የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 25

25
የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ። 2ከተ​ሞ​ችን ትቢያ አደ​ረ​ግህ፤ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መሠ​ረት አፈ​ረ​ስህ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሠ​ሩም። 3ስለ​ዚህ ድሆች ወገ​ኖች ያከ​ብ​ሩ​ሃል፤ የተ​ገፉ ሰዎች ከተ​ሞ​ችም ያከ​ብ​ሩ​ሃል። 4ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው። 5ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ል​ፈህ ከሰ​ጠ​ኸን ከኃ​ጥ​ኣን ሰዎች የተ​ነሣ በጽ​ዮን እንደ ተጠሙ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን እን​ዳጡ ሰዎች ሆነ​ናል።
6የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ። 7በዚ​ህም ተራራ ላይ ይህን ሁሉ ለአ​ሕ​ዛብ ሰጠ፤ ምክሩ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ናትና። 8ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤#ዕብ. “ሞት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ተዋጠ” ይላል። በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።
9በዚ​ያም ቀን፥ “እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድ​ር​ገ​ነ​ዋል፤ ያድ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ ነው፤ ጠብ​ቀ​ነ​ዋል፤ በመ​ዳ​ና​ች​ንም ደስ ይለ​ናል፤ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን” ይላሉ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጠ​ናል፤ እህ​ልም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ጭድም በጭቃ እን​ደ​ሚ​በ​ራይ እን​ዲሁ ሞዓብ ይረ​ገ​ጣል። 11እርሱ ክፉ እንደ አደ​ረ​ገና እንደ አጠፋ በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነ​ሣል፤ በእ​ር​ሱም ላይ እጁን ያነ​ሣው ስድ​ብን ይሽ​ራል። 12የተ​መ​ሸ​ገ​ው​ንና ከፍ ከፍ ያለ​ው​ንም ቅጥ​ር​ህን ዝቅ ያደ​ር​ገ​ዋል። ያዋ​ር​ደ​ው​ማል፤ ወደ መሬ​ትም እስከ አፈር ድረስ ይጥ​ለ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ