የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 10

10
ቶላ
1ከአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በኋላ ከይ​ሳ​ኮር ነገድ የሆነ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ዳን ተነሣ፤ እር​ሱም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ በሳ​ምር ተቀ​ምጦ ነበር። 2እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሃያ ሦስት ዓመት ገዛ፤ ሞተም፤ በሳ​ም​ርም ተቀ​በረ።
ኢያ​ዕር
3ከእ​ር​ሱም በኋላ ገለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ኢያ​ዕር ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ። 4በሠ​ላሳ ሁለት#ዕብ. “ሰላሳ” ይላል። የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው። 5ኢያ​ዕ​ርም ሞተ፤ በራ​ሞ​ንም ተቀ​በረ።
የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስለ በደሉ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በአ​ሞ​ና​ው​ያን እጅ እንደ ወደቁ
6የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአ​ራም” ይላል። አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና በአ​ሞን ልጆች እጅም አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 8በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥቃይ አበ​ዙ​ባ​ቸው፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ያሉ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው። 9የአ​ሞ​ንም ልጆች ከይ​ሁዳ፥ ከብ​ን​ያ​ምና ከኤ​ፍ​ሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እጅግ ተጨ​ነቁ።
10የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “አን​ተን አም​ላ​ካ​ች​ንን ትተን በዓ​ሊ​ምን አም​ል​ከ​ና​ልና ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ የአ​ሞ​ንና የሞ​አ​ብም ልጆች፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ 12ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንም፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንም አላ​ስ​ጨ​ነ​ቋ​ች​ሁ​ምን? ወደ እኔም ጮኻ​ችሁ፤ እኔም ከእ​ጃ​ቸው አዳ​ን​ኋ​ችሁ። 13እና​ንተ ግን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደግሞ አላ​ድ​ና​ች​ሁም። 14ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።” 15የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት። 16ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ወ​ገዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ፤ ደስም አሰ​ኙት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሥ​ቃይ የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተው ነበር።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነፍ​ሱም ስለ እስ​ራ​ኤል ጕስ​ቍ​ልና አዘ​ነች” ይላል።
17የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በገ​ለ​ዓድ ሰፈሩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተሰ​ብ​ስ​በው በመ​ሴፋ ሰፈሩ። 18የገ​ለ​ዓድ ሕዝብ አለ​ቆ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር መዋ​ጋ​ትን የሚ​ጀ​ምር ማን ነው? እርሱ በገ​ለ​ዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆ​ናል” አሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ