የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 17

17
ሚካ ያስ​ቀ​ረ​ፃ​ቸው ጣዖ​ቶች
1በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ። 2እና​ቱ​ንም፥ “ከአ​ንቺ ዘንድ የተ​ሰ​ረ​ቀው፥ የረ​ገ​ም​ሽ​በ​ትም፥ በጆ​ሮ​ዬም የተ​ና​ገ​ር​ሽ​በት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስ​ጄው ነበር” አላት። እና​ቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለ​ችው። 3አን​ዱን ሺህ አንድ መቶ ብርም ለእ​ናቱ መለ​ሰ​ላት፤ እና​ቱም፥ “ይህን ብር የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አድ​ርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ለአ​ንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” አለች። 4ለእ​ና​ቱም ገን​ዘ​ቡን መለ​ሰ​ላት እና​ቱም ብሩን ወስዳ ከእ​ርሱ ሁለ​ቱን መቶ ብር ለአ​ን​ጥ​ረኛ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አደ​ረ​ገው። በሚ​ካም ቤት አስ​ቀ​መ​ጡት። 5ሰው​ዬ​ውም ሚካ የአ​ማ​ል​ክት ቤት ነበ​ረው፤ ኤፉ​ድና ተራ​ፊም አደ​ረገ፤ ከል​ጆ​ቹም አን​ዱን ቀደ​ሰው፤ ካህ​ንም ሆነ​ለት። 6በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።
7በይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ከይ​ሁዳ ወገን የሆነ አንድ ጐል​ማሳ ነበረ፤ እር​ሱም ሌዋዊ ነበረ፤ በዚ​ያም ይቀ​መጥ ነበር። 8ይህም ሰው በአ​ገ​ኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይ​ሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚ​ያም ያድር ዘንድ ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ። 9ሚካም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም የሆ​ንሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የም​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ስፍራ ለመ​ሻት እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። 10ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው። 11ሌዋ​ዊ​ዉም ሄደ። ከዚ​ያም ሰው ጋር ይኖር ዘንድ ጀመረ፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ከል​ጆቹ እንደ አንዱ ሆነ​ለት። 12ሚካም ሌዋ​ዊ​ዉን እጁን ቀባው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ካህን ሆነ​ለት፤ በሚ​ካም ቤት ኖረ። 13ሚካም፥ “ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም እን​ዲ​ሠ​ራ​ልኝ አሁን አው​ቃ​ለሁ” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ