የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 43

43
የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች ከብ​ን​ያም ጋር ወደ ግብፅ እንደ ሄዱ
1ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና። 2ከግ​ብ​ፅም ያመ​ጡ​ትን እህል በል​ተው ከፈ​ጸሙ በኋላ አባ​ታ​ቸው፥ “እን​ደ​ገና ሂዱ፤ ጥቂት እህል ሸም​ታ​ችሁ አም​ጡ​ልን” አላ​ቸው። 3ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል። 4ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ብት​ል​ከው እን​ወ​ር​ዳ​ለን፤ እህ​ልም እን​ሸ​ም​ት​ል​ሃ​ልን፤ 5ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ባት​ል​ከው ግን አን​ሄ​ድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ካላ​መ​ጣ​ችሁ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ​ና​ልና።” 6እስ​ራ​ኤ​ልም አላ​ቸው፥ “በእኔ ላይ ያደ​ረ​ጋ​ች​ኋት ይህች ክፋት ምን​ድን ናት? በዚ​ያ​ውስ ላይ ሌላ ወን​ድም አለን ብላ​ችሁ ለምን ነገ​ራ​ች​ሁት?” 7እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትው​ል​ዳ​ችን ፈጽሞ ጠየ​ቀን፤ እን​ዲ​ህም አለን፦ ‘ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችሁ ገና በሕ​ይ​ወት ነው? ወን​ድ​ምስ አላ​ች​ሁን?’ እኛም እን​ደ​ዚሁ እንደ ጠየ​ቀን መለ​ስ​ን​ለት፤ በውኑ፦ ‘ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አምጡ’ እን​ዲ​ለን እና​ውቅ ነበ​ርን?” 8ይሁ​ዳም አባ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ልን አለው፥ “እኛና አንተ ልጆ​ቻ​ች​ንም ደግሞ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ብላ​ቴ​ና​ውን ከእኔ ጋር ላከው፤ እኛም ተነ​ሥ​ተን እን​ሄ​ዳ​ለን። 9እኔ እዋ​ሳ​ለሁ፤ ከእጄ ትሻ​ዋ​ለህ፤ ወደ አንተ ባላ​መ​ጣው፥ በፊ​ት​ህም ባላ​ቆ​መው፥ በዘ​መ​ናት ሁሉ አን​ተን የበ​ደ​ል​ሁህ ልሁን። 10ባን​ዘ​ገ​ይስ ኖሮ አሁን ሁለ​ተኛ ጊዜ በተ​መ​ለ​ስን ነበር።” 11አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ። 12ብሩን በአ​ጠ​ፌታ አድ​ር​ጋ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ውሰዱ፤ በዓ​ይ​በ​ታ​ች​ሁም አፍ የተ​መ​ለ​ሰ​ውን ብር መል​ሳ​ችሁ ውሰዱ፤ ምና​ል​ባት ባለ​ማ​ወቅ ይሆ​ናል። 13ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር ውሰዱ፤ ተነ​ሥ​ታ​ች​ሁም ወደ​ዚያ ሰው ውረዱ። 14አም​ላ​ኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገ​ስን ይስ​ጣ​ችሁ፤ ያን ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንና ብን​ያ​ም​ንም ይመ​ል​ስ​ላ​ችሁ፤ እኔም ልጆ​ችን እን​ዳ​ጣሁ አጣሁ።” 15ሰዎ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ያችን እጅ መን​ሻና ብራ​ቸ​ውን በእ​ጥፍ፥ ብን​ያ​ም​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮ​ሴ​ፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም።
16ዮሴ​ፍም ብን​ያ​ምን ከእ​ነ​ርሱ ጋር በአ​የው ጊዜ የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እር​ድም እረድ፤ አዘ​ጋ​ጅም፤ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበ​ላ​ሉና።” 17ያም ሰው ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ ሰዎ​ቹ​ንም ወደ ዮሴፍ ቤት አስ​ገባ። 18እነ​ዚ​ያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ቀድሞ ስለ ተመ​ለ​ሰው ብር ሊተ​ነ​ኰ​ሉ​ብን፥ ሊወ​ድ​ቁ​ብ​ንም፥ እኛ​ንም በባ​ር​ነት ሊገ​ዙን፥ አህ​ዮ​ቻ​ች​ን​ንም ሊወ​ስዱ ወደ​ዚህ አስ​ገ​ቡን።” 19ወደ ዮሴፍ ቤት አዛ​ዥም ቀረቡ፤ በቤ​ቱም ደጅ ተና​ገ​ሩት፤ 20እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ እን​ማ​ል​ድ​ሃ​ለን፤ ቀድሞ እህ​ልን ልን​ሸ​ምት ወር​ደን ነበር፤ 21እን​ዲ​ህም ሆነ፥ ወደ​ም​ና​ድ​ር​በ​ትም ስፍራ በደ​ረ​ስን ጊዜ ዓይ​በ​ታ​ች​ንን ከፈ​ትን፤ እነ​ሆም፥ የየ​አ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ብር በየ​ዓ​ይ​በቱ አፍ ነበር፤ አሁ​ንም ብራ​ች​ንን በእ​ጃ​ችን እንደ ሚዛኑ መለ​ስ​ነው። 22እህል እን​ሸ​ም​ት​በት ዘንድ ሌላም ብር በእ​ጃ​ችን አመ​ጣን፤ ብራ​ች​ን​ንም በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ማን እንደ ጨመ​ረው አና​ው​ቅም።” 23እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ አት​ፍሩ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ የተ​ሰ​ወረ ገን​ዘብ ሰጣ​ችሁ፤ ብራ​ች​ሁ​ንስ መዝኜ ተቀ​ብ​ያ​ለሁ።” 24ስም​ዖ​ን​ንም ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው። እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ሊታ​ጠቡ ውኃ አመ​ጣ​ላ​ቸው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ገፈራ ሰጣ​ቸው።#ዕብ. ምዕ. 43 በቍ. 24 መጀ​መ​ሪያ “ሰው​የ​ውም እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው” የሚል ይጨ​ም​ራል። 25ዮሴ​ፍም በእ​ኩለ ቀን እስ​ኪ​ገባ ድረስ እነ​ርሱ እጅ መን​ሻ​ቸ​ውን አዘ​ጋጁ፤ ከዚያ ምሳ እን​ደ​ሚ​በሉ ሰም​ተ​ዋ​ልና። 26ዮሴ​ፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእ​ጃ​ቸው ያለ​ውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው ሰገ​ዱ​ለት። 27እር​ሱም ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ውን ጠየ​ቃ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ሽማ​ግሌ አባ​ታ​ችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕ​ይ​ወት አለን?” 28እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ባሪ​ያህ ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችን ደኅና ነው፤ ገና በሕ​ይ​ወት አለ።” ዮሴ​ፍም አለ፥ “ሰው​የው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከው ነው።” ራሳ​ቸ​ው​ንም ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገ​ዱ​ለት። 29ዮሴ​ፍም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ የእ​ና​ቱን ልጅ ወን​ድሙ ብን​ያ​ምን አየው፤ እር​ሱም አለ፥ “ወደ አንተ እና​መ​ጣ​ዋ​ለን ብላ​ችሁ የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ችሁ ይህ ነውን?” እነ​ር​ሱም፥ “አዎን” አሉት። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይበ​ልህ።” 30ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ። 31ፊቱ​ንም ታጥቦ ተጽ​ና​ን​ቶም ወጣ። “እን​ጀራ አቅ​ር​ቡ​ልን” አለ። 32ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና። 33በፊ​ቱም በኵሩ እንደ ታላ​ቅ​ነቱ፥ ታና​ሹም እንደ ታና​ሽ​ነቱ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ደ​ነቅ ተያዩ። 34በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ