የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 34

34
የእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ በእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እረ​ኞ​ች​ንም እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​ሰ​ማሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!#“ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​ሰ​ማሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እረ​ኞች ራሳ​ቸ​ውን ያሰ​ማ​ራ​ሉን? እረ​ኞች በጎ​ችን ያሰ​ማሩ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ቸ​ው​ምን? 3ወተ​ቱን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤#ዕብ. “ጮማ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ” ይላል። ጠጕ​ሩ​ንም ትለ​ብ​ሳ​ላ​ችሁ፤ የወ​ፈ​ሩ​ትን ታር​ዳ​ላ​ችሁ፤ በጎ​ቹን ግን አታ​ሰ​ማ​ሩም። 4የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው። 5በጎ​ችም እረ​ኛን በማ​ጣት ተበ​ተኑ፤ ለዱ​ርም አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆኑ። 6በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።
7“ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ 8ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤ 9ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 10ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ረ​ኞች ላይ ነኝ፤ በጎ​ች​ንም ከእ​ጃ​ቸው እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ች​ንም ከማ​ሰ​ማ​ራት አስ​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ እረ​ኞች በጎ​ችን አያ​ሰ​ማ​ሩም፤ በጎ​ች​ንም ከአ​ፋ​ቸው አድ​ና​ለሁ፤ መብ​ልም አይ​ሆ​ኑ​ላ​ቸ​ውም።
11“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎ​ችን እሻ​ለሁ፤ እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም። 12በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን እረኛ ከበ​ጎቹ መካ​ከል የተ​ለ​የ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ፥ እን​ደ​ዚሁ በጎ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። 13ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገ​ራ​ቸ​ውም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጠ​ገብ፥ በም​ድ​ርም ላይ ሰዎች በሚ​ኖ​ሩ​ባት ስፍራ ሁሉ አሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ። 14በመ​ል​ካም ማሰ​ማ​ርያ አስ​ማ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጕረ​ኖ​አ​ቸ​ውም በረ​ዥ​ሞቹ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ይሆ​ናል፤ በዚያ በመ​ል​ካም ጕረኖ ውስጥ ይመ​ሰ​ጋሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ በለ​መ​ለመ ማሰ​ማ​ርያ ይሰ​ማ​ራሉ። 15እኔ ራሴ በጎ​ችን አሰ​ማ​ራ​ለሁ፤ አስ​መ​ስ​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 16የጠ​ፋ​ው​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የደ​ከ​መ​ው​ንም አጸ​ና​ለሁ፤ የወ​ፈ​ረ​ው​ንና#“የወ​ፈ​ረ​ው​ንና” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። የበ​ረ​ታ​ው​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤#ዕብ. “አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል። በፍ​ር​ድም እጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
17ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ን​ተም መን​ጋዬ ሆይ! እነሆ በበ​ግና በበግ መካ​ከል፥ በአ​ውራ በግና በአ​ውራ ፍየ​ልም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ። 18የቀ​ረ​ውን ማሰ​ማ​ር​ያ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ የረ​ገ​ጣ​ች​ሁት፥ የተ​ሰ​ማ​ራ​ች​ሁ​በት መል​ካሙ መሰ​ማ​ርያ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን? የቀ​ረ​ው​ንስ ውኃ በእ​ግ​ራ​ችሁ ያደ​ፈ​ረ​ሳ​ች​ሁት፥ ጥሩ​ውን ውኃ መጠ​ጣ​ታ​ችሁ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን? 19በጎ​ችም በእ​ግ​ራ​ችሁ በረ​ገ​ጣ​ች​ሁት ይሰ​ማ​ራሉ፤ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ያደ​ፈ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ትን ይጠ​ጣሉ።
20“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እነሆ እኔ በወ​ፈ​ሩት በጎ​ችና በከ​ሱት በጎች መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ። 21እስ​ክ​ት​በ​ት​ኑ​አ​ቸው ድረስ በእ​ን​ቢ​ያና በት​ከሻ ስለ​ም​ት​ገ​ፉ​አ​ቸው፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ን​ዳ​ችሁ ስለ​ም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው፥ 22ስለ​ዚህ መን​ጋ​ዬን አድ​ና​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ በበ​ግና በበግ መካ​ከ​ልም እፈ​ር​ዳ​ለሁ። 23በላ​ያ​ቸ​ውም አንድ እረኛ አቆ​ማ​ለሁ፤ እር​ሱም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል፤ እር​ሱም ባሪ​ያዬ ዳዊት ነው፤ እረ​ኛም ይሆ​ና​ቸ​ዋል። 24እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባሪ​ያዬ ዳዊ​ትም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።
25“የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ። 26እነ​ር​ሱ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታዬ ዙሪያ ያሉ​ትን ስፍ​ራ​ዎች#“ያሉ​ትን ስፍ​ራ​ዎች” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዝና​ቡ​ንም በጊ​ዜው#“በጊ​ዜው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ የበ​ረ​ከ​ትም ዝናብ ይሆ​ናል። 27የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 28እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም። 29የሰ​ላ​ምን ተክል አቆ​ም​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከራብ የተ​ነሣ በም​ድር አያ​ል​ቁም፤ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ሸ​ከ​ሙም። 30እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሕዝቤ እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 31እና​ን​ተም በጎች፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያዬ በጎች፥ ሰዎች#“ሰዎች” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ናችሁ፤ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ