ትንቢተ ሆሴዕ 3
3
ሆሴዕና አመንዝራዪቱ ሴት
1እግዚአብሔርም፥ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳን፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ክፋትና ዝሙት ያለባትን ሴት ውደድ” አለኝ። 2እኔም በዐሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል#“ተኩል” የሚለው በዕብ. ብቻ። ገብስና በአንድ ፊቀን ወይን#“በአንድ ፊቀን ወይን” የሚለው በዕብ. የለም። ተወዳጀኋት። 3“ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፤ አታመንዝሪም፤ ሌላ ሰውንም አታግቢ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” አልኋት። 4የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤#ዕብ. “ዓምድ” ይላል “ምሥዋዕ” በግሪክ ሰባ. ሊ. ነው። ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤#“ያለ ካህንና ያለ ራእይ” የሚለው በዕብ. የለም። ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም#“ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤ 5ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን እግዚአብሔርንና ቸርነቱን ያስቡታል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ