የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 49

49
እስ​ራ​ኤል የአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን
1ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤ 2አፌ​ንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድ​ር​ጎ​አል፤ በእጁ ጥላ ሰው​ሮ​ኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላ​ጻም አድ​ር​ጎ​ኛል፤ በሰ​ገ​ባው ውስ​ጥም ሸሽ​ጎ​ኛል። 3እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አንተ ባር​ያዬ ነህ፤ በአ​ን​ተም እከ​በ​ራ​ለሁ” አለኝ። 4እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።
5አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከብ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ አም​ላ​ኬም ጕል​በት ሆኖ​ኛ​ልና ያዕ​ቆ​ብን ወደ እርሱ እን​ድ​መ​ልስ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ እርሱ እን​ድ​ሰ​በ​ስብ ባርያ እሆ​ነው ዘንድ ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ የፈ​ጠ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል። 6እር​ሱም፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ነገ​ዶች እን​ደ​ገና እን​ድ​ታ​ስ​ነሣ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ወደ አባ​ቶች ቃል ኪዳን እን​ድ​ት​መ​ልስ ባር​ያዬ ትሆን ዘንድ ለአ​ንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ይላል። 7ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”
የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መመ​ለስ
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ዕለት ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ድኅ​ነት በሚ​ደ​ረ​ግ​በ​ትም ቀን ረድ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ቃል ኪዳን አድ​ርጌ ለሕ​ዝቡ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆ​ኑ​ትን ርስ​ቶች ትወ​ርስ ዘንድ፤ 9የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም፦ ውጡ፤ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን፦ ተገ​ለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመ​ን​ገ​ድም ሁሉ ላይ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በጥ​ር​ጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆ​ናል። 10የሚ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም ያጽ​ና​ና​ቸ​ዋ​ልና፥ በውኃ ምን​ጮ​ችም በኩል ይመ​ራ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙም፤ የፀ​ሐይ ትኩ​ሳ​ትም አይ​ጐ​ዳ​ቸ​ውም። 11ተራ​ሮ​ች​ንም ሁሉ መን​ገድ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጎዳ​ና​ዎ​ችም ሁሉ መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ናሉ። 12እነሆ፥ እነ​ዚህ ከሩቅ፥ እነ​ሆም፥ እነ​ዚህ ከሰ​ሜ​ንና ከም​ዕ​ራብ፥ እነ​ዚ​ህም ከፋ​ርስ ሀገር ይመ​ጣሉ። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ይቅር ብሎ​አ​ልና፥ ከሕ​ዝ​ቡም ችግ​ረ​ኞ​ቹን አጽ​ን​ቶ​አ​ልና። ሰማ​ያት ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ርም ደስ ይበ​ላት፤ ተራ​ሮ​ችም እልል ይበሉ።
14ጽዮን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ኛል፤ ጌታም ረስ​ቶ​ኛል” አለች። 15“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም። 16እነሆ፥ እኔ በእጄ ግን​ቦ​ች​ሽን ሣልሁ፤ አን​ቺም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነሽ። 17ከአ​ፈ​ረ​ሱሽ በኋላ ፈጥ​ነሽ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤#ዕብ. “ልጆ​ችሽ ይፈ​ጥ​ናሉ” ይላል። ያፈ​ረ​ሱሽ ከአ​ንቺ ይወ​ጣሉ። 18ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነ​ዚ​ህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለ​ብ​ሻ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ እንደ ሙሽ​ራም ትጐ​ና​ጸ​ፊ​አ​ቸ​ዋ​ለሽ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 19ፈር​ሰ​ሻ​ልና፥ ፈጽ​መ​ሽም ጠፍ​ተ​ሻ​ልና በአ​ንቺ ለሚ​ኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆ​ኚ​ባ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ ያጠ​ፉ​ሽም ከአ​ንቺ ይር​ቃሉ። 20አጥ​ተ​ሻ​ቸው የነ​በ​ሩት ልጆ​ች​ሽም በጆ​ሮሽ፦ ስፍራ ጠብ​ቦ​ና​ልና የም​ን​ቀ​መ​ጥ​በት ቦታ አስ​ፊ​ልን ይላሉ። 21አን​ቺም በል​ብሽ፦ የወ​ላድ መካን ሆኛ​ለ​ሁና፥ እኔም መበ​ለት ነኝና እነ​ዚ​ህን ማን ወለ​ደ​ልኝ? እነ​ዚ​ህ​ንስ ማን አሳ​ደ​ጋ​ቸው? እነሆ፥ ብቻ​ዬን ቀርቼ ነበር፤ እነ​ዚ​ህስ ከወ​ዴት መጡ?” ትያ​ለሽ።
22ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕ​ዛብ አነ​ሣ​ለሁ፤ ዓር​ማ​ዬ​ንም ወደ ደሴ​ቶች አቆ​ማ​ለሁ፤ ወን​ዶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በብ​ብ​ታ​ቸው ታቅ​ፈው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። 23ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”#ግእዙ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አታ​ፍ​ሪም” ይላል።
24በውኑ ምር​ኮን ከኀ​ይ​ለኛ እጅ መቀ​ማት ይቻ​ላ​ልን? በግፍ የተ​ማ​ረ​ከስ ይድ​ና​ልን? 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በኀ​ያ​ላን የተ​ማ​ረኩ ይወ​ሰ​ዳሉ፤ የጨ​ካ​ኞ​ችም ብዝ​በዛ ያመ​ል​ጣል፤ እኔም ፍር​ድ​ሽን እፈ​ር​ድ​ል​ሻ​ለሁ፤#ዕብ. “ከአ​ንቺ ጋር የሚ​ጣ​ሉ​ትን እጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” ይላል። ልጆ​ች​ሽ​ንም አድ​ና​ለሁ። 26የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽ​ንም ሥጋ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማ​ቸ​ውን ጠጥ​ተው ይሰ​ክ​ራሉ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ኀይል የም​ደ​ግፍ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ