ትንቢተ ኢሳይያስ 48
48
እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረና ሁሉን የሚያውቅ ስለ መሆኑ
1እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፥ ከይሁዳም የወጣችሁ፥ በእውነት ሳይሆን፥ በጽድቅም ሳይሆን እርሱን እየጠራችሁ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤ 2በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ ይህን ስሙ። 3የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌም ወጥቶአል፤ ድንገትም ያደረግሁት ምስክር ሆኖአል፤ እርሱም ተፈጽሞአል።
4አንተ እልከኛ፥ አንገትህም የብረት ጅማት፥ ግንባርህም ናስ እንደ ሆነ ዐውቄአለሁ፤ 5ስለዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፤ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌም ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ የሚሆነውን ከመሆኑ በፊት ነገርሁህ፤ አስረዳሁህም፤ 6ሁሉን ሰምተሃሃል፤ አላወቅህም፤ ከዛሬ ጀምሮ የሚሆነውን አዲስ ነገር ገለጥሁልህ። 7እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፥ “እነሆ፥ ዐውቄአቸዋለሁ” እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም። 8አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና። 9ስለ ስሜ ቍጣዬን አሳይሃለሁ፤#ዕብ. “አዘገያለሁ” ይላል። እንዳላጠፋህም ግርማዬን አመጣብሃለሁ።#ዕብ. “ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ” ይላል። 10እነሆ፥ ለወጥሁህ፤ ነገር ግን በብር አይደለም፤ ከመከራም እቶን አውጥቼሃለሁ። 11ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ ይህን ለአንተ አደርገዋለሁ፤ ስሜ ተነቅፎአልና፤ ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም።
12ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ፤ እኔም ዘለዓለማዊ ነኝ። 13እጄም ምድርን መሥርታለች፤ ቀኜም ሰማያትን አጽንታለች፤ እጠራቸዋለሁ፤ በአንድነትም መጥተው ይቆማሉ። 14ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ይሰማሉ፤ ይህን ማን ነገራቸው? አንተን በመውደድ የከለዳውያንን ዘር#ዕብ. “ክንዱ በከለዳውያን ላይ ይሆናል” ይላል። አስወግድ ዘንድ ፈቃድህን በባቢሎን ላይ አደረግሁ። 15እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፤ መንገዱም ትከናወንለታለች። 16ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፤ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
17ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ የምትሄድባትንም መንገድ እንዴት እንደምታገኝ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። 18ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤ 19ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁንም ስምህ ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።
20ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ። 21በምድረ በዳም በተጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓለቱ ውስጥ ያፈልቅላቸው ነበር፤ ዓለቱም ተሰነጠቀ፤ ውኃውም ይፈስስላቸው ነበር፤ ሕዝቤም ይጠጡ ነበር።#“ሕዝቤም ይጠጡ ነበር” የሚለው በዕብ. የለም። 22እንግዲህ ኃጥኣን ደስታ አያደርጉም፤#ዕብ. “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል። ይላል እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 48: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ