የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 9

9
ስለ​ሚ​መ​ጣው ንጉሥ
1የዚ​ህም ጊዜው እስ​ከ​ሚ​ደ​ርስ የተ​ቸ​ገ​ረው ሁሉ አያ​መ​ል​ጥም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዘመን የዛ​ብ​ሎ​ን​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምን ምድር አቃ​ለለ፤ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ግን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር መን​ገድ ያለ​ውን የአ​ሕ​ዛ​ብን ገሊላ ያከ​ብ​ራል። 2በጨ​ለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብር​ሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨ​ለማ ሀገ​ርም ለነ​በሩ ብር​ሃን ወጣ​ላ​ቸው። 3ብዙ ሕዝ​ብን በደ​ስታ አወ​ረ​ድህ፤ በመ​ከር ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው፥ ምር​ኮ​ንም እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ በፊ​ትህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 4በም​ድ​ያም ጊዜ እንደ ሆነ በላ​ያ​ቸው የነ​በ​ረው ቀን​በር ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና፥ በጫ​ን​ቃ​ቸው የነ​በ​ረ​ው​ንም፥ የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ንም በትር መል​ሶ​አ​ልና። 5በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በማ​ታ​ለል የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ልብስ ሁሉ ይመ​ል​ሳሉ ፤ በለ​ው​ጡም ልብ​ስን ይቀ​በ​ላሉ በእ​ሳ​ትም ሊያ​ቃ​ጥ​ሉት ይወ​ድ​ዳሉ” ይላል። 6ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤ 7ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።
8ጌታ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ሞትን#ዕብ. “ቃልን” ይላል። ላከ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ወደቀ። 9የኤ​ፍ​ሬም ሕዝብ ሁሉና በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖሩ ያው​ቃሉ፤ በት​ዕ​ቢ​ትና በልብ ኵራ​ትም እን​ዲህ ይላሉ፦ 10“ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።” 11ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል። 12ጠላ​ቶ​ቹን ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ሥ​ራቅ፥ አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ዕ​ራብ ያን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​በ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ከ​ፈተ አፍ ይበ​ሉ​ታል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።
13ሕዝቡ ግን እስ​ከ​ተ​ቀ​ሠፉ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ የሠ​ራ​ዊ​ት​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉም። 14ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ​ንና ጅራ​ትን፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን በአ​ንድ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ይቈ​ር​ጣል። 15ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው። 16ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ 17ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።
18ኀጢ​አት እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ እሳት እንደ በላ​ችው ደረቅ ሣር ይቃ​ጠ​ላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃ​ጠ​ላል፤ በተ​ራ​ራ​ዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃ​ጠ​ላል። 19በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃ​ጠ​ላ​ለች፤ ሕዝ​ቡም እሳት እን​ደ​ሚ​በ​ላው እን​ጨት ሆኖ​አል፤ ሰውም ለወ​ን​ድሙ አይ​ራ​ራም። 20ነገር ግን ሰው ወደ ቀኙ ይመ​ለ​ሳል፤ ይራ​ባ​ልና፤ በግ​ራም በኩል ይበ​ላል፤ አይ​ጠ​ግ​ብ​ምም፤ 21እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የክ​ን​ዱን ሥጋ ይበ​ላል፤ ምናሴ ኤፍ​ሬ​ምን፥ ኤፍ​ሬ​ምም ምና​ሴን ይበ​ላል፤ እነ​ርሱ በአ​ን​ድ​ነት የይ​ሁዳ ጠላ​ቶች ይሆ​ና​ሉና። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ