ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 58:6-7

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 58:6-7 አማ2000

ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው። ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።