የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 39

39
የጎግ መሸ​ነፍ
1“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትን​ቢ​ትን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ 2እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እመ​ራ​ሃ​ለሁ፤ ከሰ​ሜ​ንም ዳርቻ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ። 3ከግራ እጅ​ህም ቀስ​ት​ህን አስ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ከቀኝ እጅ​ህም ፍላ​ጾ​ች​ህን አስ​ረ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ፤#“አስ​ረ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ እጥ​ል​ሃ​ለሁ። 4አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ#“ለሚ​ና​ጠቁ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 5አንተ በሜዳ ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 6በማ​ጎ​ግም ላይ፥ በሰ​ላ​ምም በደ​ሴ​ቶች በሚ​ቀ​መጡ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 7ቅዱ​ሱም ስሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይታ​ወ​ቃል፤ ቅዱ​ሱ​ንም ስሜን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ረ​ክ​ስም፤ አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 8እነሆ ይመ​ጣል፤ እን​ደ​ሚ​ሆ​ንም ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያል​ሁት ቀን ይህ ነው። 9በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ከተ​ሞች የሚ​ኖሩ ይወ​ጣሉ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ፤ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ንና ጋሻን፥ ቀስ​ት​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ችን፥ የእጅ በት​ሮ​ች​ንና ጦር​ንም ያቃ​ጥ​ላሉ፤ ሰባት ዓመት በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል። 10እን​ጨ​ትን ከሜዳ አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ከዱ​ርም አይ​ቈ​ር​ጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣ​ሪ​ያን በእ​ሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ የገ​ፈ​ፉ​አ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፋሉ፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​አ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
የጎግ መቃ​ብር
11“በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በባ​ሕር ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ል​ፉ​በ​ትን ሸለቆ፥ የመ​ቃ​ብ​ርን ስፍራ ለጎግ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ል​ፉ​ት​ንም ይከ​ለ​ክ​ላል፤ በዚ​ያም ጎግ​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ይቀ​ብ​ራሉ፤ የሸ​ለ​ቆ​ው​ንም ስም የጎግ መቃ​ብር ብለው ይጠ​ሩ​ታል። 12ምድ​ር​ንም ያነ​ደዱ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰባት ወር መቃ​ብር እየ​ቈ​ፈሩ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤ 13የም​ድ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤ እኔም በም​መ​ሰ​ገ​ን​በት ቀን ለክ​ብር ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 14ምድ​ር​ንም ለማ​ጽ​ዳት በም​ድሩ ላይ ወድ​ቀው የቀ​ሩ​ትን የሚ​ቀ​ብሩ፥ ዘወ​ትር በም​ድሩ ላይ የሚ​ዞ​ሩ​ትን ሰዎች ይቀ​ጥ​ራሉ፤ ከሰ​ባት ወርም በኋላ ይመ​ረ​ም​ራሉ። 15በም​ድ​ርም የሚ​ዞ​ሩት ያል​ፋሉ፤ የሰ​ው​ንም አጥ​ንት ቢያዩ፥ ቀባ​ሪ​ዎች በጎግ መቃ​ብር ሸለቆ እስ​ኪ​ቀ​ብ​ሩት ድረስ ምል​ክት ያኖ​ሩ​በ​ታል። 16ደግ​ሞም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም የመ​ቃ​ብር ቦታ ይባ​ላል። እን​ዲሁ ምድ​ሪ​ቱን ያጸ​ዳሉ።
17“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሚ​በ​ርሩ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ኑ፤ ተከ​ማቹ፤ ሥጋ​ንም ትበሉ ዘንድ፥ ደም​ንም ትጠጡ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ወደ​ማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት፥ እር​ሱም ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት፥ ከየ​ሰ​ፍ​ራው ሁሉ ተሰ​ብ​ሰቡ። 18የኀ​ያ​ላ​ኑን ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አለ​ቆች፥ የአ​ውራ ፍየ​ሎ​ች​ንና የአ​ውራ በጎ​ችን፥ የወ​ይ​ፈ​ኖ​ች​ንና፥ የባ​ሳ​ንን#“የባ​ሳ​ንን” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ፍሪ​ዳ​ዎች ሁሉ፥ ደም ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ። 19እኔም ከማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት እስ​ክ​ት​ጠ​ግቡ ድረስ ጮማን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እስ​ክ​ት​ሰ​ክ​ሩም ድረስ ደምን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ። 20ከማ​ዕ​ዴም ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከፈ​ረ​ሰ​ኞች፥ ከኀ​ያ​ላ​ንና ከሰ​ል​ፈ​ኞች ሁሉ ሥጋን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
የእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ገና መቋ​ቋም
21“ክብ​ሬ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ፍር​ዴን፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያኖ​ር​ኋ​ትን እጄን ያያሉ። 22ከዚች ቀን ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 23አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት እንደ ተማ​ረኩ ያው​ቃሉ፤ ስለ ከዱኝ እኔም ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ ስለ መለ​ስሁ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሰ​ይፍ ወደቁ። 24እንደ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም እንደ መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም መጠን አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ መለ​ስሁ።
25“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሁን የያ​ዕ​ቆ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ እራ​ራ​ለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀ​ና​ለሁ። 26በም​ድ​ራ​ቸው ተዘ​ል​ለው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይሸ​ከ​ማሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም። 27ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ በመ​ለ​ስ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሀገ​ሮች በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ፊት በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ፥ 28እኔም ወደ አሕ​ዛብ አስ​ማ​ር​ኬ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ቸ​ውም ሰብ​ስ​ቤ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ በዚ​ያም ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አላ​ስ​ቀ​ርም፤ 29ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​መ​ል​ስም፤ መዓ​ቴን#ዕብ. “መን​ፈ​ሴን” ይላል። በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ላይ አፍ​ስ​ሻ​ለ​ሁና፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ