የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 29

29
በግ​ብፅ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በግ​ብጽ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ አድ​ርግ፤ በእ​ር​ሱና በግ​ብፅ ሁሉ ላይም ትን​ቢት ተና​ገር፤ 3እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ። 4በመ​ን​ጋ​ጋ​ዎ​ችህ መቃ​ጥን አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህ​ንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ አጣ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ከወ​ን​ዞ​ች​ህም መካ​ከል አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ ይጣ​በ​ቃሉ። 5አን​ተ​ንና የወ​ን​ዞ​ች​ህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥ​ላ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ እንጂ አት​ከ​ማ​ችም፤ አት​ሰ​በ​ሰ​ብ​ምም፤ መብ​ልም አድ​ርጌ ለም​ድር አራ​ዊ​ትና ለሰ​ማይ ወፎች ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ። 6ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሸ​ን​በቆ በትር ሁነ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና በግ​ብፅ የሚ​ኖሩ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 7በእጅ በያ​ዙህ ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ጫን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አቈ​ሰ​ልህ፤ በተ​ደ​ገ​ፉ​ብ​ህም ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥህ።
8“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፦ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ። 9የግ​ብ​ፅም ምድር ባድ​ማና ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው፤ የሠ​ራ​ሁ​ትም እኔ ነኝ ብለ​ሃ​ልና። 10ስለ​ዚህ፥ እነሆ በአ​ን​ተና በወ​ን​ዞ​ችህ ላይ ነኝ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ከሚ​ግ​ዶል ጀምሮ እስከ ሰዌ​ኔና እስከ ኢት​ዮ​ጵያ ዳርቻ ድረስ በጦ​ርና በቸ​ነ​ፈር ውድ​ማና ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። 11የሰው እግር አያ​ል​ፍ​ባ​ትም፤ የእ​ን​ስ​ሳም ኮቴ አይ​ረ​ግ​ጣ​ትም፥ እስከ አርባ ዓመ​ትም ድረስ ማንም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም። 12ባድ​ማም በሆኑ ምድ​ሮች መካ​ከል የግ​ብ​ፅን ምድር ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በፈ​ረ​ሱ​ትም ከተ​ሞች መካ​ከል ከተ​ሞ​ችዋ አርባ ዓመት ፈር​ሰው ይቀ​መ​ጣሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
13ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከአ​ርባ ዓመት በኋላ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ዘንድ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ 14የግ​ብ​ፅ​ንም ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ወደ ተወ​ለ​ዱ​ባ​ትም ምድር ወደ ጳት​ሮስ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ያም የተ​ዋ​ረ​ደች መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ። 15እንደ ገና በአ​ሕ​ዛብ ላይ ከፍ ከፍ እን​ዳ​ይሉ ትንሽ መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ላይ እን​ዳ​ይ​በዙ አሳ​ን​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ። 16የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እነ​ር​ሱን በተ​ከ​ተሉ ጊዜ እር​ስዋ በደ​ልን ታሳ​ስ​ባ​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ መታ​መኛ አት​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”
ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ግብ​ፅን ድል እንደ አደ​ረገ
17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 18“የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊ​ቱን በጢ​ሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠ​ራ​ቸው፤ ራስ ሁሉ የተ​ላጨ፥ ጫን​ቃም ሁሉ የተ​ላጠ ሆኖ​አል፤ ነገር ግን በላ​ይዋ ስለ አሠ​ራው ሥራ እር​ሱና ሠራ​ዊቱ ከጢ​ሮስ ደመ​ወዝ አል​ተ​ቀ​በ​ሉም። 19ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል። 20ስለ እኔ ሠር​ተ​ዋ​ልና በጢ​ሮስ ላይ ስለ አገ​ለ​ገ​ለው አገ​ል​ግ​ሎት የግ​ብ​ፅን ምድር ደመ​ወዝ አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
21“በዚያ ቀን ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ንተ የተ​ከ​ፈተ አፍን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ