የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 3

3
ስለ ቤትና ባለ​ቤቱ
1አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ። 2#ዘኍ​. 12፥7። ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታ​መነ እንደ ሆነ፥ እርሱ ለላ​ከው የታ​መነ እው​ነ​ተኛ ነው። 3ነገር ግን የባ​ለ​ቤት ክብሩ ከቤቱ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ፥ ክብሩ ከሙሴ ክብር ይልቅ እጅግ ይበ​ል​ጣል፤ 4ቤትን ሁሉ ሰው ይሠ​ራ​ዋ​ልና፤ ለሁሉ ግን ሠሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። 5ሙሴስ በኋላ ስለ​ሚ​ነ​ገ​ረው ነገር ምስ​ክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታ​መነ ነበረ። 6ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።
7 # መዝ. 94፥7-11። መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ። 8በም​ድረ በዳ በተ​ፈ​ታ​ተ​ኑ​በት ቀን እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ። 9የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፤ አርባ ዘመ​ንም ሥራ​ዬን አዩ። 10ስለ​ዚህ ይህ​ቺን ትው​ልድ ተቈ​ጣ​ኋት፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ‘ልባ​ቸው ዘወ​ትር ይስ​ታል፤ እነ​ርሱ ግን መን​ገ​ዴን አላ​ወ​ቁም።’ 11ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም ብዬ በቍ​ጣዬ ማልሁ።” 12ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከእ​ና​ንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይ​ማ​ኖት የጐ​ደ​ለ​ውና ተጠ​ራ​ጣሪ፥ ከሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ያ​ችሁ ክፉ ልብ አይ​ኑር። 13ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ። 14በዚች ጽድቅ እስከ መጨ​ረሻ የቀ​ደ​መ​ውን ሥር​ዐ​ታ​ች​ንን አጽ​ን​ተን ከጠ​በ​ቅን ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ሁነ​ና​ልና። 15“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና። 16ሰም​ተው ያሳ​ዘ​ኑ​ትስ እነ​ማን ናቸው? በሙሴ እጅ ከግ​ብፅ የወ​ጡት ሁሉ አይ​ደ​ሉ​ምን? 17አርባ ዘመን የተ​ቈ​ጣ​ቸ​ውስ እነ​ማን ነበሩ? የበ​ደሉ፥ ሬሳ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ የወ​ደ​ቀው አይ​ደ​ሉ​ምን? 18ከካ​ዱት በቀር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዳ​ይ​ገቡ በማን ላይ ማለ? 19አላ​መ​ኑ​ምና፥ ለመ​ግ​ባት እን​ዳ​ል​ቻሉ እነሆ፥ እና​ያ​ለን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ