ወደ ዕብራውያን 11
11
ስለ አበው እምነት
1እምነትስ ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የምታረጋግጥ፥ የማናየውንም ነገር የምታስረዳ ናት። 2በዚህም ለሽማግሌዎች ተመሰከረላቸው። 3#ዘፍ. 1፥1፤ መዝ. 32፥6-9፤ ዮሐ. 1፥3። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠረ፥ የሚታየውም ነገር ከማይታየው እንደ ሆነ በእምነት እናውቃለን። 4#ዘፍ. 4፥3-10። አቤል ከቃኤል ይልቅ የሚበልጥ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ምስክሩም መሥዋዕቱን በመቀበል እግዚአብሔር ነው። በዚህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተናገረ። 5#ዘፍ. 5፥21-24። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም፤ ሳይወሰድም እግዚአብሔርን ደስ እንደ አሰኘው ተመስክሮለታል። 6ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው አስቀድሞ እግዚአብሔር እንዳለ፥ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጣቸው ሊያምን ይገባዋል። 7#ዘፍ. 6፥13-22። ኖኅም ስለማይታየው ነገር የነገሩትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መርከብን ሠራ፤ በዚህም ዓለምን አስፈረደበት፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
8 #
ዘፍ. 12፥1-5። አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ። 9#ዘፍ. 35፥27። በእምነትም ከሀገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰጠው ሀገር እንደ ስደተኛ በድንኳን፥ ተስፋውን ከሚወርሱአት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ኖረ። 10መሠረት ያላትን ሠሪዋና ፈጣሪዋ እግዚአብሔር የሆነላትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበርና። 11#ዘፍ. 18፥11-14፤ 21፥2። ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረጀችበት ወራት ዘር ታስገኝ ዘንድ በእምነት ኀይልን አገኘች፤ ተስፋ የሰጣት የታመነ እንደ ሆነ አምናለችና። 12#ዘፍ. 15፥5፤ 22፥17፤ 32፥12። ስለዚህም ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ።
13 #
ዘፍ. 23፥4፤ 1ዜ.መ. 29፥15፤ መዝ. 38፥12። እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፤ ተስፋቸውንም አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው እጅ ነሱኣት፤ በምድሪቱም ላይ እነርሱ እንግዶችና መጻተኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ። 14እንዲህ የሚሉ ግን ሀገራቸውን እንደሚሹ ያሳያሉ። 15ከእርስዋ የወጡባትን ሀገር ቢሹ ኖሮስ፥ ወደ እርስዋ ሊመለሱ በተቻላቸው ነበር። 16አሁን ግን፥ በሰማያት ያለችውን የምትበልጠውን ሀገር ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእነርሱ አያፍርም፤ ተስፋ ያደረጉአትን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋልና።
17 #
ዘፍ. 22፥1-14። አብርሃምም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ ልጁን ይስሐቅን ይሠዋው ዘንድ በእምነት ወሰደው። 18#ዘፍ. 21፥12። “በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል” ብሎ ተስፋ ያናገረለትን አንድ ልጁን አቀረበው። 19እግዚአብሔር ከሙታን ለይቶ ሊያስነሣው እንደሚችል አምኖአልና፤ ስለዚህም ያው የተሰጠው መታሰቢያ ሆነለት። 20#ዘፍ. 27፥27-29፤39-40። ያገኙት ዘንድ ስለ አላቸው ነገር ይስሐቅ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው። 21#ዘፍ. 47፥31—48፥20። ያዕቆብም በሚሞትበት ጊዜ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን በእምነት ባረካቸው፤ በበትሩ ጫፍም ሰገደ። 22#ዘፍ. 50፥24-25፤ ዘፀ. 13፥19። ዮሴፍም በሚሞትበት ጊዜ፥ ስለ እስራኤል ልጆች ከግብፅ መውጣት በእምነት ዐሰበ፤ ዐጽሙንም ትተው እንዳይወጡ አዘዘ።
23 #
ዘፀ. 2፥2፤ 1፥22። ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት፤ ሕፃኑ መልካም እንደ ሆነ አይተውታልና፤ የንጉሥንም ትእዛዝ አልፈሩም። 24#ዘፀ. 2፥10-12። ሙሴም በአደገ ጊዜ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እንቢ አለ፤ 25ለጊዜው በኀጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ። 26የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት ከግብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንደሚሆን ዐውቆአልና፥ ዋጋውንም ተመልክቶአልና። 27#ዘፀ. 2፥15። የንጉሡንም ቍጣ ሳይፈራ፥ የግብፅን ሀገር በእምነት ተወ፤#ግእዙ “በግብፅ ሀገር ኖረ” ይላል። ከሚያየው ይልቅ የማይታየውን ሊፈራ ወዶአልና። 28#ዘፀ. 12፥21-30። ቸነፈር በኵራቸውን እንዳያጠፋባቸው በእምነት ፋሲካን አደረገ፤ ደሙንም ረጨ።
29 #
ዘፀ. 14፥21-31። በደረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤርትራን ባሕር በእምነት ተሻገሩአት፤ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ሰጠሙ። 30#ኢያ. 6፥12-21። ሰባት ቀን ከዞሩአት በኋላ የኢያሪኮ ቅጽር በእምነት ወደቀ። 31#ኢያ. 2፥1-21፤ 6፥22-25። ዘማ ረአብም በእምነት ከከሓዲዎች ጋር አልጠፋችም፤ ጕበኞችን በሰላም ተቀብላ ሰውራቸዋለችና። 32#መሳ. 6፥11—8፥32፤ 4፥6—5፥31፤ 13፥2—16፥31፤ 11፥1—12፥7፤ 1ሳሙ. 16፥1፤ 1ነገ. 2፥11። እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤልና ስለ ሌሎች ነቢያት እነግራችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና። 33#ዳን. 6፥1-27። እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ። 34#ዳን. 3፥1-30። የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ። 35#1ነገ. 17፥17-24፤ 2ነገ. 4፥25-37። ሴቶችም እንደ ትንሣኤ ቀን ተነሥተውላቸው ሙታኖቻቸውን ተቀበሉ፤ ተፈርዶባቸው የሞቱም አሉ፤ የምትበልጠውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አልወደዱምና። 36#1ነገ. 22፥26-27፤ 2ዜ.መ. 18፥25-26፤ ኤር. 20፥2፤ 37፥15፤ 38፥6። የገረፉአቸው፥ የዘበቱባቸውና ያሠሩአቸው ወደ ወህኒ ያገቡአቸውም አሉ። 37#2ዜ.መ. 24፥21። በመጋዝ የሰነጠቁአቸው፥ በድንጋይ የወገሩአቸው፥ በሰይፍም ስለት የገደሉዋቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምንጣፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፤ ተቸገሩ፤ መከራ ተቀበሉ፤ ተራቡ፥ ተጠሙም።#“ተራቡ ተጠሙም” የሚለው በግሪኩ የለም። 38ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱርና ተራራ ለተራራ፥ ዋሻ ለዋሻና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ።
39እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙም። 40ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ፥ እግዚአብሔር ስለ እኛ የምትበልጠውን አስቀድሞ በይኖአልና።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ