የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 41

41
ዮሴፍ የፈ​ር​ዖ​ንን ሕልም እንደ ተረ​ጐመ
1ከሁ​ለት ዓመት በኋ​ላም ፈር​ዖን ሕል​ምን አየ፤ እነ​ሆም፥ በወ​ንዙ ዳር ቆሞ ነበር። 2እነ​ሆም፥ መል​ካ​ቸው ያማረ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈረ ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በወ​ን​ዙም ዳር በመ​ስኩ ይሰ​ማሩ ነበር። 3ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም ላሞች አጠ​ገብ በወ​ንዙ ዳር ተሰ​ማ​ር​ተው ነበር። 4መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ እነ​ዚያ ሰባት ላሞች መል​ካ​ቸው ያማ​ረ​ውን፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈ​ረ​ውን ሰባ​ቱን ላሞች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ 5ደግ​ሞም ተኛ፤ ሁለ​ተኛ ሕል​ም​ንም አየ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ንድ አገዳ ላይ የነ​በሩ፥ ያማ​ሩና ምርጥ የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤ 6እነ​ሆም፥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤ 7እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱና ነፋስ የመ​ታ​ቸው እሸ​ቶች ሰባ​ቱን ያማ​ሩና የጐ​መሩ እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም ሕልም ነበር። 8በነ​ጋም ጊዜ መን​ፈሱ ታወ​ከ​ች​በት፤ የግ​ብፅ ሕልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ች​ንና ጠቢ​ባ​ንን ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሕል​ሙን ነገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ ለፈ​ር​ዖን ሕል​ሙን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ለት አል​ተ​ገ​ኘም።
9የዚ​ያን ጊዜ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለቃ እን​ዲህ ብሎ ለፈ​ር​ዖን ተና​ገረ፥ “እኔ ኀጢ​አ​ቴን ዛሬ አስ​ባ​ለሁ፤ 10ፈር​ዖን በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ላይ ተቈጣ፤ እኔ​ንም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረን፤ 11እኛም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለ​ምን፤ እኔና እርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን እንደ ሕል​ማ​ችን ትር​ጓሜ አለ​ምን። 12በዚ​ያም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች#ዕብ. “የዘብ ጥበቃ አለቃ” ይላል። አለቃ አገ​ል​ጋይ የሆነ አንድ ዕብ​ራዊ ጐል​ማሳ ከእኛ ጋር ነበር፤ ለእ​ር​ሱም ነገ​ር​ነው፤ ሕል​ማ​ች​ን​ንም ተረ​ጐ​መ​ልን። 13እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እንደ ተረ​ጐ​መ​ልን እን​ደ​ዚ​ያው ሆነ፤ እኔ ወደ ሹመቴ ተመ​ለ​ስሁ፤ እር​ሱም ተሰ​ቀለ።”
14ፈር​ዖ​ንም ልኮ ዮሴ​ፍን አስ​ጠ​ራው፤ ከግ​ዞት ቤትም አወ​ጡት፤ ራሱ​ንም ላጩት፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጡ፤ ወደ ፈር​ዖ​ንም ገባ። 15ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ሕል​ምን አየሁ፤ የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ል​ኝም አጣሁ፤ ሕል​ምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረ​ጐ​ም​ህም ስለ አንተ ሰማሁ።” 16ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት። 17ፈር​ዖ​ንም ለዮ​ሴፍ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ በሕ​ልሜ በወ​ንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ 18እነ​ሆም፥ ሥጋ​ቸው የወ​ፈረ፥ መል​ካ​ቸ​ውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፤ በወ​ንዙ ዳር በመ​ስ​ኩም ይሰ​ማሩ ነበር፤ 19ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ የደ​ከሙ፥ መል​ካ​ቸ​ውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ሁሉ እንደ እነ​ርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላ​የ​ሁም፤ 20እነ​ዚያ የከ​ሱ​ትና መልከ ክፉ​ዎቹ ላሞች እነ​ዚ​ያን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ያማ​ሩና የወ​ፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡ​አ​ቸው፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ተዋጡ፤ 21በሆ​ዳ​ቸ​ውም ውስጥ የገባ እን​ደ​ሌለ ሆኑ፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ጀ​መ​ሪያ እንደ ነበ​ረው የከፋ ነበረ፤ ነቃ​ሁም። ዳግ​መ​ኛም ተኛሁ፤ 22በሕ​ል​ሜም እነሆ፥ የጐ​መ​ሩና መል​ካም የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ከአ​ንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ፤ 23ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሌሎች ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤ 24እነ​ዚያ የሰ​ለ​ቱ​ትና በነ​ፋስ የተ​መ​ቱት እሸ​ቶች እነ​ዚ​ያን ያማ​ሩ​ት​ንና የጐ​መ​ሩ​ትን ሰባ​ቱን እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ለሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችም ሕል​ሜን ነገ​ርሁ፤ የተ​ረ​ጐ​መ​ል​ኝም የለም።”
25ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል። 26እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው። 27ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው። 28ለፈ​ር​ዖን የነ​ገ​ር​ሁት ነገር ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​የው። 29እነሆ፥ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ይመ​ጣሉ፤ 30ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ 31በኋ​ላም ከሚ​ሆ​ነው ከዚያ ራብ የተ​ነሣ በም​ድር የሆ​ነው ጥጋብ አይ​ታ​ወ​ቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆ​ና​ልና። 32ሕል​ሙም ለፈ​ር​ዖን ደጋ​ግሞ መታ​የቱ ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ስለ​ሆነ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈጥኖ ያደ​ር​ገ​ዋል። 33አሁ​ንም ብል​ህና ዐዋቂ ሰውን ለአ​ንተ ፈልግ፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ሹመው። 34ፈር​ዖን በግ​ብፅ ምድር ላይ ሹሞ​ችን ይሹም፤ በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ከአ​ም​ስት እጅ አን​ደ​ኛ​ውን ይው​ሰድ። 35የሚ​መ​ጡ​ትን የመ​ል​ካ​ሞ​ቹን ሰባት ዓመ​ታት እህ​ላ​ቸ​ውን ያከ​ማቹ፤ ስን​ዴ​ው​ንም ከፈ​ር​ዖን እጅ በታች ያኑሩ፤ እህ​ሎ​ችም በከ​ተ​ሞች ይጠ​በቁ። 36በግ​ብፅ ምድር ስለ​ሚ​ሆ​ነው ስለ ሰባቱ ዓመ​ታት ራብ እህሉ ለሀ​ገሩ ሁሉ ተጠ​ብቆ ይኑር፥ ምድ​ሪ​ቱም በራብ አት​ጠ​ፋም።”
ዮሴፍ በግ​ብፅ አዛዥ እንደ ሆነ
37ነገ​ሩም ፈር​ዖ​ን​ንና ሰዎ​ቹን ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው፤ 38ፈር​ዖ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ያለ​በ​ትን እን​ደ​ዚህ ያለ ሰውን እና​ገ​ኛ​ለን?” 39ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና ከአ​ንተ ይልቅ ብል​ህና ዐዋቂ ሰው የለም። 40አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።” 41ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን፥ “በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾም​ሁህ” አለው። 42ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤ 43የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤#ዕብ. “አዋጅ ነጋ​ሪም ስገዱ እያለ በፊቱ ይጮኽ ነበር” ይላል። በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው። 44ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እኔ ራሴ ፈር​ዖን ነኝ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁን#ዕብ. “እጁ​ንም እግ​ሩ​ንም” ይላል። አያ​ንሣ።” 45ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።
46ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ። 47በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ግብፅ ያስ​ገ​ኘ​ችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ። 48በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ያለ​ውን የሰ​ባ​ቱን የጥ​ጋብ ዓመ​ታት እህል ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እህ​ል​ንም በከ​ተ​ሞቹ አደ​ለበ፤ በየ​ከ​ተ​ማ​ይ​ቱም ዙሪያ ያለ​ውን የእ​ር​ሻ​ውን እህል ሁሉ በዚ​ያው ከተተ። 49ዮሴ​ፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስን​ዴን አከ​ማቸ፤ መስ​ፈር እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ፤ ሊሰ​ፈር አል​ተ​ቻ​ለ​ምና።
50ለዮ​ሴ​ፍም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይ​መጣ ተወ​ለ​ዱ​ለት። 51ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤” 52የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”
53በግ​ብፅ ምድር የነ​በ​ረ​ውም ሰባቱ የጥ​ጋብ ዓመት አለፈ፤ 54ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። 55የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው። 56በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።#ዕብ. ምዕ. 41 ቍ. 56 መጨ​ረሻ “ራብም በግ​ብፅ ምድር ጸንቶ ነበር” የሚል ይጨ​ም​ራል። 57ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ