ትንቢተ ሕዝቅኤል 30
30
ጌታ ግብፅን እንደሚቀጣ
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥#“ዋይ በሉ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ለቀኑ ወዮ! 3ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደመና ቀን፥ የአሕዛብ ማለቂያ ጊዜ ይሆናል። 4ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብፅ ውስጥ ይወድቃሉ፤ ብዛቷንም ይወስዳሉ፤ መሠረቷም ይፈርሳል። 5ኢትዮጵያና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፋርስ” ይላል። ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብያም፤ ቀርጤስም የተደባለቀ ሕዝብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳንንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።
6“እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ግብፅን የሚደግፉ ይወድቃሉ፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ#“ሰዌኔ” አስዋን ነው። ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 7ባድማም በሆኑ ሀገሮች መካከል ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞችዋም በፈረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ። 8እሳትንም በግብፅ ላይ በአነደድሁ ጊዜ፥ ረዳቶችዋም ሁሉ በተሰበሩ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 9በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው#“ተዘልለው” የሚለው በዕብ. ብቻ። የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ከፊቴ በመርከብ#“በመርከብ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይወጣሉ፤ በግብፅም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።
10“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የግብፅን ብዛት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አጠፋለሁ። 11እርሱና ሕዝቡ የአሕዛብም ኀያላን ምድሪቱን ለማጥፋት ይላካሉ፤ ግብፃውያንንም በሰይፍ ይወጉአቸዋል፤ ምድሪቱም በሙታን ትሞላለች። 12ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ምድሪቱንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰጣለሁ፥#“በክፉ ሰዎች እጅ እሰጣለሁ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ምድሪቱንና ሞላዋንም በባዕዳን እጅ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
13“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ፤ ምስሎቹንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መኳንንቶችንም” ይላል። ከሜምፎስ እሽራለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በግብፅ ምድር አለቃ አይሆንም፤ በግብፅ ምድር ላይም ፍርሀትን አደርጋለሁ። 14ጳትሮስንም አፈርሳለሁ፤ በጣኔዎስም ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዲዮስጶሊን ላይም ፍርድን አደርጋለሁ። 15በግብፅም ኀይል በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ የሜምፎስንም ብዛት አጠፋለሁ። 16በግብፅም ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ ሲንም ትታወካለች፤ ኖእም ትሰበራለች፤ ሜምፎስም ምድረ በዳ ትሆናለች። 17የሄልዮቱ ከተማና የቡባስቱም ጐልማሶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ሴቶችም ይማረካሉ። 18የግብፅን ቀንበር በዚያ በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይጠፋባታል፤ ደመናም ይጋርዳታል፤ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ። 19እንዲሁ በግብፅ ላይ ፍርድን አደርጋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
20እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ አንደኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 21“የሰው ልጅ ሆይ! የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፥ እነሆም ይድን ዘንድ መድኃኒት ቀብተው አያደርቁትም፤ ሰይፉንም ለመያዝ ኀይልን ያገኝ ዘንድ አልታሰረም። 22ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ የጸናችውንና የተሰበረችውንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የተዘረጋችውንም” ይላል። ክንዱን እሰብራለሁ፤ ሰይፉንም ከእጁ አስጥለዋለሁ። 23ግብፃውያንንም በአሕዛብ መካከል እበትናለሁ፤ በሀገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ። 24የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥#ዕብ. “የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ” ይላል። ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።#ዕብ. “ተወግቶም በሚሞተው እንጕርጕሮ በፊቱ ያንጐራጕራል” ይላል። 25የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አጸናለሁ፤ የፈርዖንም ክንድ ይወድቃል፤ ሰይፌንም በባቢሎን ንጉሥ እጅ በሰጠሁ ጊዜ፥ እርሱም በግብፅ ምድር ላይ በዘረጋው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 26ግብፃውያንንም በአሕዛብ መካከል እበትናለሁ፤ በሀገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 30: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ