የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 13

13
የሶ​ም​ሶን ልደት
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አርባ ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።
2ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር። 3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሴ​ቲቱ ተገ​ልጦ እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ድ​ሽም፤ ነገር ግን ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ። 4አሁ​ንም ተጠ​ን​ቀቂ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጪ፤ ርኩ​ስም ነገር አት​ብዪ። 5እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።” 6ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አል​ጠ​የ​ቅ​ሁ​ትም” ይላል። እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም። 7እር​ሱም፦ እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ እን​ግ​ዲህ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥን አት​ጠጪ፥ ርኩስ ነገ​ር​ንም አት​ብዪ፤ ልጁ ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና አለኝ” ብላ ተና​ገ​ረች።
8ማኑ​ሄም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላ​ክ​ኸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው፥ እባ​ክህ እን​ደ​ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ልጅ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ያስ​ገ​ን​ዝ​በን” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የማ​ኑ​ሄን ቃል ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ እንደ ገና በእ​ርሻ ውስጥ ተቀ​ምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእ​ር​ስዋ ጋር አል​ነ​በ​ረም። 10ሴቲ​ቱም ፈጥና ሮጠች ለባ​ል​ዋም፥ “እነሆ፥ አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣው ያ ሰው ደግሞ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ” ብላ ነገ​ረ​ችው። 11ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ። 12ማኑ​ሄም፥ “እነሆ፥ ቃልህ በደ​ረሰ ጊዜ የልጁ ነገሩ፥ ግብ​ሩስ ምን​ድን ነው?” አለው። 13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “ለሚ​ስ​ትህ ከነ​ገ​ር​ኋት ሁሉ ተጠ​በቁ። 14ከወ​ይ​ንም ከሚ​ወ​ጣው ሁሉ አት​ብላ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጣ፤ ርኩ​ስ​ንም ነገር ሁሉ አት​ብላ፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ትን ሁሉ ጠብቁ” አለው።
15ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “የፍ​የል ጠቦት እና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ዘንድ ግድ እን​ል​ሃ​ለን” አለው። 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “አንተ የግድ ብት​ለኝ እህ​ል​ህን አል​በ​ላም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ብታ​ደ​ርግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ር​በው” አለው። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን አላ​ወ​ቀም ነበር። 17ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “ነገ​ርህ በደ​ረሰ ጊዜ እን​ድ​ና​ከ​ብ​ርህ ስምህ ማን ነው” አለው። 18የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ?” አለው። 19ማኑ​ሄም የፍ​የ​ሉን ጠቦ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ወስዶ በድ​ን​ጋይ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​በው። መል​አ​ኩም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ይመ​ለ​ከቱ ነበር። 20ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።
21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዳግ​መኛ ለማ​ኑ​ሄና ለሚ​ስቱ አል​ተ​ገ​ለ​ጠም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን ዐወቀ። 22ማኑ​ሄም ሚስ​ቱን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ተ​ና​ልና ሞትን እን​ሞ​ታ​ለን” አላት። 23ሚስ​ቱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ሊገ​ድ​ለን ቢወ​ድድ ኖሮ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ከእ​ጃ​ችን ባል​ተ​ቀ​በ​ለን፥ ይህ​ንም ነገር ሁሉ ባላ​ሳ​የን፥ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርም በዚህ ጊዜ ባላ​ሰ​ማን ነበር” አለ​ችው።
24ሴቲ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሶም​ሶን ብላ ጠራ​ችው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው፤ ልጁም አደገ። 25የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሶ​ራ​ሕና በእ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ