የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 47

47
ዮሴፍ የዘ​መ​ዶ​ቹን መም​ጣት ለፈ​ር​ዖን መና​ገሩ
1ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።” 2ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም አም​ስት ሰዎ​ችን ወስዶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​ማ​ቸው። 3ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድ​ሞች፥ “ሥራ​ችሁ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈር​ዖ​ንን፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፥ አባ​ታ​ች​ንም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች ነን” አሉት። 4ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።” 5ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አባ​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል፤ እነሆ፥ የግ​ብፅ ምድር በፊ​ትህ ናት፤ 6በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤#ዕብ. “በጌ​ሤም ምድር ይኑሩ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”#“ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 7ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው። 8ፈር​ዖ​ንም ያዕ​ቆ​ብን፥ “የኖ​ር​ኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው። 9ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።” 10ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ወጣ። 11ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው። 12ዮሴ​ፍም ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ ለአ​ባ​ቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው እየ​ሰ​ፈረ እህ​ልን ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።
በግ​ብፅ የራብ መጽ​ና​ትና የዮ​ሴፍ አመ​ራር
13በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ። 14ዮሴ​ፍም ከግ​ብፅ ምድ​ርና ከከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ህል ሸመታ የተ​ገ​ኘ​ውን ብሩን ሁሉ አከ​ማቸ፤ ዮሴ​ፍም ብሩን ወደ ፈር​ዖን ቤት አስ​ገ​ባው። 15ብሩም በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር አለቀ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እን​ዲህ ሲሉ፥ “በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አል​ቆ​ብ​ና​ልና።” 16ዮሴ​ፍም፥ “ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ብር ከአ​ለ​ቀ​ባ​ችሁ በከ​ብ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈንታ እህል እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ። 17ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ ዮሴ​ፍም በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸው፥ በበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በላ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ፈንታ እህ​ልን ሰጣ​ቸው፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም ስለ ከብ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ፈንታ እህ​ልን መገ​ባ​ቸው። 18ያችም ዓመት ተፈ​ጸ​መች፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዋም ዓመት ወደ እርሱ መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ ለጌ​ታ​ችን ሞተን እን​ዳ​ና​ል​ቅ​በት እህል ስጠን፤ ብሩ በፍ​ጹም አለቀ፤ ንብ​ረ​ታ​ች​ንና ከብ​ታ​ች​ንም በጌ​ታ​ችን ዘንድ ነው፤ ከሰ​ው​ነ​ታ​ች​ንና ከም​ድ​ራ​ችን በቀር በጌ​ታ​ችን ፊት አን​ዳች የቀ​ረን የለም፤ 19እን​ግ​ዲህ እኛ በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ፥ እኛ​ንም፥ ምድ​ራ​ች​ን​ንም በእ​ህል ግዛን፤ እኛም ለፈ​ር​ዖን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ ምድ​ራ​ች​ንም ለእ​ርሱ ትሁን፤ እኛ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ እን​ዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።” 20ዮሴ​ፍም የግ​ብ​ፅን ምድር ሁሉ ለፈ​ር​ዖን ገዛ፤ የግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለ​ጸ​ና​ባ​ቸው ርስ​ታ​ቸ​ውን ሸጠ​ዋ​ልና፤ ምድ​ሪቱ ለፈ​ር​ዖን ሆነች። 21ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ አን​ሥቶ እስከ ሌላው ዳር​ቻዋ ድረስ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ጋ​ቸው። 22ዮሴፍ የካ​ህ​ና​ትን ምድር ብቻ አል​ገ​ዛም፤ ፈር​ዖን ለካ​ህ​ናቱ ድርጎ ይሰ​ጣ​ቸው ነበ​ርና፥ ፈር​ዖ​ንም የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን አል​ሸ​ጡም። 23ዮሴ​ፍም የግ​ብ​ፅን ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ ዛሬ እና​ን​ተ​ንና ምድ​ራ​ች​ሁን ለፈ​ር​ዖን ገዝ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ንተ ዘር ውሰ​ዱና ምድ​ሪ​ቱን ዝሩ፤ 24በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።” 25እነ​ር​ሱም፥ “አንተ አዳ​ን​ኸን፤ በጌ​ታ​ች​ንም ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘን፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሆ​ና​ለን” አሉት። 26ዮሴ​ፍም ለፈ​ር​ዖን ካል​ሆ​ነ​ችው ከካ​ህ​ናቱ ምድር በቀር አም​ስ​ተ​ኛው እጅ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲ​ሆን በግ​ብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደ​ረ​ጋት።
ያዕ​ቆብ በሀ​ገሩ እን​ዲ​ቀ​በር ዮሴ​ፍን መለ​መኑ
27እስ​ራ​ኤ​ልም በግ​ብፅ ምድር በጌ​ሤም ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም ርስ​ታ​ቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅ​ግም ተባዙ። 28ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀ​መጠ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም መላው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ። 29የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የሞቱ ቀን ቀረበ፤ ልጁን ዮሴ​ፍ​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ​ህን በጕ​ል​በቴ ላይ አድ​ርግ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም እን​ዳ​ት​ቀ​ብ​ረኝ ምሕ​ረ​ት​ንና እው​ነ​ትን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ 30ከአ​ባ​ቶ​ችም ጋር በአ​ን​ቀ​ላ​ፋሁ ጊዜ ከግ​ብፅ ምድር አው​ጥ​ተህ ትወ​ስ​ደ​ኛ​ለህ፤ በአ​ባ​ቶ​ችም መቃ​ብር ትቀ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።” እር​ሱም፥ “እንደ ቃልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ማል​ልኝ” አለው። 31ዮሴ​ፍም ማለ​ለት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ል​ጋው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በበ​ትሩ ጨፍ ሰገደ” ይላል። ራስ ላይ ሰገደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ