ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 4

4
ምዕ​ራፍ 4።
1በዚ​ያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እን​ጀ​ራ​ች​ንን እን​በ​ላ​ለን፤ የገዛ ልብ​ሳ​ች​ን​ንም እን​ለ​ብ​ሳ​ለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰ​ደ​ባ​ች​ን​ንም አር​ቅ​ልን” ብለው አን​ዱን ወንድ ይይ​ዙ​ታል።
ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ገና እን​ደ​ም​ት​ታ​ደስ
2በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል። 3በጽ​ዮን የቀሩ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ረፉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሕ​ይ​ወት የተ​ጻፉ ሁሉ፥ ቅዱ​ሳን ይባ​ላሉ። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴቶች ልጆ​ችና ወን​ዶች ልጆች እድፍ ያጥ​ባ​ልና፥ በፍ​ርድ መን​ፈ​ስና በሚ​ያ​ቃ​ጥል መን​ፈ​ስም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ደምን ያነ​ጻ​ልና። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ጣል፤ በጽ​ዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌ​ሊ​ትም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል የእ​ሳት ብር​ሃን ይጋ​ር​ዳል፤ በክ​ብ​ርም ሁሉ ላይ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል። 6ከሙ​ቀት ለጥላ፥ ከዐ​ውሎ ነፋ​ስና ከዝ​ና​ብም ለመ​ጠ​ጊ​ያና ለመ​ሸ​ሸ​ጊያ ጎጆ ይሆ​ናል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ