መጽሐፈ መሳፍንት 20
20
እስራኤል ከብንያም ልጆች ጋር እንደ ተዋጉ
1የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ። 2ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ የሕዝቡ ሁሉ አለቆች ሰይፍ በሚመዝዙ፥ በቍጥርም አራት መቶ ሺህ እግረኞች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። 3የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን” አሉ። 4የተገደለችውም ሴት ባል ሌዋዊዉ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፥ “እኔና ዕቅብቴ በዚያ ለማደር ወደ ብንያም ሀገር ወደ ገባዖን መጣን። 5የገባዖንም ሰዎች ተነሡብን፤ ቤቱንም በሌሊት በእኛ ላይ ከበቡት፤ ሊገድሉኝም ወደዱ፤ ዕቅብቴንም አዋረድዋት፤ አመነዘሩባትም፤ እርስዋም ሞተች። 6እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ። 7እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላችሁ፥ ምክራችሁንና እዝናታችሁን በዚህ ስጡ።”
8ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነሥተው እንዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይሄድም፤ ወደ ቤቱም አይመለስም። 9አሁንም በገባዖን ላይ እንዲህ አድርጉ፤ በየዕጣችን እንዘምትባቸዋለን። 10በእስራኤል ላይ ስላደረጉት ስንፍና ሁሉ የብንያም ገባዖንን ይወጉ ዘንድ ለሚሄዱ ሕዝብ በመንገድ ስንቅ የሚይዙ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከመቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺሁም መቶ ሰው፥ ከዐሥሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን።” 11የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በከተማዪቱ ላይ ተሰበሰቡ።
12የእስራኤልም ነገዶች፥ “በእናንተ መካከል የተደረገ ይህ ክፉ ነገር ምንድን ነው?” ብለው ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ ሰዎችን ላኩ። 13“አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም። 14የብንያምም ልጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየከተማዎቻቸው ወደ ገባዖን ተሰበሰቡ። 15በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከገባዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አምስት ሺህ#ዕብ. “ሃያ ስድስት ሺህ” ይላል። ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገባዖንም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፤ 16ከእነዚያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተመረጡ፥ ሁለቱም እጆቻቸው ቀኝ የሆኑላቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ሁሉ ድንጋይ ይወነጭፉ ነበር፤ አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም ነበር።
17ከብንያምም ልጆች ሌላ የእስራኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተቈጠሩ፤ እነዚህም ሁሉ ሰልፈኞች ነበሩ። 18የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
19የእስራኤልም ልጆች በማለዳ ተነሥተው በገባዖን ፊት ሰፈሩ። 20የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ በገባዖንም ገጠሙአቸው። 21የብንያምም ልጆች ከገባዖን ወጡ፤ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ። 22የእስራኤልም ሰዎች ተበራቱ፤ በፊተኛውም ቀን በተሰለፉበት ስፍራ ደግመው ተሰለፉ። 23የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ።
24በሁለተኛውም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ልጆች ጋር ሊዋጉ ቀረቡ። 25በሁለተኛውም ቀን የብንያም ልጆች ሊገጥሙአቸው ከገባዖን ወጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ። 26የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለቀሱም፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትንና የደኅንነት መሥዋዕትን አቀረቡ። 27በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበረችና፥ የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ጠየቁ፤ 28በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በፊቷ ይቆም ነበርና። “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን? ወይስ እንቅር?” አሉ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጡ” አላቸው።
29የእስራኤልም ልጆች ገባዖንን የሚከብቡአት ሰዎችን በዙሪያዋ አኖሩባት። 30በሦስተኛውም ቀን የእስራኤል ልጆች ወደ ብንያም ልጆች ወጡ፤ በገባዖንም ፊት እንደ ቀድሞው ጊዜ ተዋጉአቸው። 31የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከተማዪቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለተኛውም ወደ ገባዖን ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ ሕዝቡን ይመቱ፥ ይገድሉም ጀመር፤ ከእስራኤልም ሠላሳ#ግእዝ “ሠላሳ እልፍ የሚያህሉ ሰዎች” ይላል። የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። 32የብንያምም ልጆች፥ “እንደ ቀድሞው በፊታችን ይሞታሉ” አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፥ “እንሽሽ፤ ከከተማም ወደ መንገድ እናርቃቸው” አሉ። 33የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከስፍራቸው ተነሥተው በበዓልታምር ተዋጉ። ከእስራኤልም አድፍጠው የነበሩት ከስፍራቸው ከገባዖን ምዕራብ ወጡ። 34ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባዖን አንጻር መጡ፤ ውጊያውም በርትቶ ነበር፤ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር። 35እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ጣላቸው፤ በዚያም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።
እስራኤል የብንያምን ልጆች ድል እንዳደረጉ
36የብንያም ልጆችም እንደ ተመቱ አዩ፤ የእስራኤል ልጆች ግን በገባዖን ላይ ባኖሩት ድብቅ ጦር ታምነዋልና ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው። 37ተደብቀው የነበሩትም ፈጥነው ወደ ገባዖን ሮጡ፤ ተደብቀው የነበሩትም መጥተው ከተማውን ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ። 38የተደበቁትም ሰዎች ከከተማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እንዲያስነሡ በእስራኤል ልጆችና በተደበቁት ሰዎች መካከል ምልክት ተደርጎ ነበር። 39የእስራኤልም አርበኞች ከሰልፉ ተመለሱ፤ ብንያማውያንም እንደ ቀድሞው ሰልፍ በፊታችን ተመትተዋል እያሉ ከእስራኤል ሰዎች ሠላሳ የሚያህሉ#ግእዝ “ስድስት መቶ የሚያህሉ” ይላል። ሰዎችን መምታትና መግደል ጀመሩ። 40ምልክቱም በጢሱ ዐምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደኋላቸው ተመለከቱ፤ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ። 41የእስራኤልም ልጆች ተመለሱ፤ የብንያምም ሰዎች ተሸበሩ፤ ክፉ ነገር እንደ ደረሰባቸውም አዩ። 42ከእስራኤልም ሰዎች ፊት ወደ ምድረ በዳ መንገድ ሸሹ፤ ሰልፉም ደረሰባቸው፤ ከየከተማውም የወጡት በመካከላቸው ገደሉአቸው። 43ብንያማውያንንም ወግተው አጠፉአቸው፤ በምሥራቅ በኩል ባለው በገባዖንም ፈጽመው ደመሰሱአቸው። 44ከብንያምም ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰው ሞተ፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ። 45ከእነርሱም የተረፉት ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእነርሱም በየመንገዱ ላይ አምስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድዓምም አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ። 46እንዲሁም በዚያ ቀን ከብንያም የሞቱት ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ። 47ስድስቱም መቶ ሰዎች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ በሬሞንም ዓለት አራት ወር ተቀመጡ። 48የእስራኤልም ሰዎች በብንያም ልጆች ላይ ዳግመኛ ተመለሱ፤ ሞላውን ከተማ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሜትላን ከተማ” ይላል። ከብቱንም፥ ያገኙትንም ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፉ፤ ያገኙትንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 20: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ