የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 47

47
የባ​ቢ​ሎን ውድ​ቀት
1አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ። 2ወፍጮ ወስ​ደሽ ዱቄ​ትን ፍጪ፤ ክን​ብ​ን​ብ​ሽን ግለጪ፤ ሽበ​ትሽ ይታይ፤#ዕብ. “ረዥ​ሙን ልብ​ስ​ሽን አው​ል​ቀሽ ጣዪው” ይላል። ባት​ሽን ግለጪ፤ ወን​ዙ​ንም ተሻ​ገሪ። 3ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።#ዕብ. “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ ፤ ለማ​ንም አል​ራ​ራም” ይላል። 4ታዳ​ጊሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ስሙ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው። 5የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፥ “የመ​ን​ግ​ሥ​ታት እመ​ቤት” አት​ባ​ዪ​ምና በድ​ን​ጋጤ ዝም ብለሽ ተቀ​መጪ፤ ወደ ጨለ​ማም ውስጥ ግቢ። 6በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል። 7አን​ቺም፥ “እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እመ​ቤት እሆ​ና​ለሁ” ብለ​ሻል፤ ይህ​ንም በል​ብሽ አላ​ሰ​ብ​ሽም፤ ፍጻ​ሜ​ው​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ስ​ሽም።
8አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤ 9አሁን ግን በአ​ንድ ቀን እነ​ዚህ ሁለት ነገ​ሮች በድ​ን​ገት ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ትና መበ​ለ​ት​ነት ስለ መተ​ቶ​ችሽ ብዛ​ትና ስለ አስ​ማ​ቶ​ችሽ ጽናት ፈጽ​መው ይመ​ጡ​ብ​ሻል። 10በክ​ፋ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ አንቺ ግን፥ “እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻል፤ በዝ​ሙ​ትሽ ኀፍ​ረት ያሰ​ብ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ፤ በል​ብሽ፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻ​ልና። 11ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።
12ምና​ል​ባ​ትም ሊያ​ድ​ንሽ የሚ​ችል እንደ አለ፥ ከአ​ስ​ማ​ቶ​ች​ሽና ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ከተ​ማ​ር​ሽው ከመ​ተ​ቶ​ችሽ ብዛት ጋር ቁሚ። 13በክፉ ምክ​ርሽ ደክ​መ​ሻል፤ አሁ​ንም የሰ​ማ​ይን ከዋ​ክ​ብት የሚ​ቈ​ጥሩ፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከቱ ይነሡ፤ ያድ​ኑ​ሽም፤ ምን እን​ደ​ሚ​መ​ጣ​ብ​ሽም ይን​ገ​ሩሽ፤#ዕብ. “በየ​መ​ባ​ቻው የሚ​መ​ጣ​ውን” ይላል። 14እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ከነ​በ​ል​ባል ኀይል አያ​ድ​ኑም፤ እንደ እሳ​ትም ፍም ይሆ​ኑ​ብ​ሻል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።#ዕብ. “እርሱ ሰው እን​ደ​ሚ​ሞ​ቀው ፍም ወይም በፊቱ ሰው እን​ደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት እሳት ያለ አይ​ደ​ለም” ይላል። 15እነ​ርሱ ረዳ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ደከ​ምሽ፤ ሰው በራሱ ይሳ​ሳ​ታል፤ ለአ​ንቺ ግን መድ​ኀ​ኒት የለ​ሽም።#ዕብ. “የደ​ከ​ም​ሽ​ባ​ቸው ነገ​ሮች እን​ዲህ ይሆ​ኑ​ብ​ሻል ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ከአ​ንቺ ጋር ይነ​ግዱ የነ​በሩ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይሄ​ዳሉ ፤ የሚ​ያ​ድ​ን​ሽም የለም” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ