ትንቢተ ኢሳይያስ 49
49
እስራኤል የአሕዛብ ብርሃን
1ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተም አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ከረዥም ዘመን በኋላ እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፤ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠርቶአል፤ 2አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፤ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፤ በሰገባው ውስጥም ሸሽጎኛል። 3እርሱም፥ “እስራኤል ሆይ፥ አንተ ባርያዬ ነህ፤ በአንተም እከበራለሁ” አለኝ። 4እኔ ግን፥ “በከንቱ ደከምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ይፈርድልኛል፤ መከራዬም በአምላኬ ፊት ነው” አልሁ።
5አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፥ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባርያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የፈጠረኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። 6እርሱም፥ “የያዕቆብን ነገዶች እንደገና እንድታስነሣ፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ወደ አባቶች ቃል ኪዳን እንድትመልስ ባርያዬ ትሆን ዘንድ ለአንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ይላል። 7ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
የእስራኤል ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ
8እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ፤ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትን ርስቶች ትወርስ ዘንድ፤ 9የተጋዙትንም፦ ውጡ፤ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ተገለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመንገድም ሁሉ ላይ ይሰማራሉ፤ ማሰማሪያቸውም በጥርጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆናል። 10የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም። 11ተራሮችንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጎዳናዎችም ሁሉ መሰማርያ ይሆናሉ። 12እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ከፋርስ ሀገር ይመጣሉ። 13እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
14ጽዮን ግን፥ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ ጌታም ረስቶኛል” አለች። 15“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም። 16እነሆ፥ እኔ በእጄ ግንቦችሽን ሣልሁ፤ አንቺም ሁልጊዜ በፊቴ ነሽ። 17ከአፈረሱሽ በኋላ ፈጥነሽ ትታነጺያለሽ፤#ዕብ. “ልጆችሽ ይፈጥናሉ” ይላል። ያፈረሱሽ ከአንቺ ይወጣሉ። 18ዐይንሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ ይላል እግዚአብሔር። 19ፈርሰሻልና፥ ፈጽመሽም ጠፍተሻልና በአንቺ ለሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆኚባቸዋለሽ፤ ያጠፉሽም ከአንቺ ይርቃሉ። 20አጥተሻቸው የነበሩት ልጆችሽም በጆሮሽ፦ ስፍራ ጠብቦናልና የምንቀመጥበት ቦታ አስፊልን ይላሉ። 21አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም መበለት ነኝና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?” ትያለሽ።
22ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፤ ዓርማዬንም ወደ ደሴቶች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ታቅፈው ያመጡአቸዋል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። 23ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”#ግእዙ “ከእንግዲህ ወዲያ አታፍሪም” ይላል።
24በውኑ ምርኮን ከኀይለኛ እጅ መቀማት ይቻላልን? በግፍ የተማረከስ ይድናልን? 25እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፥ “በኀያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፤ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ እኔም ፍርድሽን እፈርድልሻለሁ፤#ዕብ. “ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ” ይላል። ልጆችሽንም አድናለሁ። 26የአስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን ይበላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኀኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብን ኀይል የምደግፍ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 49: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ