ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 6

6
የኢ​ሳ​ይ​ያስ ለነ​ቢ​ይ​ነት መጠ​ራት
1ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ዖዝ​ያን በሞ​ተ​በት ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ዥ​ምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ አየ​ሁት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ቤቱን ሞል​ቶት ነበር። 2ሱራ​ፌ​ልም በዙ​ሪ​ያው ቆመው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ስድ​ስት ክንፍ ነበ​ረው፤ በሁ​ለቱ ክን​ፎ​ቻ​ቸው ፊታ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ይበ​ርሩ ነበር። 3አን​ዱም ለአ​ንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምድር ሁሉ ከክ​ብሩ ተሞ​ል​ታ​ለች” እያለ ይጮኽ ነበር። 4የመ​ድ​ረ​ኩም መሠ​ረት ከጩ​ኸ​ታ​ቸው ድምፅ የተ​ነሣ ተና​ወጠ፤ ቤቱ​ንም ጢስ ሞላ​በት። 5እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።
6ከሱ​ራ​ፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤ በእ​ጁም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በጕ​ጠት የወ​ሰ​ደው ፍም ነበረ። 7አፌ​ንም ዳሰ​ሰ​በ​ትና፥ “እነሆ፥ ይህ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህን ነክ​ቶ​አል፤ በደ​ል​ህም ከአ​ንተ ተወ​ገደ፤ ኀጢ​አ​ት​ህም ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለኝ። 8የጌ​ታ​ንም ድምፅ፥ “ማንን እል​ካ​ለሁ? ማንስ ወደ​ዚያ ሕዝብ ይሄ​ድ​ል​ናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነ​ሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ። 9እር​ሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፥ አታ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፥ አት​መ​ለ​ከ​ቱ​ምም” በላ​ቸው አለኝ። 10እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው፥#ዕብ. “በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ይ​ፈ​ወሱ የዚ​ያን ሕዝብ ልብ አደ​ን​ድን ፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አደ​ን​ቍር ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ጨፍን አለኝ” ይላል። ልባ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፍ​ነ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና። 11እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤” 12ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን ያር​ቃል፤ በም​ድ​ርም የቀ​ሩት ይበ​ዛሉ።#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን እስ​ኪ​ያ​ርቅ በም​ድ​ርም መካ​ከል ውድ​ማው መሬት እስ​ኪ​በዛ ድረስ ነው” ይላል። 13በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ዐሥ​ረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ቅጠ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በረ​ገፉ ጊዜ እንደ ግራ​ርና እንደ ኮም​በል ዛፍ ሁነው ይቀ​ራሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ