ኦሪት ዘፍጥረት 46
46
ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ ጋር ወደ ግብፅ መሄዱ
1እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘቅተ መሐላም መጣ፤ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። 2እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፥ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም “ምንድን ነው?” አለ። 3አለውም፥ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መውረድን አትፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። 4እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ፤ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ልጅህ ዮሴፍም እጁን በዐይንህ ላይ ያኖራል።” 5ያዕቆብም ከዐዘቅተ መሐላ ተነሣ፤ የእስራኤልም ልጆች አባታቸውን፥ ገንዘባቸውን፥ ሚስቶቻቸውንም እነርሱን ያመጡባቸው ዘንድ ዮሴፍ በላካቸው ሰረገሎች ጭነው ወሰዱ።#ዕብ. “ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በላካቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃኖቻቸውን፥ ሚስቶቻቸውንም ወሰዱ” ይላል። 6ጓዛቸውን፥ በከነዓን ሀገርም ያገኙትን ጥሪታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤ 7ወንዶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የሴቶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው።
8ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። 9የሮቤልም ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስሮን፥ ከርሜ። 10የስምዖን ልጆች፤ ይሙኤል፥ ያሚን፥ አኡድ፥ ያኪን፥ ሱሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳዑል። 11የሌዊም ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 12የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስሮም፥ ይሞሔል፤ 13የይሳኮርም ልጆች፤ ቶላዕ፥ ፎሓ፥ ያሱብ፥ ስምራ። 14የዛብሎንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል። 15ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ሰላሳ ሦስት” ይላል። ነፍስ ናቸው። 16የጋድም ልጆች፤ ስፎን፥ ሐጊ፥ ሱኒ፥ አዜን፥ አድ፥ አሮሐድ፥ አርሔል። 17የአሴርም ልጆች፤ ኢያምን፥ ኢያሱ፥ኢዩል፥ በሪዓ፥ እኅታቸው ሳራ፤ የበሪዓ ልጆችም፤ ኮቦር፥ መልኪኤል። 18ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እርስዋም እነዚህን ዐሥራ ስድስቱን ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። 19የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው። 20ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው። 21የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ። 22ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔል ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሁሉም ዐሥራ አራት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዐሥራ ስምንት” ይላል። ነፍስ ናቸው። 23የዳንም ልጅ አሳ ነው። 24የንፍታሌምም ልጆች፤ አሴሔል፥ ጎሂን፥ ዮሴር ሴሌም። 25ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ ባላ የወለደቻቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። 26ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጕልበቱ የወጡት፥ ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ፥ ሁላቸው ስድሳ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ስድሳ ስድስት” ይላል። ናቸው። 27በግብፅ ምድር የተወለዱለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዘጠኝ” ይላል። ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባ አምስት” ይላል። ናቸው።
ያዕቆብና ቤተ ሰቡ በግብፅ
28ይሁዳንም ኤሮስ በምትባል በራምሴ ከተማ እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከው፤ 29ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፤ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአየውም ጊዜ አንገቱን አቀፈው፤ ረዥም ጊዜም አለቀሰ። 30እስራኤልም ዮሴፍን፥ “አንተ ገና በሕይወት ሳለህ ፊትህን አይችአለሁና አሁን ልሙት” አለው። 31ዮሴፍም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞችና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤ 32እነርሱም ከብት ጠባቂዎች፥ መንጋ አርቢዎች ናቸው፤ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። 33ፈርዖንም ቢጠራችሁ ተግባራችሁስ ምንድን ነው? ቢላችሁ፥ 34በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐረብ በኩል በጌሤም እንድትቀመጡ እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴንነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን” በሉት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 46: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ