የነበሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑበት።
10“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራስህም በደመናት መካከል ደርሶአልና፤ ትዕቢቱንም አየሁ፤ 11በአሕዛብም አለቆች እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም እንደ ክፋቱ መጠን ያደርግበታል፤ እኔም አሳድደዋለሁ።#“እኔም አሳድደዋለሁ” የሚለው በዕብ. ብቻ። 12የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአሕዛብ ጨካኞች የሆኑ፥ ቈርጠው ጣሉት፤ በተራሮችና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ከጥላው ተመልሰው ተዉት። 13በወደቀው ግንድ ላይ የሰማይ ወፎች ሁሉ ይቀመጣሉ፤ የምድርም አራዊት ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይሆናሉ። 14በውኃው አጠገብ ያሉ የዕንጨቶች ሁሉ ቁመት እንዳይረዝም ራሱም ወደ ደመና እንዳይደርስ ያንም ውኃ የሚጠጡት እንጨቶች ሁሉ በርዝመታቸው ከእርሱ ጋራ እንዳይተካከሉ ሁሉም ወደ መቃብር በሚወርዱ ሰዎች መካከል በጥልቅ ምድር ሞቱ።
15“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶን አስለቀስሁ፤ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት፤ ፈሳሾችንም ከለከልሁ፤ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት። የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ። 16ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ከመውደቁ ድምፅ የተነሣ አሕዛብን አንቀጠቀጥሁ፤ ውኃም የሚጠጡ ሁሉ፥ ምርጦችና መልካሞች የሊባኖስ ዛፎች፥ የዔድን ዛፎች ሁሉ በታችኛው ምድር ውስጥ ተጽናንተዋል። 17እነርሱም በሰይፍ ወደ ተገደሉት ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወረዱ፤ በጥላው ሥር ይኖሩ የነበሩ ዘሮቹም በአሕዛብ መካከል ጠፉ።
18“በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማንን ትመስላለህ? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፤ በሰይፍም በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትተኛለህ። ይህም ፈርዖንና የሕዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 31: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ