ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 3

3
በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ​ሚ​ደ​ርስ ሁከት
1እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ከይ​ሁዳ ኀይ​ለ​ኛ​ውን ወን​ድና ኀይ​ለ​ኛ​ዋን ሴት፥ የእ​ን​ጃ​ራን ኀይል ሁሉ፥ የው​ኃ​ው​ንም ኀይል ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ 2ኀያ​ሉ​ንም፥ ተዋ​ጊ​ው​ንም፥ ፈራ​ጁ​ንም፥ ነቢ​ዩ​ንም፥ ዐዋ​ቂ​ው​ንም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም፥ 3የአ​ምሳ አለ​ቃ​ው​ንም፥ የተ​ከ​በረ አማ​ካ​ሪ​ው​ንም፥ ጠቢ​ቡ​ንም፥ የአ​ና​ጢ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ፥ አስ​ተ​ዋይ አድ​ማ​ጩ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል። 4በእ​ነ​ርሱ ላይ አለ​ቆ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ ጐል​ማ​ሶ​ችን እሾ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዘባ​ቾ​ችም ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል። 5ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል። 6ሰውም በአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወን​ድ​ሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለ​ቃም ሁን​ልን፥ ምግ​ባ​ች​ንም ከእ​ጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥ 7በዚያ ቀን ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እን​ጀራ ወይም ልብስ የለ​ኝ​ምና ለሕ​ዝቡ አለቃ አል​ሆ​ንም”#ዕብ. “ባለ መድ​ኀ​ኒት አል​ሆ​ንም” ይላል። ብሎ መለ​ሰ​ለት። 8ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ ይሁ​ዳም ወድ​ቃ​ለ​ችና፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዐመ​ፅን ስለ​ሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ዘ​ዙም። 9ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰዶም ያወ​ራሉ ይገ​ል​ጡ​አ​ት​ማል” ይላል። 10ክፉ ምክ​ርን መክ​ረ​ዋ​ልና ለነ​ፍ​ሳ​ቸው ወዮ​ላት! እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጻድ​ቁን እን​ሻ​ረው፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ሰ​ረው” ይላል። ሸክም ሆኖ​ብ​ና​ልና፤” ስለ​ዚህ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ፍሬ ይበ​ላሉ። 11እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል። 12ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥ​ዎ​ቻ​ችሁ ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል፤ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ሴቶ​ችም በላ​ያ​ችሁ ይሠ​ለ​ጥ​ኑ​ባ​ች​ኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ችሁ ያስ​ቱ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋሉ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ እን​ደ​ሚ​ፈ​ርድ
13ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ለፍ​ርድ ይነ​ሣል፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሊፈ​ርድ ይነ​ሣል። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ለፍ​ርድ ይመ​ጣል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፥ “ወይ​ኔን አቃ​ጥ​ላ​ች​ኋል፤ ከድ​ሃው የበ​ዘ​በ​ዛ​ች​ሁ​ትም በቤ​ታ​ችሁ አለ፤ 15ሕዝ​ቤ​ንስ ለምን ትገ​ፋ​ላ​ችሁ? የድ​ሃ​ውን ፊትስ ለምን ታሳ​ፍ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ?”
ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴቶች የተ​ሰጠ ማስ​ጠ​ን​ቀ​ቂያ
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፥ “የጽ​ዮን ቆነ​ጃ​ጅት ኰር​ተ​ዋ​ልና፥ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን እያ​ሰ​ገጉ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም እያ​ጣ​ቀሱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ረ​ገዱ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እየ​ጐ​ተቱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ማቱ ይሄ​ዳ​ሉና፤ 17ስለ​ዚህ ጌታ የጽ​ዮን ታላ​ላቅ ሴቶች ልጆ​ችን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ይገ​ል​ጣል። 18በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ግር አል​ቦ​ውን ክብር፥ መር​በ​ቡ​ንም፥ ጨረቃ የሚ​መ​ስ​ለ​ው​ንም ጌጥ፥ 19የጆሮ እን​ጥ​ል​ጥ​ሉ​ንም፥ አን​ባ​ሩ​ንም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ው​ንም፥ ቀጸ​ላ​ው​ንም፥ 20ሰን​ሰ​ለ​ቱ​ንም፥ መቀ​ነ​ቱ​ንም፥ የሽ​ቱ​ው​ንም ዕቃ፥ አሸ​ን​ክ​ታ​ቡ​ንም፥ 21የእ​ጅና የአ​ፍ​ንጫ ቀለ​በ​ቱ​ንም፥ 22የዓ​መት በዓ​ል​ንም ልብስ፥ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም፥ ልግ​ም​በ​ገ​ላ​ው​ንም፥ ከረ​ጢ​ቱ​ንም፥ 23መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል። 24እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁ​ን​ብሽ፤ በወ​ርቅ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸ​ላ​ሽም ፋንታ ቡሃ​ነት ይው​ጣ​ብሽ፤ በሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ። 25የም​ት​ወ​ጂው ትልቁ ልጅሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ኀያ​ላ​ን​ሽም በው​ጊያ ይወ​ድ​ቃሉ። 26የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ