ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 15

15
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ቃል ኪዳ​ንን እንደ ሰጠው
1ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።” 2አብ​ራ​ምም፥ “አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳል​ወ​ልድ እሞ​ታ​ለሁ፤ የቤ​ቴም ወራሽ ከዘ​መዴ ወገን የሚ​ሆን የደ​ማ​ስቆ ሰው የማ​ሴቅ ልጅ ይህ ኢያ​ው​ብር#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ኤሊ​ዔ​ዜር” ይላል። ነው” አለ። 3አብ​ራ​ምም፥ “ለእኔ ዘር አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ የዘ​መዴ ልጅ እርሱ ይወ​ር​ሰ​ኛል” አለ። 4ያን ጊዜም የአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አብ​ራም እን​ዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይ​ወ​ር​ስ​ህም፤ ነገር ግን ከአ​ብ​ራ​ክህ የሚ​ወ​ጣው እርሱ ይወ​ር​ስ​ሃል።” 5ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው። 6አብ​ራ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት። 7“ይህ​ችን ምድር ትወ​ር​ሳት ዘንድ እን​ድ​ሰ​ጥህ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ” አለው። 8“አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እን​ደ​ም​ወ​ር​ሳት በምን አው​ቃ​ለሁ?” አለው። 9እር​ሱም አለው፥ “የሦ​ስት ዓመት ላም፥ የሦ​ስት ዓመት ፍየ​ልም፥ የሦ​ስት ዓመት በግም፥ ዋኖ​ስም፥ ርግ​ብም አምጣ፤ እኒ​ህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው።”#“ይህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፥ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። 10እን​ዲ​ሁም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወሰ​ደ​ለት፤ በየ​ሁ​ለ​ትም ከፈ​ላ​ቸው፤ የተ​ከ​ፈ​ሉ​ት​ንም በየ​ወ​ገኑ ትይዩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አል​ቈ​ረ​ጣ​ቸ​ውም። 11አሞ​ራ​ዎ​ችም በተ​ቈ​ረ​ጠው ሥጋ​ቸው ላይ ወረዱ፤ አብ​ራ​ምም በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተቀ​ምጦ አባ​ረ​ራ​ቸው።
12ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ በአ​ብ​ራም ድን​ጋጤ#ዕብ. “ከባድ ዕን​ቅ​ልፍ” ይላል። መጣ​በት፤ እነ​ሆም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣ​በት፤ 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዘርህ ለእ​ነ​ርሱ ባል​ሆ​ነች ምድር ስደ​ተ​ኞች እን​ዲ​ሆኑ በእ​ር​ግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመ​ታ​ትም ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ያሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ዋ​ልም። 14ደግ​ሞም የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውን እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። ከዚ​ህም በኋላ ከብዙ ገን​ዘብ ጋር ወደ​ዚህ ይወ​ጣሉ። 15አንተ ግን ወደ አባ​ቶ​ችህ በሰ​ላም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ል​ናም ትቀ​በ​ራ​ለህ። 16በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።” 17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ። 18በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ 19ቀኔ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ዜ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ሚ​ሎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ 20ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ፈራ​ዮ​ና​ው​ያ​ን​ንም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ራፋ​ይ​ምን” ይላል። 21አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን” የሚል አለ። ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል