የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 20

20
እስ​ራ​ኤል ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር እንደ ተዋጉ
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ። 2ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ የሕ​ዝቡ ሁሉ አለ​ቆች ሰይፍ በሚ​መ​ዝዙ፥ በቍ​ጥ​ርም አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች በሆኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጉባኤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ። 3የብ​ን​ያ​ምም ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እን​ደ​ምን እንደ ተደ​ረገ ንገ​ሩን” አሉ። 4የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ሴት ባል ሌዋ​ዊዉ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “እኔና ዕቅ​ብቴ በዚያ ለማ​ደር ወደ ብን​ያም ሀገር ወደ ገባ​ዖን መጣን። 5የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ተነ​ሡ​ብን፤ ቤቱ​ንም በሌ​ሊት በእኛ ላይ ከበ​ቡት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ኝም ወደዱ፤ ዕቅ​ብ​ቴ​ንም አዋ​ረ​ድ​ዋት፤ አመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ትም፤ እር​ስ​ዋም ሞተች። 6እኔም ዕቅ​ብ​ቴን ይዤ በመ​ለ​ያ​ያዋ ቈራ​ረ​ጥ​ኋት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና ስለ ሠሩ ወደ እስ​ራ​ኤል ርስት አው​ራጃ ሁሉ ሰደ​ድሁ። 7እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላ​ችሁ፥ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንና እዝ​ና​ታ​ች​ሁን በዚህ ስጡ።”
8ሕዝ​ቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነ​ሥ​ተው እን​ዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይ​ሄ​ድም፤ ወደ ቤቱም አይ​መ​ለ​ስም። 9አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ላይ እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በየ​ዕ​ጣ​ችን እን​ዘ​ም​ት​ባ​ቸ​ዋ​ለን። 10በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ስን​ፍና ሁሉ የብ​ን​ያም ገባ​ዖ​ንን ይወጉ ዘንድ ለሚ​ሄዱ ሕዝብ በመ​ን​ገድ ስንቅ የሚ​ይዙ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከመ​ቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺ​ሁም መቶ ሰው፥ ከዐ​ሥ​ሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እን​ወ​ስ​ዳ​ለን።” 11የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።
12የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች፥ “በእ​ና​ንተ መካ​ከል የተ​ደ​ረገ ይህ ክፉ ነገር ምን​ድን ነው?” ብለው ወደ ብን​ያም ነገድ ሁሉ ሰዎ​ችን ላኩ። 13“አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ውስጥ የበ​ደሉ የዐ​መፅ ሰዎ​ችን እን​ድ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው አው​ጥ​ታ​ችሁ ስጡን፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክፋ​ትን እና​ር​ቃ​ለን።” የብ​ን​ያም ልጆች ግን የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አል​ወ​ደ​ዱም። 14የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየ​ከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ወደ ገባ​ዖን ተሰ​በ​ሰቡ። 15በዚ​ያም ቀን ከየ​ከ​ተ​ማው የመጡ የብ​ን​ያም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ከገ​ባ​ዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አም​ስት ሺህ#ዕብ. “ሃያ ስድ​ስት ሺህ” ይላል። ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤ 16ከእ​ነ​ዚ​ያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ፥ ሁለ​ቱም እጆ​ቻ​ቸው ቀኝ የሆ​ኑ​ላ​ቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ድን​ጋይ ይወ​ነ​ጭፉ ነበር፤ አን​ዲት ጠጕ​ርስ እንኳ አይ​ስ​ቱም ነበር።
17ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች ሌላ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰል​ፈ​ኞች ነበሩ። 18የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
19የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በማ​ለዳ ተነ​ሥ​ተው በገ​ባ​ዖን ፊት ሰፈሩ። 20የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከብ​ን​ያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ገጠ​ሙ​አ​ቸው። 21የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ በዚ​ያም ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ። 22የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተበ​ራቱ፤ በፊ​ተ​ኛ​ውም ቀን በተ​ሰ​ለ​ፉ​በት ስፍራ ደግ​መው ተሰ​ለፉ። 23የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።
24በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ሊዋጉ ቀረቡ። 25በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ። 26የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ። 27በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበ​ረ​ችና፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቁ፤ 28በዚ​ያም ዘመን የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በፊቷ ይቆም ነበ​ርና። “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ው​ጣን? ወይስ እን​ቅር?” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጡ” አላ​ቸው።
29የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ገባ​ዖ​ንን የሚ​ከ​ብ​ቡ​አት ሰዎ​ችን በዙ​ሪ​ያዋ አኖ​ሩ​ባት። 30በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ብን​ያም ልጆች ወጡ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ፊት እንደ ቀድ​ሞው ጊዜ ተዋ​ጉ​አ​ቸው። 31የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ#ግእዝ “ሠላሳ እልፍ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች” ይላል። የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ። 32የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፥ “እንደ ቀድ​ሞው በፊ​ታ​ችን ይሞ​ታሉ” አሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን፥ “እን​ሽሽ፤ ከከ​ተ​ማም ወደ መን​ገድ እና​ር​ቃ​ቸው” አሉ። 33የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነ​ሥ​ተው በበ​ዓ​ል​ታ​ምር ተዋጉ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አድ​ፍ​ጠው የነ​በ​ሩት ከስ​ፍ​ራ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ምዕ​ራብ ወጡ። 34ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የተ​መ​ረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባ​ዖን አን​ጻር መጡ፤ ውጊ​ያ​ውም በር​ትቶ ነበር፤ መከ​ራም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አላ​ወ​ቁም ነበር። 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ጣላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ሃያ አም​ስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።
እስ​ራ​ኤል የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ድል እን​ዳ​ደ​ረጉ
36የብ​ን​ያም ልጆ​ችም እንደ ተመቱ አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በገ​ባ​ዖን ላይ ባኖ​ሩት ድብቅ ጦር ታም​ነ​ዋ​ልና ለብ​ን​ያም ስፍራ ለቀ​ቁ​ላ​ቸው። 37ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም ፈጥ​ነው ወደ ገባ​ዖን ሮጡ፤ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም መጥ​ተው ከተ​ማ​ውን ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ። 38የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ሰዎች ከከ​ተ​ማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እን​ዲ​ያ​ስ​ነሡ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በተ​ደ​በ​ቁት ሰዎች መካ​ከል ምል​ክት ተደ​ርጎ ነበር። 39የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አር​በ​ኞች ከሰ​ልፉ ተመ​ለሱ፤ ብን​ያ​ማ​ው​ያ​ንም እንደ ቀድ​ሞው ሰልፍ በፊ​ታ​ችን ተመ​ት​ተ​ዋል እያሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ#ግእዝ “ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህሉ” ይላል። ሰዎ​ችን መም​ታ​ትና መግ​ደል ጀመሩ። 40ምል​ክ​ቱም በጢሱ ዐምድ ከከ​ተ​ማው ሊወጣ በጀ​መረ ጊዜ ብን​ያ​ማ​ው​ያን ወደ​ኋ​ላ​ቸው ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ የሞላ ከተ​ማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ። 41የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተመ​ለሱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ሰዎች ተሸ​በሩ፤ ክፉ ነገር እንደ ደረ​ሰ​ባ​ቸ​ውም አዩ። 42ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፊት ወደ ምድረ በዳ መን​ገድ ሸሹ፤ ሰል​ፉም ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ ከየ​ከ​ተ​ማ​ውም የወ​ጡት በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ገደ​ሉ​አ​ቸው። 43ብን​ያ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ወግ​ተው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በገ​ባ​ዖ​ንም ፈጽ​መው ደመ​ሰ​ሱ​አ​ቸው። 44ከብ​ን​ያ​ምም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰው ሞተ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ። 45ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ረ​ፉት ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በየ​መ​ን​ገዱ ላይ አም​ስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድ​ዓ​ምም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደሉ። 46እን​ዲ​ሁም በዚያ ቀን ከብ​ን​ያም የሞ​ቱት ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ። 47ስድ​ስ​ቱም መቶ ሰዎች ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ በሬ​ሞ​ንም ዓለት አራት ወር ተቀ​መጡ። 48የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በብ​ን​ያም ልጆች ላይ ዳግ​መኛ ተመ​ለሱ፤ ሞላ​ውን ከተማ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሜ​ት​ላን ከተማ” ይላል። ከብ​ቱ​ንም፥ ያገ​ኙ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት አጠፉ፤ ያገ​ኙ​ት​ንም ከተማ ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ