የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 24

24
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በም​ድር ላይ
1እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለ​ምን ያጠ​ፋ​ታል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ይገ​ለ​ብ​ጣ​ት​ማል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ይበ​ት​ናል። 2ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪ​ያ​ውም እንደ ጌታው ባሪ​ያ​ይ​ቱም እንደ እመ​ቤቷ፥ የሚ​ሸ​ጠ​ውም እን​ደ​ሚ​ገ​ዛው፥ ተበ​ዳ​ሪ​ውም እንደ አበ​ዳ​ሪው፥ ዕዳ ከፋ​ዩም እንደ ዕዳ አስ​ከ​ፋዩ ይሆ​ናል። 3እነሆ፥ ምድር መፈ​ታ​ትን ትፈ​ታ​ለች፤ ፈጽ​ማም ትበ​ረ​በ​ራ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። 4ምድ​ርም አለ​ቀ​ሰች፤ ጠፋ​ችም፤ ዓለም ተገ​ለ​በ​ጠች፤ የም​ድ​ርም ታላ​ላ​ቆች አለ​ቀሱ። 5ምድ​ርም በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ምክ​ን​ያት በደ​ለች፤ ሕጉን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ለው​ጠ​ዋ​ልና፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙ​ንም ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና። 6ስለ​ዚህ ምድር ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ በም​ድር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ይቸ​ገ​ራሉ፤ ጥቂት ሰዎ​ችም ይቀ​ራሉ። 7የወ​ይን ጠጅ አለ​ቀ​ሰች፤ የወ​ይን ግንድ ደከ​መች፤ ልባ​ቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ። 8የከ​በ​ሮ​አ​ቸው ደስታ አል​ቆ​አል፤ መታ​ጀ​ራ​ቸ​ውም አል​ቃ​ለች፤#“መታ​ጀ​ራ​ቸው አል​ቃ​ለች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የኃ​ጥ​ኣን ሀብት አል​ቆ​አል፤ የመ​ሰ​ንቆ ድም​ፅም ቀር​ቶ​አል። 9ወይ​ንን የሚ​ጠ​ጡት አፈሩ፤ የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም ለሚ​ጠ​ጡት መራራ ሆነ። 10ከተ​ሞች ሁሉ ምድረ በዳ ሆኑ፤ ቤቶ​ችም ሁሉ ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ባ​ባ​ቸው ተዘጉ። 11ስለ ወይ​ኑም ጠጅ በአ​ደ​ባ​ባይ አል​ቅሱ፤ የም​ድር ደስታ ሁሉ ጨል​ሞ​አ​ልና፥ የም​ድ​ርም ሐሤት ፈል​ሶ​አ​ልና። 12ከተ​ሞ​ችም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ቤቶ​ችም ባዶ ሆነው ይቀ​ራሉ፤ ይጠ​ፋ​ሉም። 13ይህ ሁሉ በሀ​ገር ውስጥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይሆ​ናል። የወ​ይራ ፍሬ ለቀማ ባለቀ ጊዜ በቃ​ር​ሚ​ያው ውስጥ የወ​ይራ ፍሬ እን​ደ​ሚ​ለ​ቀም እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይቃ​ር​ሟ​ቸ​ዋል።
14እነ​ዚህ ድም​ፃ​ቸ​ውን ያነ​ሣሉ፤ በም​ድር የቀ​ሩ​ትም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የባ​ሕ​ርም ውኃ ይና​ወ​ጣል። 15ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በባ​ሕር ደሴ​ቶች ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይከ​ብ​ራል።
16የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ የጻ​ድ​ቁን ድንቅ ተስፋ ከም​ድር ዳርቻ ሰም​ተ​ናል። እነ​ርሱ ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለሚ​ያ​ፈ​ርሱ ወን​ጀ​ለ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” አሉ። 17በም​ድር ላይ በሚ​ኖሩ፥ ፍር​ሀ​ትና ገደል ወጥ​መ​ድም አሉ። 18የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፍ​ተ​ዋ​ልና፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ከፍ​ር​ሀት ድምፅ የሸሸ በገ​ደል ይወ​ድ​ቃል፤ ከገ​ደ​ልም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል። 19ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ታወ​ከ​ችም፤ ምድር ጐሰ​ቈ​ለች፤ ተነ​ዋ​ወ​ጠ​ችም። 20ምድር በወ​ይን እንደ ሰከረ ሰው ትን​ገ​ዳ​ገ​ዳ​ለች፤ እንደ ዳስም ትወ​ዛ​ወ​ዛ​ለች፤ ሕግን መተ​ላ​ለ​ፍ​ዋም ይከ​ብ​ድ​ባ​ታል፤ ትወ​ድ​ቅ​ማ​ለች፤ ደግ​ማም አት​ነ​ሣም።
21በዚ​ያም ቀን እን​ደ​ዚህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትና በም​ድር ነገ​ሥ​ታት ላይ እጁን ይጥ​ላል። 22እነ​ር​ሱም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ተዘ​ግ​ቶ​ባ​ቸ​ውም በግ​ዞት ቤት ይኖ​ራሉ፤ ከብዙ ትው​ል​ድም በኋላ ይጐ​በ​ኛሉ። 23ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ