የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 44

44
የጠ​ፋው ጽዋዕ
1ዮሴ​ፍም የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የእ​ነ​ዚህ ሰዎች ዓይ​በ​ቶ​ቻ​ቸው መያዝ የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል እህል ሙላ​ላ​ቸው፤ የሁ​ሉ​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው አፍ ጨም​ረው፤ 2በታ​ና​ሹም ዓይ​በት አፍ የብ​ሩን ጽዋ​ዬ​ንና የእ​ህ​ሉን ዋጋ ጨም​ረው።” እር​ሱም ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ። 3ነግህ በሆነ ጊዜም ሰዎቹ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሄዱ ዘንድ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። 4ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ወጥ​ተው ገና ሳይ​ርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እን​ዲህ አለ፥ “ተነ​ሥ​ተህ ሰዎ​ቹን ተከ​ት​ለህ ያዛ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በመ​ል​ካሙ ፈንታ ስለ​ምን ክፉን መለ​ሳ​ችሁ? 5ጌታዬ የሚ​ጠ​ጣ​በ​ትን፥ ምስ​ጢ​ር​ንም የሚ​ያ​ው​ቅ​በ​ትን የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ችሁ? ባደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር በደ​ላ​ችሁ።” 6እር​ሱም ሂዶ አገ​ኛ​ቸው፤ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ስለ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም ነገር ለምን ክፉ ትከ​ፍ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የጌ​ታ​ዬ​ንስ የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ች​ሁኝ?” አላ​ቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. ምዕ. 44 ቍ. 6 “እር​ሱም ሄዶ አገ​ኛ​ቸው ይህ​ንም ቃል ነገ​ራ​ቸው” ይላል። 7እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ​ችን እን​ደ​ዚህ ለምን ክፉ ትና​ገ​ራ​ለህ? ይህን ነገር ያደ​ር​ጉት ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ አግ​ባ​ባ​ቸው አይ​ደ​ለም። 8በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ችን አፍ ያገ​ኘ​ነ​ውን ብር እን​ኳን ይዘን ከከ​ነ​ዓን ሀገር ወደ አንተ ተመ​ል​ሰ​ናል፤ ከጌ​ታ​ህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እን​ዴት እን​ሰ​ር​ቃ​ለን? 9አሁ​ንም ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት እርሱ ይሙት፤ እኛም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን።” 10እር​ሱም አለ፥ “አሁ​ንም እን​ዲሁ እንደ ነገ​ራ​ችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት እርሱ ለእኔ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ፤ እና​ን​ተም ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።” 11እየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ፈጥ​ነው ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አወ​ረዱ፤ እየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን ፈቱ። 12እር​ሱም ከታ​ላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረ​በ​ራ​ቸው፤ ጽዋ​ው​ንም በብ​ን​ያም ዓይ​በት ውስጥ አገ​ኘው። 13ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​አ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ጭነው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ተመ​ለሱ።
14ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ፤ እር​ሱም ገና ከዚ​ያው ነበረ፤ በፊ​ቱም በም​ድር ላይ ወደቁ። 15ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?”#“እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” የሚ​ለው ከግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና ከዕብ. የተ​ወ​ሰደ ነው። አላ​ቸው። 16ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።” 17ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት ሰው እርሱ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ እንጂ፤ እና​ንተ ግን ወደ አባ​ታ​ችሁ በደ​ኅና ሂዱ።”
ይሁዳ ስለ ብን​ያም ዮሴ​ፍን መለ​መኑ
18ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና። 19ጌታዬ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ አባት አላ​ች​ሁን? ወይስ ወን​ድም? ብለህ ጠየ​ቅ​ሃ​ቸው። 20እኛም ለጌ​ታዬ እን​ዲህ አልን፦ ሽማ​ግሌ አባት አለን፤ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደ​ውም ታናሽ ብላ​ቴና አለ፤ ወን​ድሙ ግን ሞተ፤ ለእ​ና​ቱም እርሱ ብቻ​ውን ቀረ፤ አባ​ቱም ይወ​ድ​ደ​ዋል። 21አን​ተም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፦ ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ አልህ። 22ጌታ​ዬ​ንም፦ ብላ​ቴ​ናው አባ​ቱን መተው አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ የተ​ወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞ​ታ​ልና አል​ንህ። 23አንተ ጌታ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ላ​መ​ጣ​ች​ሁት ዳግ​መኛ ፊቴን አታ​ዩም አል​ኸን። 24ወደ ባሪ​ያህ ወደ አባ​ታ​ችን በተ​መ​ለ​ስን ጊዜም የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ነገ​ር​ነው። 25አባ​ታ​ች​ንም፦ ዳግ​መኛ ሄዳ​ችሁ ጥቂት እህል ሸም​ቱ​ልን አለን። 26እኛም አል​ነው፦ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ካል​ሄደ መሄድ አን​ች​ልም፤ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚ​ያን ሰው ፊት ማየት አይ​ቻ​ለ​ን​ምና። 27አገ​ል​ጋ​ይህ አባ​ታ​ች​ንም እን​ዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወን​ዶች ልጆ​ችን እንደ ወለ​ደ​ች​ልኝ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ 28አን​ዱም ከእኔ ወጣ፤ አውሬ በላው አላ​ች​ሁኝ፤ እስከ ዛሬም ገና አላ​የ​ሁ​ትም፤ 29ይህ​ንም ከእኔ ለይ​ታ​ችሁ ደግሞ ብት​ወ​ስ​ዱት በመ​ን​ገ​ድም ክፉ ቢያ​ገ​ኘው፥ እር​ጅ​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ። 30አሁ​ንም እኛ ወደ አባ​ታ​ችን ወደ አገ​ል​ጋ​ይህ ብን​ሄድ፥ ብላ​ቴ​ና​ውም ከእኛ ጋር ከሌለ፥ ነፍሱ በብ​ላ​ቴ​ናው ነፍስ ታስ​ራ​ለ​ችና 31ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር እን​ደ​ሌለ በአየ ጊዜ ይሞ​ታል፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን የአ​ባ​ታ​ች​ንን እር​ጅና በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር እና​ወ​ር​ዳ​ለን። 32እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በአ​ባቴ ዘንድ ስለ ብላ​ቴ​ናው እን​ዲህ ብዬ ተው​ሼ​አ​ለ​ሁና፦ እር​ሱ​ንስ ወደ አንተ መልሼ በፊ​ትህ ባላ​ቆ​መው በአ​ባቴ ዘንድ በዘ​መ​ናት ሁሉ ኀጢ​አ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ። 33አሁ​ንም እኔ በብ​ላ​ቴ​ናው ፈንታ የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋይ ሆኜ ልቀ​መጥ፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር ይሂድ። 34አለ​ዚ​ያም ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባ​ታ​ችን እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? አባ​ታ​ች​ንን የሚ​ያ​ገ​ኘ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ