ኦሪት ዘፍጥረት 40
40
ዮሴፍ የእስረኞችን ሕልም እንደ ተረጐመ
1ከዚህ ነገር በኋላም እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፅ ንጉሥን በደሉ። 2ፈርዖንም በሁለቱ ሹሞች በጠጅ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ አበዛዎቹ አለቃ ላይ ተቈጣ፤ 3በእስር ቤት ውስጥም ዮሴፍ ታስሮ በነበረበት የግዞት ስፍራ አጋዛቸው። 4የእስር ቤቱ ዘበኞች አለቃም ለዮሴፍ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ያገለግላቸው ነበር፤ በግዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀመጡ። 5ሁለቱም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለሙ። በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ሁለቱም እየራሳቸው ሕልምን አለሙ። 6ዮሴፍም ማልዶ ወደ እነርሱ ገባ፤ እነሆም፥ አዝነው አያቸው። 7በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖን ሹሞች እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፥ “እናንት ዛሬ ስለምን አዝናችኋል?” 8እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
9የጠጅ አሳላፊዎች አለቃም ለዮሴፍ ሕልሙን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “በሕልሜ የወይን ሐረግ በፊቴ ሆና አየሁ፥ 10በሐረጉም ሦስት ቅርንጫፎች ወጡ፤ እርስዋም ቅጠልና አበባ አወጣች፤ ዘለላም አንጠለጠለች፤ የዘለላዋም ፍሬ በሰለ፤ 11የፈርዖንም ጽዋ በእጄ ነበር፤ ፍሬውንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ጨመቅሁት፤ ጽዋዉንም ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” 12ዮሴፍም አለው፥ “የሕልምህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስት ቅርንጫፎች ሦስት ቀኖች ናቸው። 13እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈርዖን ሹመትህን ያስባል፤ ወደ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃነትህም ይመልስሃል፤ ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታደርገው እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሹመትህም የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ። 14ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤ 15ሌቦች በስውር ከዕብራውያን ሀገር ሰርቀውኛልና፤ በዚህም ደግሞ ምንም ያደረግሁት ሳይኖር በግዞት ቤት አኑረውኛልና።”
16የእንጀራ አበዛዎቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጐመለት በአየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ 17በላይኛውም መሶብ ፈርዖን የሚበላው ጋጋሪው በያይነቱ የሠራው መብል ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር።” 18ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው፥ “የሕልምህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ይቈርጥሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ የሰማይ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።” 20እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ። 21የጠጅ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ ሹመቱ መለሰው፤ ጽዋውንም በፈርዖን እጅ ሰጠ፤ 22የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በዕንጨት ላይ ሰቀለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው። 23የጠጅ አሳላፊዎች አለቃ ግን ዮሴፍን አላሰበውም፤ ረሳው እንጂ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 40: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ