ወደ ዕብራውያን 3
3
ስለ ቤትና ባለቤቱ
1አሁንም ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞቻችን ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ። 2#ዘኍ. 12፥7። ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታመነ እንደ ሆነ፥ እርሱ ለላከው የታመነ እውነተኛ ነው። 3ነገር ግን የባለቤት ክብሩ ከቤቱ እንደሚበልጥ፥ ክብሩ ከሙሴ ክብር ይልቅ እጅግ ይበልጣል፤ 4ቤትን ሁሉ ሰው ይሠራዋልና፤ ለሁሉ ግን ሠሪው እግዚአብሔር ነው። 5ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ። 6ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤ እኛም የምንደፍርበትን፥ የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።
7 #
መዝ. 94፥7-11። መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብሎአልና፥ “ዛሬ ቃሉን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ። 8በምድረ በዳ በተፈታተኑበት ቀን እንደ አሳዘኑት ጊዜ። 9የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፤ አርባ ዘመንም ሥራዬን አዩ። 10ስለዚህ ይህቺን ትውልድ ተቈጣኋት፤ እንዲህም አልሁ፦ ‘ልባቸው ዘወትር ይስታል፤ እነርሱ ግን መንገዴን አላወቁም።’ 11ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ።” 12ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ዕወቁ፤ ከእናንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይማኖት የጐደለውና ተጠራጣሪ፥ ከሕያው እግዚአብሔር የሚለያችሁ ክፉ ልብ አይኑር። 13ዛሬ የሚባለው ቀን ሳለ ከእናንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢአት በሚያደርስ ስሕተት እንዳይጸና ሁልጊዜ ሰውነታችሁን መርምሩ። 14በዚች ጽድቅ እስከ መጨረሻ የቀደመውን ሥርዐታችንን አጽንተን ከጠበቅን ከክርስቶስ ጋር አንድ ሁነናልና። 15“ዛሬ ቃሉን ብትሰሙ እነዚያ እንደ አሳዘኑት ጊዜ ልባችሁን አታጽኑ” ብሎአልና። 16ሰምተው ያሳዘኑትስ እነማን ናቸው? በሙሴ እጅ ከግብፅ የወጡት ሁሉ አይደሉምን? 17አርባ ዘመን የተቈጣቸውስ እነማን ነበሩ? የበደሉ፥ ሬሳቸውም በምድረ በዳ የወደቀው አይደሉምን? 18ከካዱት በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ በማን ላይ ማለ? 19አላመኑምና፥ ለመግባት እንዳልቻሉ እነሆ፥ እናያለን።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ