ትንቢተ ሕዝቅኤል 35
35
በኤዶምያስ ላይ የተነገረ ትንቢት
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትንቢትም ተናገርበት፤ 3እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘረጋብሃለሁ፤ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ። 4ከተሞችህንም አፈራርሳቸዋለሁ፤ አንተም ባድማ ትሆናለህ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። 5የዘለዓለም ጠላት ሁነሃልና፥ በመከራቸውም ጊዜ በኀይለኛይቱ የኀጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፤ 6ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደልህ ደም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 7የሴይርንም ተራራ ውድማ አደርገዋለሁ፤ ሰውንና እንስሳውንም#ዕብ. “አላፊ አግዳሚውን” ይላል። አጠፋለሁ። 8ተራሮችህንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህና በሸለቆዎችህ፥ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ። 9ለዘለዓለምም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።
10“እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች፥ እነዚህም ሁለቱ ሀገሮች ለእኔ ይሆናሉ፤ እኔም እወርሳቸዋለሁ#ዕብ. “እኛም እንወርሳቸዋለን” ይላል። ብለሃልና፤ 11ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንአትህ መጠን እኔ እፈርድብሃለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ። 12አንተም፦ ፈርሰዋል፤ መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። 13አንተ አፍህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደረግህ#ዕብ. “በአፋችሁም ተመካችሁብኝ ፤ ቃላችሁንም አበዛችሁብኝ” ይላል። እኔ ሰምቼአለሁ።” 14ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። 15የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ! አንተና መላው ኤዶምያስ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 35: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ