ኦሪት ዘፍጥረት 39
39
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤት
1ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የመጋቢዎቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ከአወረዱት ከይስማኤላውያን እጅ ገዛው። 2እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ተሾመ። 3ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ። 4ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፤ እርሱንም ደስ ያሰኘው ነበር፤ በቤቱም ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። 5እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት በዮሴፍ ምክንያት ባረከው። የእግዚአብሔርም በረከት በቤቱም፥ በእርሻውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ። 6ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ በእጁ አስረከበው፤ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። ዮሴፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተዋበ ነበር።
7ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይንዋን ጣለችበት፤ “ከእኔም ጋር ተኛ” አለችው። 8እርሱም እንቢ አለ፤ ለጌታውም ሚስት እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስረክቦኛል፤ በቤቱ ያለውንም ምንም የሚያውቀው የለም፤ 9በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?” 10ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም። 11በአንዲትም ቀን እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራውን እንዲሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አልነበረም። 12ልብሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ። 13እንዲህም ሆነ፤ ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ በአየች ጊዜ፥ 14የቤቷን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብራዊ ባርያ በእኛ እንዲሣለቅ አመጣብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤ 15ድምፄንም ከፍ አድርጌ እንደ ጮኽሁ ቢሰማ፥ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።” 16ጌታው ወደ ቤቱ እስኪገባ ድረስም ልብሱን ከእርስዋ ዘንድ አኖረች። 17ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው፥ “ያመጣኸው ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ፤ ከአንቺም ጋር ልተኛ አለኝ። 18እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።”
19ጌታውም፥ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ። 20ዮሴፍንም ወሰደው፤ የንጉሡ እስረኞች ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። 21እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፤ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው። 22የግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ። 23የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 39: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ