ትንቢተ ኢሳይያስ 5
5
ስለ ወይን ቦታ የተነገረ መዝሙር
1አሁን የወይኔን ቦታ በተመለከተ የወዳጄን መዝሙር ለወዳጄ እዘምራለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ቦታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። 2አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤#በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በግእዝ የለም። ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
3አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፥ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ። 4ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ጠበቅሁት፤ ነገር ግን እሾህን አፈራ። 5አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል። 6ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ። 7የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
8ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው! 9ይህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰምቶአልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆናሉ፤ ታላላቅና የሚያምሩ ቤቶችም የሚቀመጥባቸው አይኖርም። 10ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
11በጥዋት ወደ መሸታ ቤት ለሚገሠግሡና በመጠጥ ቤት ለሚውሉ ወዮላቸው! ወይኑ ያቃጥላቸዋልና። 12በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
13ስለዚህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግዚአብሔርን አላወቁትምና፤ ብዙዎቹ በረኃብና በውኃ ጥም ሞቱ፤ 14ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ። 15ታናሹ ሰውም ይጐሰቍላል፤ ታላቁ ሰውም ይዋረዳል፤ የትዕቢተኞችም ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ 16የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍርድ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ በጽድቅ ይከብራል። 17የተማረኩ እንደ በሬዎች ይሰማራሉ፤ የተረሱትም ምግባቸውን ሲፈልጉ እንደ በግ ጠቦቶች በማሰማርያቸው ይሰማራሉ።
18በደልን እንደ ረዥም ገመድ ለሚስቡ፥ ኀጢአትንም እንደ በሬ ቀንበር ለሚያስሩ ወዮላቸው! 19“እናይ ዘንድ፥ ሥራውን ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮላቸው!
20ክፉውን መልካም መልካሙንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
21ለክፋት ጥበበኞች ለሆኑ፥ እኛ ጠቢባን ነን ለሚሉም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በራሳቸው ጥበበኞች በራሳቸውም አስተዋዮች” ይላል። ወዮላቸው!
22የወይን ጠጅ ለሚጠጡ ኀያላን፥ የሚያሰክረውንም መጠጥ ለሚደባልቁ ጽኑዓን ወዮላቸው! 23በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!
24ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና። 25ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
26በሩቅ ላሉ አሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ። 27አይራቡም፤ አይጠሙምም፤#“አይጠሙም” የሚለው በግእዝ ብቻ። አይደክሙም፤ አይተኙም፤ የወገባቸውን መታጠቂያ አይፈቱም፤ የጫማቸውም ማዘቢያ አይበጠስም። 28ፍላጾቻቸው ተስለዋል፤ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል። 29ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ይቆማሉ፤ ከጕድጓዱ እንደሚወጣ አውሬም ይነጥቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ የሚድንም የለም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እርሱም ያስወጣቸዋል ፤ የሚያድናቸውም የለም” ይላል። 30በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፤ ወደ ምድርም ይመለከታሉ፤ ድቅድቅ ጨለማን ያያሉ፤ ይጨነቃሉም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 5: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ