የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 35

35
በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤ 3እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ባድ​ማና ውድ​ማም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። 4ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም አፈ​ራ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ባድማ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ። 5የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤ 6ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 7የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ውድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም#ዕብ. “አላፊ አግ​ዳ​ሚ​ውን” ይላል። አጠ​ፋ​ለሁ። 8ተራ​ሮ​ች​ህ​ንም በተ​ገ​ደ​ሉት ሰዎች እሞ​ላ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ች​ህና በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችህ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ች​ህም ሁሉ ላይ በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደ​ሉት ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ። 9ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ህም ሰው የማ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።
10“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነ​ዚህ ሁለቱ ሕዝ​ቦች፥ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ ሀገ​ሮች ለእኔ ይሆ​ናሉ፤ እኔም እወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ#ዕብ. “እኛም እን​ወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለን” ይላል። ብለ​ሃ​ልና፤ 11ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነ​ር​ሱ​ንም ጠል​ተህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኸው እንደ ቅን​አ​ትህ መጠን እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በፈ​ረ​ድ​ሁ​ብ​ህም ጊዜ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ። 12አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ። 13አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ#ዕብ. “በአ​ፋ​ች​ሁም ተመ​ካ​ች​ሁ​ብኝ ፤ ቃላ​ች​ሁ​ንም አበ​ዛ​ች​ሁ​ብኝ” ይላል። እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።” 14ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አን​ተን ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። 15የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ