ትንቢተ ሕዝቅኤል 36
36
የእግዚአብሔር በረከት በእስራኤል ላይ
1“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው። 2ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘለዓለም ጥፋት፥#ዕብ. “የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል” ይላል። ለእኛ ርስት ሆነዋል ብሎአልና፤ 3ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤ 4ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ! የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆዎች፥ ለምድረ በዳዎች፥ ባዶ ለሆኑትና ለፈረሱት፥ በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሣለቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፦ 5ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤ 6ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮችና ለኮረብቶችም፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆዎችም እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንአቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ። 7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ በአሉ አሕዛብ ላይ እኔ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረታቸውን ይሸከማሉ።
8“የእስራኤል ተራሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉና ወይናችሁንና ፍሬያችሁን ይበላሉ። 9እነሆ እኔ ለእናንተ ነኝና፤ ወደ እናንተም እመለከታለሁ፤ እናንተም ትታረሳላችሁ፤ ትዘራላችሁም፤ 10እኔም የእስራኤልን ቤት ሰዎች ሁሉ ሁሉንም አበዛባችኋለሁ፤ በከተሞችም ሰዎች ይኖሩባቸዋል፤ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ። 11ሰውንና እንስሳውንም አበዛላችኋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ያፈሩማል፤#“ይበዛሉ ፤ ያፈሩማል” የሚለው በዕብ. ብቻ። እንደ ጥንታችሁም ሰዎችን አኖርባችኋለሁ፤ ቀድሞም እንደ አደረግሁላችሁ መልካም አደርግላችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 12ሰዎችንም፥ ሕዝቤን እስራኤልን በእናንተ ላይ አበዛለሁ፤ እነርሱም ይወርሱአችኋል፤ ርስትም ትሆኑአቸዋላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም። 13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ፦ ሰው በላተኛ ነሽ፤ በሕዝብሽም መካከል ልጆችሽን አጥፍተሻል ብለዋችኋልና፤ 14ስለዚህ ዳግመኛ ሰው በላተኛ አትሆኝም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን ልጅ አልባ አታደርጊም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 15ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አትሸከሚም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥”#አንዳንድ ዘርዕ “እንግዲህ ወዲህ ሕዝብሽን አታመክኚም” ይላል። ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
የእስራኤል አዲስ ሕይወት
16የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 17“የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በጣዖታቸው አረከሱአት፤ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵሰት ነበረ። 18በምድር ላይ ስለ አፈሰሱት ደም፥ በጣዖቶቻቸውም ስለ አረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው፤ 19ወደ አሕዛብም በተንኋቸው፤ ወደ ሀገሮችም ዘራኋቸው፤ እንደ መንገዳቸውና እንደ በደላቸውም መጠን ፈረድሁባቸው። 20ወደ ገቡባቸውም ወደ አሕዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድራቸው የወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 21እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስለ አረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው።
22“ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! በገባችሁባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ የምሠራ አይደለሁም። 23በአሕዛብም ዘንድ የረከሰውን፥ በመካከላቸው ያረከሳችሁትን ገናና ስሜን እቀድሰዋለሁ፤ በዐይናቸውም ዘንድ በተቀደስሁባችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 24ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ። 25ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ። 26አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። 27መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በትእዛዜም እንድትሄዱ አደርጋችኋለሁ፤ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። 28ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብም ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። 29ከርኵሰታችሁም ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህልንም እጠራዋለሁ፤ አበዛውማለሁ፤ ራብንም አላመጣባችሁም። 30ደግሞም የራብን ስድብ ከአሕዛብ ዘንድ እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን መከር አበዛለሁ። 31ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፤ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። 32ይህን የሠራሁ ስለ እናንተ እንዳይደለ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።
33“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከኀጢአታችሁ ሁሉ በአነጻኋችሁ ጊዜ በከተሞች ሰዎችን አኖራለሁ፤ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ። 34ባድማ የነበረች፥ በመንገደኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነበረች ምድር ትታረሳለች። 35ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ። 36በዙሪያችሁም የቀሩት አሕዛብ፥ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆነውንም እንደ ተከልሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ።
37“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ። 38እንደ ተቀደሱ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 36: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ