የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 4

4
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ ወቀሰ
1እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 2ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ። 3ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች#“ከም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ። 4ነገር ግን ሕዝቤ እን​ደ​ሚ​ከ​ራ​ከር ካህን ነውና እን​ግ​ዲህ የሚ​ከ​ራ​ከር፥ ማንም አይ​ኑር፥ የሚ​ዘ​ል​ፍም ማንም አይ​ኑር። 5በቀ​ንም ትደ​ክ​ማ​ለህ፤ ነቢ​ዩም ከአ​ንተ ጋር ይደ​ክ​ማል፤ እና​ታ​ች​ሁም ሌሊ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች።#ዕብ. “እና​ት​ህ​ንም አጠ​ፋ​ታ​ለሁ” ይላል።
6ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ። 7እንደ ብዛ​ታ​ቸው መጠን ኀጢ​አት ሠሩ​ብኝ፤ እኔም ክብ​ራ​ቸ​ውን ወደ ውር​ደት እለ​ው​ጣ​ለሁ። 8ሕዝ​ቤ​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሕ​ዝቤ ኀጢ​አት መብል ሆኖ​ላ​ቸ​ዋል ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም በበ​ደ​ላ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋል” ይላል። ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም በበ​ደ​ላ​ቸው ይወ​ስ​ዷ​ታል። 9እንደ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ካህኑ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መጠ​በቅ ትተ​ዋ​ልና ሲበሉ አይ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሲያ​መ​ነ​ዝ​ሩም አይ​በ​ዙም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ​ቀ​ና​ቸ​ውም” ይላል።
11የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ። 12ሕዝቤ በዝ​ሙት መን​ፈስ ስተ​ዋ​ልና ከአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ርቀው አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና በት​ርን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ በት​ሩም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋል። 13በተ​ራ​ሮ​ችም ራስና በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎች ላይ ይሠ​ዋሉ፤ ጥላ​ውም መል​ካም ነውና ከኮ​ም​በ​ልና ከል​ብን፥ ከአ​ሆ​ማም ዛፍ በታች ያር​ዳሉ፤ ስለ​ዚህ ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ይሰ​ስ​ናሉ፤ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም ያመ​ነ​ዝ​ራሉ። 14ወን​ዶ​ችም ደግሞ ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ይጫ​ወ​ታ​ሉና፥ ከጋ​ለ​ሞ​ቶ​ችም ጋር ይሠ​ዋ​ሉና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ሰኑ ጊዜ፥ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም በአ​መ​ነ​ዘሩ ጊዜ አል​ቀ​ጣ​ኋ​ቸ​ውም፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ው​ልም ሕዝብ ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር ይቀ​ላ​ቀ​ላል።#ዕብ. “የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ይገ​ለ​በ​ጣል” ይላል።
15እስ​ራ​ኤል ሆይ! አንተ አላ​ዋቂ አት​ሁን፤ አን​ተም ይሁዳ! ወደ ጌል​ጌላ አት​ሂድ፤ ወደ ቤት​አ​ዊ​ንም አት​ውጡ፤ በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ማሉ። 16እስ​ራ​ኤል እን​ደ​ም​ት​ደ​ነ​ብር ጊደር ደን​ብ​ሮ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰ​ማ​ራ​ዋል። 17እን​ዲ​ሁም ኤፍ​ሬም ከጣ​ዖ​ታት ጋር ተጋ​ጠመ፤ ለራ​ሱም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖረ። 18ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም መረ​ጣ​ቸው፤ ፈጽ​መ​ውም አመ​ነ​ዘሩ፤ በክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም#ዕብ. “ከክ​ብ​ራ​ቸው ይልቅ” ይላል። ውር​ደ​ትን መረጡ። 19አንተ በክ​ን​ፎ​ችዋ ውስጥ የነ​ፋስ መና​ወጥ ነህ፤ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ያፍ​ራሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ