ትንቢተ ሆሴዕ 13
13
በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ
1ኤፍሬም እንደ ተናገረ በእስራኤል ሥርዐቱን ወሰደ፤ ለበዓልም አደረገው፤ ሞተም። 2ዳግመኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚሠራው አምሳል ከወርቃቸውና ከብራቸው ጣዖትን ሠሩ፤ እንዲህም አሉ #ዕብ. “ስለ እነርሱም የሚሠዉ ሰዎች እንቦሳውን ይሳሙ” ይላል።“ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አልቋል።” 3ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋት እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፋስም ከዐውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከምድጃም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።
4ሰማይን ያጸናሁ፥ ምድርንም የፈጠርሁ፥ እጆችም የሰማይ ሠራዊትን ያቆሙ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንዳትከተላቸውም እነርሱን አላሳየሁህም። ከግብፅ ምድርም ያወጣሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አትወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለምና። 5በምድረ በዳና በዞርህበት ምድር ሁሉ ጠበቅሁህ። 6ከተሰማራችሁ በኋላ ጠገባችሁ፤ በጠገባችሁም ጊዜ ልባችሁ ታበየ፤ ስለዚህም ረሳችሁኝ። 7ስለዚህም ለይሁዳ ቤት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለይሁዳ ቤትና ... ለኤፍሬምም” አይልም። እንደ አንበሳ፥ ለኤፍሬምም እንደ ነብር ሆንሁባቸው። 8በአሦራውያንም መንገድ አጠገብ እንደ ተራበ ድብ እገጥማቸዋለሁ፤ የልባቸውንም ሥር እቈርጣለሁ፤ በዚያም የዱር አንበሶች ይበሏቸዋል፤ የምድረ በዳም አራዊት ይነጣጠቋቸዋል።
9እስራኤል ሆይ! በመከራህ ጊዜ ማን ይረዳሃል? 10ንጉሥህ ወዴት አለ? በየከተማህ ሁሉ እስኪ ያድንህ! ንጉሥና አለቃ ስጠኝ የምትለኝ እስኪ እነርሱ ይበቀሉልህ? 11በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት። 12የዐመፅህን ወንጀል ታገሥሁት፤ የኤፍሬም ኀጢአቱም ተከማችትዋል ። 13ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይዘዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋቂም አይደለም፤ በልጆችም ተግሣጽ አይጸናም። 14ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፤ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መንሣትህ ወዴት አለ? ደስታህ ከዐይኖችህ ተሰወረች።
15ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 13: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ