መጽሐፈ መሳፍንት 21
21
ብንያማውያን ሚስቶችን እንዲያገኙ የተደረገ ምክር
1የእስራኤልም ሰዎች፥ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያም ልጆች በጋብቻ አይስጥ” ብለው በመሴፋ ተማማሉ። 2ሕዝቡም ወደ ቤቴል መጥተው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ጽኑዕ ልቅሶ አለቀሱ። 3እነርሱም፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ?” አሉ። 4በነጋውም ሕዝቡ ማልደው ተነሡ፤ በዚያም መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረቡ። 5የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ስላልወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፥ “ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። 6የእስራኤልም ልጆች ስለ ወንድማቸው ስለ ብንያም ልጆች አዝነው እንዲህ አሉ፥ “ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ ጠፍቶአል። 7እኛ ልጆቻችንን እንዳንድርላቸው በእግዚአብሔር ምለናልና የተረፉት ሚስቶችን እንዲያገኙ ምን እንድርግ?”
8እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር። 9ሕዝቡም በተቈጠሩ ጊዜ፥ እነሆ፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሰው አልተገኘም። 10ማኅበሩም ወደዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላን ሰዎችን ልከው፥ “ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ሴቶችንም ሕዝቡንም#ዕብ. “ከሴቶችና ከሕፃናት ጋር” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎችን” ይላል። በሰይፍ ስለት ግደሉ። 11የምታደርጉትም ይህ ነው፤ ወንዱን ሁሉ፥ ወንድ የሚያውቁትንም ሴቶች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ፤ ደናግሉን ግን አትግደሉአቸው፤” ብለው አዘዙአቸው፤ እንዲሁም አደረጉ። 12በኢያቢስ ገለዓድ በሚኖሩ መካከልም ወንድ ያላወቁ አራት መቶ ቆነጃጅት ደናግልን አገኙ፤ በከነዓንም ሀገር ወዳለችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመጡአቸው።
13ማኅበሩም ሁሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ወደ ብንያም ልጆች መልእክተኞችን ላኩ፤ በሰላምም ጠሩአቸው። 14በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ የእስራኤልም ልጆች ከኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች ሰጡአቸው። በዚህም ተስማሙ።#ዕብ. “ነገር ግን የሚበቁ ሴቶችን አላገኙም” የሚል ይጨምራል። 15እግዚአብሔርም በእስራኤል ነገድ ውስጥ ስብራት ስላደረገ ሕዝቡ ስለ ብንያም አዘኑ።
16የማኅበሩ ሽማግሌዎችም፥ “ከብንያም ሴቶች ጠፍተዋልና የቀሩት ስዎች ሚስት እንዲያገኙ ምን እናደርጋለን?” አሉ። 17ደግሞም፥ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይደመሰስ ከብንያም ላመለጡት ርስት ይኑር። 18የእስራኤልም ልጆች፥ “ልጁን ለብንያም የሚሰጥ ርጉም ይሁን ብለው ምለዋልና እኛ ከልጆቻችን ሚስቶችን ለእነርሱ መስጠት አንችልም” አሉ። 19እነርሱም፥ “እነሆ፥ በቤቴል በመስዕ በኩል፥ ከቤቴልም ወደ ሰቂማ በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል በሌብና በዐዜብ በኩል ባለችው በሴሎ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ አለ” አሉ። 20የብንያምንም ልጆች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው፥ “ሂዱ በወይኑም ስፍራ ተደበቁ፤ 21ተመልከቱም፤ እነሆ፥ የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘፈን ሲወጡ ከወይኑ ስፍራ ውጡ፤ ከሴሎ ሴቶች ልጆችም ለየራሳችሁ ሚስትን ንጠቁ፤ ወደ ብንያም ምድርም ሂዱ። 22አባቶቻቸውና ወንድሞቻቸውም ሊጣሉአችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩአቸው፥ እኛ ሚስት ለያንዳንዳቸው በሰልፍ አልወሰድንላቸውምና፥ እናንተም በደል ይሆንባችሁ ስለ ነበር አላጋባችኋቸውምና፥” እንላቸዋለን። 23የብንያምም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ በቍጥራቸውም መጠን ከተነጠቁት ዘፋኞች ሚስትን ወሰዱ፤ ወደ ርስታቸውም ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም ሠርተው ተቀመጡባቸው። 24በዚያ ጊዜም የእስራኤል ልጆች ከዚያ ተነሡ፤ እያንዳንዱም ወደ ወገኑና ወደ ነገዱ ሄደ፤ ሰውም ሁሉ ከዚያ ወደ ርስቱ ተመለሰ።
25በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 21: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ