የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 11

11
ስለ አበው እም​ነት
1እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት። 2በዚ​ህም ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ተመ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው። 3#ዘፍ. 1፥1፤ መዝ. 32፥6-9፤ ዮሐ. 1፥3። ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን። 4#ዘፍ. 4፥3-10። አቤል ከቃ​ኤል ይልቅ የሚ​በ​ልጥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት አቀ​ረበ፤ በዚ​ህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመ​ሰ​ከ​ረ​ለት፤ ምስ​ክ​ሩም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን በመ​ቀ​በል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በዚ​ህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተና​ገረ። 5#ዘፍ. 5፥21-24። ሄኖክ ሞትን እን​ዳ​ያይ በእ​ም​ነት ተወ​ሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ወሰ​ደው አል​ተ​ገ​ኘም፤ ሳይ​ወ​ሰ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እንደ አሰ​ኘው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ለ​ታል። 6ያለ እም​ነ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ቻ​ልም፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርብ ሰው አስ​ቀ​ድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳለ፥ ለሚ​ሹ​ትም ዋጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሊያ​ምን ይገ​ባ​ዋል። 7#ዘፍ. 6፥13-22። ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
8 # ዘፍ. 12፥1-5። አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ። 9#ዘፍ. 35፥27። በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ። 10መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና። 11#ዘፍ. 18፥11-14፤ 21፥2። ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና። 12#ዘፍ. 15፥5፤ 22፥17፤ 32፥12። ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ።
13 # ዘፍ. 23፥4፤ 1ዜ.መ. 29፥15፤ መዝ. 38፥12። እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ። 14እን​ዲህ የሚሉ ግን ሀገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚሹ ያሳ​ያሉ። 15ከእ​ር​ስዋ የወ​ጡ​ባ​ትን ሀገር ቢሹ ኖሮስ፥ ወደ እር​ስዋ ሊመ​ለሱ በተ​ቻ​ላ​ቸው ነበር። 16አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።
17 # ዘፍ. 22፥1-14። አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ተ​ነው ጊዜ ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ይሠ​ዋው ዘንድ በእ​ም​ነት ወሰ​ደው። 18#ዘፍ. 21፥12። “በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል” ብሎ ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለ​ትን አንድ ልጁን አቀ​ረ​በው። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ ሊያ​ስ​ነ​ሣው እን​ደ​ሚ​ችል አም​ኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም ያው የተ​ሰ​ጠው መታ​ሰ​ቢያ ሆነ​ለት። 20#ዘፍ. 27፥27-29፤39-40። ያገ​ኙት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ነገር ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ኤሳ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው። 21#ዘፍ. 47፥31—48፥20። ያዕ​ቆ​ብም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ የዮ​ሴ​ፍን ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው፤ በበ​ትሩ ጫፍም ሰገደ። 22#ዘፍ. 50፥24-25፤ ዘፀ. 13፥19። ዮሴ​ፍም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ፥ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ መው​ጣት በእ​ም​ነት ዐሰበ፤ ዐጽ​ሙ​ንም ትተው እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘዘ።
23 # ዘፀ. 2፥2፤ 1፥22። ሙሴ በተ​ወ​ለደ ጊዜ በእ​ም​ነት ሦስት ወር በአ​ባቱ ቤት ሸሸ​ጉት፤ ሕፃኑ መል​ካም እንደ ሆነ አይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ የን​ጉ​ሥ​ንም ትእ​ዛዝ አል​ፈ​ሩም። 24#ዘፀ. 2፥10-12። ሙሴም በአ​ደገ ጊዜ የፈ​ር​ዖን የልጅ ልጅ እን​ዳ​ይ​ባል በእ​ም​ነት እንቢ አለ፤ 25ለጊ​ዜው በኀ​ጢ​አት ከሚ​ገኝ ደስታ ይልቅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀ​በ​ልን መረጠ። 26የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት ከግ​ብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ባለ​ጠ​ግ​ነት እን​ደ​ሚ​ሆን ዐው​ቆ​አ​ልና፥ ዋጋ​ው​ንም ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። 27#ዘፀ. 2፥15። የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤#ግእዙ “በግ​ብፅ ሀገር ኖረ” ይላል። ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና። 28#ዘፀ. 12፥21-30። ቸነ​ፈር በኵ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ባ​ቸው በእ​ም​ነት ፋሲ​ካን አደ​ረገ፤ ደሙ​ንም ረጨ።
29 # ዘፀ. 14፥21-31። በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ። 30#ኢያ. 6፥12-21። ሰባት ቀን ከዞ​ሩ​አት በኋላ የኢ​ያ​ሪኮ ቅጽር በእ​ም​ነት ወደቀ። 31#ኢያ. 2፥1-21፤ 6፥22-25። ዘማ ረአ​ብም በእ​ም​ነት ከከ​ሓ​ዲ​ዎች ጋር አል​ጠ​ፋ​ችም፤ ጕበ​ኞ​ችን በሰ​ላም ተቀ​ብላ ሰው​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ችና። 32#መሳ. 6፥11—8፥32፤ 4፥6—5፥31፤ 13፥2—16፥31፤ 11፥1—12፥7፤ 1ሳሙ. 16፥1፤ 1ነገ. 2፥11። እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና። 33#ዳን. 6፥1-27። እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ተጋ​ደሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሡ፤ ጽድ​ቅን አደ​ረጉ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ውን አገኙ፤ የአ​ና​ብ​ስ​ት​ንም አፍ ዘጉ ። 34#ዳን. 3፥1-30። የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ። 35#1ነገ. 17፥17-24፤ 2ነገ. 4፥25-37። ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና። 36#1ነገ. 22፥26-27፤ 2ዜ.መ. 18፥25-26፤ ኤር. 20፥2፤ 37፥15፤ 38፥6። የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ። 37#2ዜ.መ. 24፥21። በመ​ጋዝ የሰ​ነ​ጠ​ቁ​አ​ቸው፥ በድ​ን​ጋይ የወ​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ በሰ​ይ​ፍም ስለት የገ​ደ​ሉ​ዋ​ቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምን​ጣ​ፍና የፍ​የል ሌጦ ለብ​ሰው ዞሩ፤ ተጨ​ነቁ፤ ተቸ​ገሩ፤ መከራ ተቀ​በሉ፤ ተራቡ፥ ተጠ​ሙም።#“ተራቡ ተጠ​ሙም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 38ዓለም የማ​ይ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱ​ርና ተራራ ለተ​ራራ፥ ዋሻ ለዋ​ሻና ፍር​ኩታ ለፍ​ር​ኩ​ታም ዞሩ።
39እነ​ዚ​ህም ሁሉ በእ​ም​ነ​ታ​ቸው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ላ​ቸው ሳሉ፥ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የተ​ስፋ ቃል አላ​ገ​ኙም። 40ያለ እኛ ፍጹ​ማን እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን አስ​ቀ​ድሞ በይ​ኖ​አ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ