የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 18

18
ሚካና የዳን ነገድ
1በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች መካ​ከል ርስት አል​ደ​ረ​ሳ​ቸ​ውም ነበ​ርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ርስት ይሹ ነበር። 2የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ። 3በሚካ ቤትም በነ​በሩ ጊዜ የሌ​ዋ​ዊ​ዉን የጐ​ል​ማ​ሳ​ውን ድምፅ ዐወቁ፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው፥ “ወደ​ዚህ ማን አመ​ጣህ? በዚ​ህስ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድን ነው? በዚ​ህስ ምን አለህ?” አሉት። 4እር​ሱም፥ “ሚካ እን​ዲህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ፤ ቀጠ​ረ​ኝም፤ እኔም ካህን ሆን​ሁ​ለት” አላ​ቸው። 5እነ​ር​ሱም፥ “የም​ን​ሄ​ድ​በት መን​ገድ የቀና መሆ​ኑን እና​ውቅ ዘንድ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይ​ቅ​ልን” አሉት። 6ያም ካህን፥ “የም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነውና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።
7አም​ስ​ቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በው​ስ​ጡም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ተዘ​ል​ለው አዩ​አ​ቸው፤ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐር​ፈው፥ ተዘ​ል​ለ​ውም ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ በተ​መ​ዘ​ገ​በች የር​ስ​ታ​ቸው ምድ​ርም ቃልን መና​ገር አል​ቻ​ሉም፤#ዕብ. “የሚ​ያ​ስ​ቸ​ግ​ራ​ቸው የሚ​ገ​ዛ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም” ይላል። ከሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። 8እነ​ዚ​ያም አም​ስቱ ሰዎች ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ወደ ሶራ​ሕና ወደ እስ​ታ​ሔል ተመ​ለሱ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ “ምን አስ​ቀ​ም​ጦ​አ​ች​ኋል?” አሉ​አ​ቸው። 9እነ​ር​ሱም፥ “ምድ​ሪቱ እጅግ መል​ካም እንደ ሆነች አይ​ተ​ናል፤ ተነሡ፤ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ውጣ፤ እና​ንተ ዝም ትላ​ላ​ች​ሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አት​በሉ። 10በሄ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ ተዘ​ል​ለው ወደ ተቀ​መጡ ሕዝብ ትደ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰፊ ናት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ካለው ነገር ሁሉ አን​ዳች የማ​ይ​ጐ​ድ​ል​ባ​ትን ስፍራ በእ​ጃ​ችሁ ሰጥ​ቶ​አል” አሉ።
11ከዳን ወገ​ንም የጦር ዕቃ የታ​ጠቁ ስድ​ስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከሶ​ራ​ሕና ከእ​ስ​ታ​ሔል ተነ​ሥ​ተው ሄዱ። 12ወጥ​ተ​ውም በይ​ሁዳ ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነ​ሆም፥ ቦታዉ ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም በስ​ተ​ኋላ ነው። 13ከዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ።
14የሌ​ሳን ምድር ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎ​ችም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉ​ድና ተራ​ፊም፥ የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም እን​ዳሉ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?፤ አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ዕወቁ” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው። 15ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት። 16የጦር ዕቃ የታ​ጠ​ቁት፥ ከዳን ልጆ​ችም የሆ​ኑት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆመው ነበር። 17ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎች መጥ​ተው ወደ​ዚያ ገቡ፤ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም የጦር ዕቃ ከታ​ጠ​ቁት ከስ​ድ​ስት መቶ ሰዎች ጋር በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር። 18እነ​ዚ​ህም ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብ​ተው የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን ምስል፥ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም፥ “ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። 19እነ​ር​ሱም፥ “ዝም በል፤ እጅ​ህ​ንም በአ​ፍህ ላይ ጫን፤ ከእ​ኛም ጋር ና፥ አባ​ትና ካህ​ንም ሁን​ልን፤ ለአ​ንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለነ​ገ​ድና ለወ​ገን ካህን መሆን ማና​ቸው ይሻ​ል​ሃል?” አሉት። 20ካህ​ኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ምስል ወሰደ፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ገባ።
21እነ​ር​ሱም ተመ​ል​ሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገን​ዘ​ቡ​ንና ሀብ​ቱ​ንም ሁሉ፥ በፊ​ታ​ቸው አድ​ር​ገው ወሰዱ። 22ከሚ​ካም ቤት ሳይ​ርቁ ሚካና የሚካ ጎረ​ቤ​ቶች ጮኹ፤ የዳ​ን​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​ባ​ቸው።
የዳን ሰዎች በሌሳ እንደ ሰፈሩ
23ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳ​ንም ልጆች ፊታ​ቸ​ውን መል​ሰው ሚካን፥ “የም​ት​ጮ​ኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት። 24እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ። 25የዳ​ንም ልጆች እን​ዲህ አሉት፥ “የተ​ቈጡ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​ህና ነፍ​ስ​ህም፥ የቤተ ሰቦ​ች​ህም ነፍስ እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ብህ፥ ድም​ፅህ በእኛ መካ​ከል አይ​ሰማ።” 26የዳ​ንም ልጆች መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ፤ ሚካም ከእ​ርሱ እንደ በረቱ ባየ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።።
27እነ​ር​ሱም ሚካ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት። 28የሚ​ታ​ደ​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ ከሲ​ዶና ርቀው ነበ​ርና፥ እነ​ር​ሱም ከሌ​ሎች ሰዎች ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና። እር​ስ​ዋም በቤ​ት​ሮ​አብ አጠ​ገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበ​ረች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሠር​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባት። 29ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል በተ​ወ​ለ​ደው በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ስም አስ​ቀ​ድሞ ሌሳ ነበረ። 30የዳ​ንም ልጆች የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን የሚ​ካን ምስል ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ፤ የሙ​ሴም ልጅ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የም​ናሴ ልጅ” ይላል። የጌ​ር​ሳም ልጅ ዮና​ታን፥ እር​ሱና ልጆቹ እስከ ሀገ​ራ​ቸው ምርኮ ድረስ ለዳን ነገድ ካህ​ናት ነበሩ። 31ሚካም ያደ​ረ​ገ​ውን የተ​ቀ​ረፀ ምስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሴሎ ባለ​በት ዘመን ሁሉ አቆሙ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ