ትንቢተ ኢሳይያስ 50
50
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች። 2እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ። 3ሰማይን በጨለማ እሸፍነዋለሁ፤ መጋረጃውንም ማቅ አደርጋለሁ።”
4የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል። 5የጌታ የእግዚአብሔር ተግሣጽም ጆሮዬን ከፍቶአል፤ እኔም ዐመፀኛ አልነበርሁም፤ አልተከራከርሁም። 6ጀርባዬን ለግርፋት፥ ጕንጬንም ለጽፍዐት ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከምራቅ ኀፍረት አልመለስሁም። 7ጌታ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ ስለዚህም አላፈርሁም፤ ፊቴንም እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፤ እንዳላፍርም አውቃለሁ። 8የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚከራከረኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ። 9እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይጎዳኛል? እነሆ፥ ሁላችሁ እንደ ልብስ ታረጃላችሁ፤ ብልም ይበላችኋል።
10ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤ 11እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 50: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ