የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 42

42
የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች ወደ ግብፅ እንደ ሄዱ
1ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ የሚ​ሸ​መት እህል እን​ዳለ ሰማ፤ ልጆ​ቹ​ንም፥ “ለምን ትተ​ክ​ዛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። 2እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግ​ብፅ እን​ዳለ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ወደ​ዚያ ውረዱ፤ እን​ድ​ን​ድ​ንና በራብ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ከዚያ ሸም​ቱ​ልን።” 3የዮ​ሴ​ፍም ዐሥሩ ወን​ድ​ሞቹ እህ​ልን ከግ​ብፅ ይሸ​ምቱ ዘንድ ወረዱ፤ 4የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድም ብን​ያ​ምን ግን ያዕ​ቆብ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር አል​ሰ​ደ​ደ​ውም፥ “ምና​ል​ባት ክፉ እን​ዳ​ያ​ገ​ኘው” ብሎ​አ​ልና። 5የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና። 6ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት። 7ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት። 8ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ዐወ​ቃ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ዮሴ​ፍም አይ​ቶት የነ​በ​ረ​ውን ሕልም ዐሰበ። 9እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ፤ የሀ​ገ​ሩን ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።” 10እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ስንዴ ሊገዙ መጥ​ተ​ዋል፤ 11እኛ ሁላ​ችን የአ​ንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰ​ላም ሰዎች ነን፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ሉም።” 12እር​ሱም አላ​ቸው፥ “አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።” 13እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ በከ​ነ​ዓን ምድር የም​ን​ኖር ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤#ዕብ. “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖር የአ​ንድ ሰው ልጆች ነን” ይላል። ታና​ሹም እነሆ ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር ነው፤ ሌላ​ውም ሞቶ​አል።” 14ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ብዬ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​አ​ች​ሁም ይህ ነው፤ በዚህ ትታ​ወ​ቃ​ላ​ችሁ፤ 15ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከአ​ላ​መ​ጣ​ችሁ በቀር ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ከዚህ አት​ወ​ጡም። 16ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ያመጣ ዘንድ ከእ​ና​ንተ አን​ዱን ላኩ፤ እና​ንተ ግን እው​ነ​ትን የም​ት​ና​ገሩ ከሆነ ወይም ከአ​ል​ሆነ ነገ​ራ​ችሁ እስ​ኪ​ታ​ወቅ ድረስ ከዚህ ተቀ​መጡ፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ሰላ​ዮች ናችሁ።” 17ሦስት ቀን ያህ​ልም በግ​ዞት ቤት ጨመ​ራ​ቸው።
18በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና። 19እና​ንተ ሰላ​ማ​ው​ያን ከሆ​ና​ችሁ ከእ​ና​ንተ አንዱ ወን​ድ​ማ​ችሁ በግ​ዞት ቤት ይታ​ሰር፤ እና​ንተ ግን ሂዱ፤ የሸ​መ​ታ​ች​ሁ​ትን እህ​ልም ውሰዱ፤#ዕብ. “እህ​ሉ​ንም ለተ​ራ​ቡት ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ችሁ ውሰዱ” ይላል። 20ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገ​ራ​ችሁ የታ​መነ ይሆ​ና​ልና፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ግን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ። 21እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።” 22ሮቤ​ልም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብላ​ቴ​ና​ውን አት​በ​ድሉ ብዬ​አ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፤ ስለ​ዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈ​ላ​ለ​ጋ​ች​ኋል።” 23እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ነገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ሰ​ማ​ባ​ቸው አላ​ወ​ቁም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ተ​ር​ጓሚ ነበ​ርና። 24ዮሴ​ፍም ከእ​ነ​ርሱ ዘወር ብሎ አለ​ቀሰ፤ ደግ​ሞም ወደ እነ​ርሱ ተመ​ልሶ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ስም​ዖ​ን​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለይቶ ወስዶ በፊ​ታ​ቸው አሰ​ረው። 25ዮሴ​ፍም ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን እህል ይሞ​ሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየ​ራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ይመ​ል​ሱት ዘንድ፥ ደግ​ሞም የመ​ን​ገድ ስንቅ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ አዘዘ። እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ።
የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች ወደ ከነ​ዓን መመ​ለ​ሳ​ቸው
26እነ​ር​ሱም እህ​ሉን በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚ​ያም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ። 27ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ በአ​ደ​ሩ​በት ስፍራ ለአ​ህ​ዮቹ ገፈ​ራን ይሰጥ ዘንድ ዓይ​በ​ቱን ፈታ፤ ብሩ​ንም በዓ​ይ​በቱ አፍ ተቋ​ጥሮ አገኘ። 28ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ “ብሬ ተመ​ለ​ሰ​ች​ልኝ፤ እር​ስ​ዋም በዓ​ይ​በቴ አፍ እነ​ኋት” አላ​ቸው። ልባ​ቸ​ውም ደነ​ገጠ፤ እየ​ታ​ወ​ኩም እርስ በር​ሳ​ቸው ተባ​ባሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” 29ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ያዕ​ቆብ ወደ ከነ​ዓን ምድር መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ እን​ዲህ ብለው አወሩ፦ 30“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።” 31እኛም እን​ዲህ አል​ነው፥ “ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ነን እንጂ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ለ​ንም፤ 32እኛ የአ​ባ​ታ​ችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ አንዱ ሞቶ​አል፤ ታና​ሹም በከ​ነ​ዓን ምድር ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር አለ። 33የሀ​ገ​ሩም ጌታ ያ ሰው እን​ዲህ አለን፦ ‘ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ከሆ​ና​ችሁ በዚህ ዐው​ቃ​ለሁ፤ አን​ደ​ኛ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእኔ ጋር ተዉት፤ ለቤ​ታ​ች​ሁም የሸ​መ​ታ​ች​ሁ​ትን እህል ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ 34ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”
35እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእ​ነ​ርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ብራ​ቸ​ውን በዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ተቋ​ጥሮ አገ​ኙት፤ እነ​ር​ሱም አባ​ታ​ቸ​ውም የተ​ቋ​ጠረ ብራ​ቸ​ውን አይ​ተው ፈሩ። 36አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።” 37ሮቤ​ልም አባ​ቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላ​መ​ጣ​ሁት እን​ደ​ሆነ ሁለ​ቱን ልጆ​ችን ግደል፤ ልጅ​ህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።” 38እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ