የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 8

8
የኢ​ሳ​ይ​ያስ ልጅ ለሕ​ዝቡ የም​ርኮ ምል​ክት እንደ ሆነ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ታላቅ አዲስ ሰሌዳ ወስ​ደህ፦ ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ በሰው ብርዕ ጻፍ​በት። 2የታ​መ​ኑ​ትን ሰዎች ካህ​ኑን ኦር​ያ​ንና የበ​ራ​ክ​ዩን ልጅ ዘካ​ር​ያ​ስን ምስ​ክ​ሮች አድ​ር​ግ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አድ​ሮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤”#“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አድ​ሮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 3ወደ ነቢ​ዪ​ቱም ቀረ​ብሁ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስሙን ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ ጥራው። 4ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፦ 6“እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና። 7ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ቱና ብዙ የሆ​ነ​ውን የወ​ንዝ ውኃ፥ የአ​ሦ​ርን ንጉ​ሥና ክብ​ሩን ሁሉ ያመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዙም ሞልቶ ይወ​ጣል፤ በዳ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ 8ከይ​ሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ ኀያ​ላ​ኑ​ንም ይጨ​ር​ሳል፤ ሰፈ​ሩም በሰ​ፊው ምድ​ርና በሀ​ገ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይሞ​ላል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።#ዕብ. “እየ​ጐ​ረ​ፈም ወደ ይሁዳ ይገ​ባል፥ እያ​ጥ​ለ​ቀ​ለ​ቀም ያል​ፋል፥ እስከ አን​ገ​ቱም ይደ​ር​ሳል፥ አማ​ኑ​ኤል ሆይ የክ​ንፉ መዘ​ር​ጋት የሀ​ገ​ር​ህን ስፋት ትሞ​ላ​ለች” ይላል።
9አሕ​ዛብ ሆይ፥ ዕወ​ቁና ደን​ግጡ፤ እስከ ምድር ዳር​ቻም ስሙ፤ ኀያ​ላን! ድል ሁኑ፤ ዳግ​መ​ኛም ብት​በ​ረቱ እንደ ገና ድል ትሆ​ና​ላ​ችሁ። 10ምክ​ርን ብት​መ​ክ​ሩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ራ​ች​ሁን ይለ​ው​ጣል፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ትም ነገር አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና። 11የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ እን​ዲህ ተና​ገ​ረኝ፤ በዚ​ህም ሕዝብ መን​ገድ እን​ዳ​ል​ሄድ አስ​ጠ​ነ​ቀ​ቀኝ፤ 12እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚ​ለ​ውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አት​በሉ፤ መፈ​ራ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም። 13ነገር ግን የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀድ​ሱት፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ሁም እርሱ ይሁን። 14ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።#ዕብ. “እር​ሱም ለመ​ቅ​ደስ ይሆ​ናል ፤ ነገር ግን ለሁ​ለቱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤቶች ለዕ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋ​ይና ለማ​ሰ​ና​ከያ ዓለት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖሩ ለወ​ጥ​መ​ድና ለአ​ሽ​ክላ ይሆ​ናል ፤” ይላል። 15ስለ​ዚ​ህም ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ ይወ​ድ​ቁ​ማል፤ ይሰ​በ​ሩ​ማል፤ ይጠ​መ​ዱ​ማል፤ ይያ​ዙ​ማል።”
16እን​ዳ​ይ​ማ​ሩ​አት ሕግን የሚ​ያ​ጠ​ፉ​አት ሰዎች ያን​ጊዜ ይገ​ለ​ጣሉ።#ዕብ. “ምስ​ክ​ሩን እሰር ፤ በደቀ መዛ​ሙ​ር​ቶች መካ​ከል ሕጉን አትም” ይላል። 17ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ፊቱን የመ​ለ​ሰ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፥ እተ​ማ​መ​ን​በ​ት​ማ​ለሁ። 18እነሆ፥ እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል በጽ​ዮን ተራራ ከሚ​ኖ​ረው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ነን።
19እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን? 20ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና። 21በዚ​ህም በር​ግጥ ጽኑ ረኃብ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋል፤ በተ​ራ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በአ​ለ​ቆ​ችና በመ​ኳ​ን​ን​ቱም ላይ ክፉ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ። 22ወደ ታችም ወደ ምድር ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማ​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ታላቅ መከ​ራ​ንም ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትቸ​ገ​ራ​ላ​ች​ሁም፤ በፊ​ታ​ች​ሁም ጨለማ ይሆ​ናል፤ አታ​ዩ​ምም፤ በመ​ከ​ራም ያለ ጊዜው እስ​ኪ​ደ​ርስ አይ​ድ​ንም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ